የወር አበባ ለምን ይዛባል?

7

manustrationበተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የወር አበባ ሊዛባ ይችላል፡፡ ለመፍትሄው ግንዛቤ እንዲኖር መነሻዎችን መረዳት ያሻል፡፡ እንደ መንደርደሪያ የሚከተለውን ሃሳባዊ ገጠመኝ እንመልከት፡- ‹‹እድሜዬ 28 ነው፡፡ ላለፉት ስድስት ወራት አካባቢ የወር አበባዬ ተዛብቷል፡፡ አንዴ ይመጣል ሌላ ጊዜ ደግሞ ይጠፋል፡፡ አሁን ዳግም ይባስ ብሎ ጭራሹኑ ጠፍቷል፡፡ ላለፉት ሶስት ወራት ያህል፡፡ እንዲህ አይነት ችግር አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ባለሙያ ማማከር ያሻኛል? ለመሆኑ መነሻው ምን ይሆን?››
ለክፉም ለደጉም ባለሙያ ማማከር መልካም ነው፡፡ የችግሩ መነሻ ምክንያቶች ብዙ ስለሆኑ ፊት ለፊት ሲወያዩባቸው በገጠመኙ ከተመለከተው ሃሳብ በላይ ተጨማሪ ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ የሆነው ሆኖ ቀን እያዛባ የሚመጣ የወር አበባ የተለያዩ ሁኔታዎችን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል፡፡
ያለፈ ጊዜ የጤና ችግር፣ አንዳንድ መድኃኒቶች፣ የአኗኗር ዘይቤ እንዲሁም አሁን ያለዎት አጠቃላዩ የጤና ሁኔታ የወር አበባ ኡደትን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡ ከአንድ የወር አበባ ኡደት (እንደሚታወቀው) ከአንድ ፔሬድ መጀመርያ ቀን እስከሚቀጥለው ፔሬድ የመጀርያ ቀን ይቆያል፡፡ ይሄ የጊዜ ርዝመት ለሁሉም ሴቶች እኩል ወይም አንድ አይነት አይደለም፡፡ አብዛኛዎቹ በየ21 እስከ 35 ቀን፣ በአማካይ በየ28 ቀን የወር አበባ ያያሉ፡፡ የወር አበባ ከ2 እስከ 7 ቀን ሊቆይ ይችላል፡፡ የአንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ቀን የማያሳልፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ በየጊዜው በየ24 ቀኑ የሚመጣ ለ4 ቀናትም የሚቆይ የሆነ፣ አለበለዚያ ደግሞ በተወሰነ መልኩ የተዛባ፣ የሚፈሰው የደም መጠን የበዛ ወይም በጣም አነስተኛ፣ የወር አበባ በመጣ ቁጥር በህመም የታጀበ፣ ምንም ህመም የሌለበት፣ ለረዥም ወይም ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ለወራት ያህል ምንም ሳያዩ ከቆዩ ግን ምርመራ ማድረግ ወይም ባለሙያ ማማከር ተገቢ ይሆናል፡፡
በመጀመርያ መታሰብ የሚኖርበት ጉዳይ እርግዝና ነው፡፡ በጠያቂዋ እድሜ (28 ዓመት) የወር አበባን ለአንድ ጊዜ አለማየት እርግዝናን ለማሰብ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ማረጋገጥ ግን ያስፈልጋል፡፡ የወር አበባ ቢዛባ እንኳን ለማርገዝ የሚያስችለው ወቅት እንደተጠበቀ ነው፡፡ እርግዝና አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ከባለሙያ ጋር መመካከር መልካም ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተዛባ የወር አበባ ከነበረ በአሁኑ ወቅት የተዛባው በተመሳሳይ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ችግርም ላያስከትል ይችላል፡፡ ቀደም ሲል ቀኑን ጠብቆ ይመጣ ከነበረ እና ምናልባትም የአልትራሳውንድ ምርመራ ተደርጎልዎት ውሃ የቋጠረ የመራቢያ አካል(ovary)እጢ ወይም መሰል ችግር ከነበረበት አሁን የገጠመዎት ችግር ከእሱ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡
ባለሙያ በሚያማክሩበት ጊዜ የሚወስዱትን ማንኛውም መድሃኒት ዝርዝር ይናገሩ፡፡ ለውጥረትም ይሁን ለጭንቀት የሚሰጡ መድሃኒቶች የወር አበባን ሊያዛቡ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከፍተኛ ውጥረት የወር አበባን ሊያዛባ ይችላል፡፡ ከልክ ያለፈ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግም ጨርሶውኑ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ያጠፋዋል፡፡ የክብደት መቀነስና የአመጋገብ ችግርም በቂ መነሻዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ለሃኪምዎ የገለጧቸው ሁኔታዎች ምንጭ ካልሰጡ ቀጣዩ ሃላፊነት የባለሙያው ይሆናል ማለት ነው፡፡ የታሮይድ እጢ ችግር የወር አበባ መዛባት ሊያስከትል ይችላል፡፡
ሌሎች የተለያዩ ችግሮች የወር አበባ መዛባት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የደም ማነስ፣ አባላዘር በሽታ ወዘተ፡፡ የወር አበባ መቆሚያ ወቅት(ማረጥ) ሲቃረብ እንዲህ አይነት ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡ የወር አበባ መዛባት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ምልክቶችም ይኖሩታል፡፡ ላብና ሰውነትን የመወበቅ ስሜት እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡ በ20ዎቹና በ30ዎቹ የእድሜ ክልል የማረጥ መቃረብን የሚያሳዩ ምልክቶች አይኖሩም፡፡
ለማንኛውም የወር አበባ ለምን እንደተዛባ፣ ከዚያም አልፎ ለምን እንደቀረ ለመረዳት ባለሙያ መጎብኘት መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ የወር አበባ መዛባት ተዘውትሮ የሚከሰትበት የእድሜ ክልል በአስራዎቹ ባሉ ወጣት ሴቶች ላይ ነው፡፡ ቀኑን በትክክል ተከትሎ ለመምጣት አንድ አመት አካባቢ ይፈጃል፡፡ የኮረዳነት ወቅት የሆርሞን ፍሰቶች ሚዛን ሊያዛባ ይችላል፡፡ ይህም የወር አበባ መዛባትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ባስ ሲል ወር እያሰለሰ ወይም በአጫጭር ጊዜ ስንዝር ሊመጣ ይችላል፡፡ አንዲት ወጣት ወር አበባ ማየት ካየችበት ጊዜ አንስቶ ከአመት በኋላ መዛባቱ ከቀጠለ ከተፈጥሮ ፍሰት ውጭ ሊሆን ስለሚችል ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው፡፡
በአጠቃላይ ጤና ብቻ ሳይሆን ሰውነትን በሌላ መልኩ ስለሚጎዱ የወር አበባ መዛባትን አስከትለው ሊሆን ይችላል፡፡ ከባድ እንቅስቃሴ የወር አበባን ከማዛባት እስከ ማስቀረት ሊያርሰው ይችላል፡፡ መጠነኛ እንቅስቃሴ ግን ውጥረትንም በመቀነስ የተዛባ የወር አበባን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ ያህል በቀን ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡
የወር አበባ ማየት (ቢዛባም እንኳ) ለቻለ ሁሉ ለመቅረቱ መነሻ ምክንያት እርግዝና ሊሆን ይችላል፡፡ እስከሚያረጋግጡ ድረስ እርጉዝ ነኝ ብሎ ማሰቡ ክፋት የለውም፡፡ እርጉዝ ካልሆኑ የሚከተሉት የወር አበባ እንዲቀር ወይም እንዲዛባ መነሻ ይሆናሉ፡፡
*.ከልክ ያለፈ ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር፡፡ ምንም እንኳን የክብደት መጠን ዝቅተኝነት የተለመደ ቢሆንም ከልክ ያለፈ ውፍረትም የወር አበባን ሊያዛባ ይችላል፡፡
*.የአመጋገብ ችግር (ከልክ በላይ መብላት ወይም ከበቂ በታች መብላት)
*.ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፤ የወር አበባን አለማየት ከባድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ለረዥም ጊዜ በሚያካሂዱ ስፖርተኞች ላይ ይከሰታል፡፡
*.ውጥረት
*.ህመም
*.ጉዞ(የረዥም ርቀት ጉዞ)
*.መድሃኒቶች፣ ለምሳሌ ያልተፈለገ እርግዝና ለመከላከል የሚወሰዱ ታብሌቶች፣ ቀለል ያለ አልፎ የሚመጣ፣ ቶሎ ቶሎ የሚመጣ ወይም የወር አበባው ጭርሱኑ እንዲቀር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
*.የሆርሞኖች መዛባት፣ የሆርሞኖች ሚዛን መጠበቅ
*.ህገወጥ እፆችን መጠቀም
*.በማህፀንና በማህፀን ዙርያ ካሉ የሰውነት ክፍሎች አካባቢ በሚከሰቱ ችግሮች
*.ጡት ማትባት፣ ብዙ የሚያጠቡ እናቶች አጥብተው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ የወር አበባ ቀኑን ጠብቆ አይመጣም፡፡
ምንም እንኳን የወር አበባ ቢያዩም እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ያስቡበት፡፡ እርጉዝ መሆን ካላሰቡ የወሊድ መከላከያ ይጠቀሙ፡፡ ቀድመው ለረዥም ጊዜ በማሰብ የድንገተኛ የወሊድ መከላከያ እንክብሎችን ደጋግሞ ላለመጠቀም ያስቡበት፡፡ የወር አበባን ሊዛባ ስለሚችል፡፡
የመራቢ አካል ድክመት(ovarian failure)ሲያጋጥም የወር አበባ ሙሉ በሙሉ ያቆማል፡፡ ያለወቅቱ ተከሰተ የሚባለው ከ40 አመት በፊት ሲያጋጥም ነው፡፡ በሆድ እቃና በዳሌ አካባቢ የሚደረጉ የቀዶ ጥገና፣ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምና ችግሩን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
የቲቢ፣ የጉበት፣ የስኳርና ሌሎች ተቀራረቢ ህመሞች የወር አበባ እንዲቀር ወይም እንዲዛባ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ህመሞች አንዱ ካለ በወር አበባ መዛባት ብቻ ሳይሆን ከመሰረታዊ ምልክቶቹ ጋር ይከሰታል፡፡
የወር አበባዬ አልመጣም ብለው አይጨነቁ፡፡ ለስሜታዊም ይሁን ለአካላዊ ሚዛን መጠበቅ ሲባል ዘና ይበሉ፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን ብዙ ሴቶች በተደጋጋሚ የወር አበባቸው ይዛባባቸዋል፡፡ እርስዎም ከተዛባብዎት እርጉዝ ካልሆኑ ቢቀር የወር አበባዎን በሚቀጥለው ወር ይጠብቁት፡፡

 

7 COMMENTS

  1. yemeemeriya lijen ke weledku 5 wer honognal ke welid bohala wera bebaye simeta betam yibezabignal betechemari kewelid befit 3 ken bicha yikoyi yenebere ahun le samint belay yikoyal. Mensiew ina Meftihew bitinegirugn.
    Ameseginalehu!

  2. werabebaye simeta yihimem simetu kedimo jemro iskiyalif dires yaschegiregnal siram mesirat alchilim ke himemu yetenesa
    meftihe bititokumugn

    • የወር አበባዮ በጣም ይዛባል ማለትም 15 ካለም 10 ቀን ሊመጣ ይችላል ከዚህ በላይ ያሳሰበኝ በመሀላ የሚፈሰኝ የደረቀ ደም ማለት ጥቁር ወፍራም ግራ ገብቶኛል

  3. Hi ene meteyek yefelekut be and wer hulete ymetal malet 14 august jemro 18 august cheresku. Keza demo 30 august endegena meta 3 september akome ahun demo 23 september endegena meta. Ena yehone chigr ynorewal mels etebkalewu thanx

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.