በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውሰጥ በየከተማው አሰተዉሎ ለሚመለከትው ሁሉ ብዙ ሰዎች ጫት አንደሚቅሙ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። በየቦታው የጫት ምርት katጨምራል፤ የመሸጫና የመቃሚያ ሱቆች በብዛት ተከፍተዋል፡ የመጋበዣ ማሰታወቂያዎችም እንደዚሁ በየቦታው ተለጥፈው ይታያሉ። ዘር፤ ሀይማኖት፤ ጾታ፤ የሰራ አይነት ወዘት ሳይገድበው ሁሉም የህብረተስብ ክፍል ጫት በመቃሙ ተግባር የተሰማራ ይመሰላል። አሰተማሪዎች ሳይቀሩ ተማሪዎቻቸዉን ጫት በጉንጫቸው ይዘው በክፍል ዉሰጥ አንደሚያሰተምሩ ይነገራል። ወላጆችም አንደዚሁ ብስለት በሊላቸው ልጆቻቸው ፊት ያለአንዳች ገደብ ወይም ጥንቃቂ ጫቱን ያላምጣሉ። ያለው ሁኒታ እንደዚህ የሚቀጥል ከሆነ ድርጊቱ ወደሚቀጥለው ትዉልድ አንደሚተላለፍ ያመለክታል። የጫትን ጉዳት ለተገነዘቡ ዚጎች የሚታየው ሁኒታ አሳሳቢ አየሆነ መጥታል። “ሁኒታው ለምን ከዚህ ደረጃ ለመድረሰ ቻለ?” የሚል ጥያቂ ሊነሳ ይችላል።

ለዚህ ሁኒታ ካሰቻሉት ምክኒያቶች መካከል የሚቅጥሉት ጉልተው የሚታዩት ናቸው፦
– ጫት ሱስ እንደሚያሲዝና ለጉዳት እንደሚያጋልጥ በትክክል እለመገንዘብ
– በጫት ምርት፤ ሸያጭ/ግዢና አጠቃቀም ላይ ቁጥጥር አለመኖሩ።
– ለጫት ምርት፤ ሸያጭ/ግዢና አጠቃቀም የሚያበረታቱ (በተለይም በመንግሰት በኩል) ሁኒታዎች መኖራቸው።
– በተለያዩ የፖለቲካ ችግሮች ምክኒያቶች የተነሳ ለተፈጥረው የግለሰቦች የሞራል ውድቀት እንደመወጫ መንገድ አድርጎ ጫትን መጠቀም።

አሳሳቢ የሆነውን የጫት ችግር ለማቃለል የእጹን ጉዳት በሚገባ ማወቅ የሚያሻ ነው። ጫት ሲቃም የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ የሚችል ሲሆን ዋናውቹ ቅጥሎ የተመለከቱት ይሆናሉ፡፤
– በአእምሮ ላይ ለተወሰነ (አጭር) ጊዚ የንቃትና የደስታ ሰሚቶችን ፈጥሮ በማታለል ወደ ድብርትነት፤ መረበሸና ቀውሰነት/እብድነት እንዲያመሩ ያደርጋል። ይህ የአእምሮ ሁኒታ ሱሰ ይሚያሰከትል ሰለሚሆን ተጠቃሚው ጫቱን መውሰድ ይቀጥላል፤ እንዲያውም በየወቅቱ ከቀድሞው በበለጠ መጠንና ጊዚ። ለማገናዘብ ያህል በዚህ መልክ ከጫት የሚገኝው የአእምሮ ሰሚት አምፊታሚን ተበሎ ከሚታወቀው ሱሰ አምጪ መድሃኒት ጋር የሚመሳሰል ነው።
– ሆድና አንጀት ላይ በሚያደርገው ክንዋኒ ውይም ሰራ ድርቅትን ያመጥል። በአእምሮ ላይ የሚያደርገው ድርጊት ተጨምሮ የምግብን ፍላጎትንም ይቀንሳል። ይህ ሰውነትን የሚያመነመንና በጀርም ምክኒያት የሚተላለፉ በሸታዎችን የመከላከልን አቅም የሚቀንሰ ይሆናል፤ እንደ ቲቢና ሂፓታይትሰ ለመሳሰሉ የበሸታ አይነቶች ያጋልጣል።
– የተለያዩ የአፍ ውሰጥ በሰታዎችንና የጥርሰ መበለዝን ያሰክትላል።
– ጫት እንደተወሰደ የልበን የመምታት ሰርና የደም ብዛትን/ግፊትን ይጨምራል፡፡ ከረጅም ጊዚ ጠቀም በሃላም ቢሆን የደም ብዛት እንደጨመረ ይቀጥላል።
– ወንድ በሆኑ ቃሚዎች ላይ የግብረሰጋ ግንኙንት ፍላጎትንም ሆነ ችሎታን ይቀንሳል። መሃን የመሆንም እድል ይጨምራል።
– ጫት ከሚቅሙ ሲቶች የሚወልውዱ ልጆች ክብደታቸው ያነሰ እንደሆነ ተመዝግባል። እናቶቹም በቂ የጡት ወተት የሚሰጡ እይደሉም። ሰለሆነም ልጆቹ ጥሩ የሆነ የእድገት ደረጃ ላይኖራቸው ይችላል።

የተጠቀሱትና ሊሎችም በጫት ምክኒያት የሚነሱ ህመሞች በብዛት የሚያጠቁት ያረጁና ቀድሞውኑም በሸታ ያለባቸውን ቃሚዎች ነው።

ጫት በሚቃምበት ጊዚም ሆነ በሃላ ሊሎች ነግሮችም አብረው እንደሚወስዱ የተለመደ ነው። ከነዚህም መካከል ሰካር መቃም ወይም ሰካርነት ያላቸውን ለሰላሳ መጠጦች መጎንጨት፤ ሲጋራ ማጨሰና የአልኮል መጠጦችን መውሰድ የገኛሉ። ሰካርን ያለአገባብ መውሰዱ የሰካር በሽታ ላለው ተጠቃሚ የሚበጅ አይደለም፡ ለጥርሰም ጢንነት ቢሆን እንደዚሁ ጥሩ አይደለም። ሲጋራ ማጨሱ በይበልጥ ለሳንባና ለልብ በሰታዎች የሚያጋልጥ ይሆናል። የአልኮል መጠጥ በራሱ ጎጂ ሆኖ ሳለ የሚጠጡትን ጫት ቃሚዎች በይበልጥ ወደሰህተት በማምራት ጥንቃቂ የጎደለው የገብረሰጋ ግንኙነት እንዲያደርጉ የመራቸዋል። በዚህም የተነሳ የአባለዘር በሸታዎች ሊይዛቸው ይችላል፡ በሸታውም ካላቸው ወደሊላ ያሰተላልፋሉ። በቅርቡ በተደረገው ጥናት፤ ጫት ቃሚዎች በብዛት/በቀላሉ በኢይድሰ ባይረሰ ሊበከሉ እንደሚችሉ ወይም ከተበከሉም ወደሊሎች ሊያሰተላልፉ እንደሚችሉ ታውቃል።

ጫት በጢንነት ላይ ከሚያመጣው ጉዳት በተጨማሪ ኢኮኖሚንም ይጉዳል። ይህ የሚሆነው ለጫት መገዣ ተብሎ ገንዘብ ሰለሚወጣንና በጫት መቃም ምክኒያት በቂ ለኑሮ ተፈላጊው ሰራ ሰለማይሰራ ነው። ይህ ሁኒታ የግለሰቡን ቃሚም ሆነ የተሪጂዎችን ኑሮ ያቃዉሳል። ከፍቅር መጋደል ጋር ታክሎ፤ ችግሩ ወደ ቢተሰብ መፋረሰ ሊያመራ እንደሚቸል የታየ ጉዳይ ነው። በዚህ በኩል ተመሳሳይ የሆነ የብዙ ቢተስቦች ሁኒታ ሲደማመር፤ ችግሩ ህብረተሰብንም፤ ብሎም መላው አገርን፤ የሚመለክት ይሆናል ማለት ነው።

በሱሰ አምጪነቱ ምክኒያትና በሚያሰከትለው ጉዳት የተነሳ፤ በብዙ የውጭ አገሮች ያለፈቃድ ጫትን ማምረት፤ መሸጥ፤ መግዛት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው። ሕጉ ከተጣሰ የሚያሰቀጣ ይሆናል። እንደምሳሊ ለመጥቀሰ ያሀል ይህ ሁኒታ በአሚሪካ አገር በየጊዚው እየታየ ያለ ጉዳይ ነው። ወደጎረቢት አገር ስናተኩር ደግሞ፤ የመንም ይህንን ፈለግ እየተከተለች ነው። የአለም የጢና ጥበቃ ድርጅትም ሆነ ተመሳሳዩ የአፍሪካ ድርጅት የጫትን አጠቃቀም ሁኒታ በሕግ የመቆጣጠር ደንብ አላቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ አይነት ወይም ተመሳሳይ የሆነ ሕግ ወይም ደንብ የለም። ሰለሆነም ጫት ያለአንዳች ገደብ በሕዝብ እንደቆሎ እየተቃመ ነው፡ ጉዳትም እያሰከተለ ይገኛል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ሕግ አውጪ የሆነው የአቶ መለሰ መንግሰት ከዚህ ሁኒታ ተጠቃሚ ሰለሆነ በአሁኑ ወቅት በዚህ በኩል መልካም ነገር ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም። ለማናቸውም ሕጉ እሰከሚታወጅ ድረሰ ህዝብን ማሰተማሩ የግድ አሰፋላጊ ነው። ይህች ጽሁፍ በመጠኑም ቢሆን ለዚህ ተግባር ታገለግላለችበሚል ተሰፋ የቀረበች ናት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.