የሰውዬው ‹‹ብታከመው ብታከመው ከውስጤ አልወጣልህ ያለኝን ጃርዲያን በምን ልከላከል?›› ጥያቄና የዶ/ሩ ምክር

0

ጃርዲያ የሚባል በሽታ ከምን ይመጣል? መከላከያውስ ምንድን ነው? ብዙ ጊዜ እየደጋገመ ይይዘኛል፡፡ ምን ላድርግ? ብታከምም እስከመጨረሻው ከበሽታው ልድን አልቻልኩም፡፡
ይማም አበበ ነኝ

giardia-trph1የጃርዲያን ኢንፌክሽ /giardiasis/ የአንጀት ኢንፌክሽን ሲሆን የሚታወቀው በሆድ ቁርጠት፣ ሆድ መንፋት፣ ቋቅ ማለጽና ቀጭን ተቅማጥ የህመሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ በሽ በብዛት የሚመጣው በመላው ዓለም በሚገኝ ነገር ግን የፅዳት ችግር በሚታይባቸውና ለመጠጥ ብቁ ያልሆኑ ውሃ ተጠቃሚዎች ዘንድ ነው፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ ይህ በሽታ በውሃ ከሚታለለፉ በሽዎች ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ በአሜሪካንም ቢሆን በውሃ ከሚታለለፉ በሽታዎች እንዲሁ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ የጃርዲያ ኢንፌክሽን በምግብና ከሰው ወደ ሰውም ሊተላለፍ ይችላል፡፡
የዚህ በሽታ አብዛኛው ምልክቶች መጥፎ ጠረን ያለው ቀጭን ተቅማጥ አንዳዴ ለስለስ ያለ፣ አንዳንዴ ልፋጭ ያለው ሲሆን፣ ድካም፣ የሆድ ቁርጠትና መነፋት፣ ቋቅ ማለት እና የክብደት መቀነስ ናቸው፡፡

የዚህ በሽታ አምጪ ፓራሳይት /ተህዋስ/ ጃርዲያ ላምብሊያ /giardia lambila/ ሲባል ሁለት አይነት መልክ አለው፡፡ ይኸውም ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ ይባላሉ፡፡ ምርመራው የሰገራ ናሙናን በመውሰድ በማይክሮስኮፕ በማየት መለየት የሚያስችል ዘዴን በመጠቀም ነው፡፡

ይህ በሽታ በተለያዩ አንቲባዮቲክ መድሃኒቶች ሊታከም ይችላል፡፡ ነገር ግን ከምንም በላይ ንጽህና በመጠበቅ ሊጠፋ ስለሚችል ንፅህና ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግ ይገባል፡፡ ከህክምናው በላይም ንፅህናቸውን የጠበቁ ምግቦችና ፈሳሾችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ንጽህና ሳይኖር ህክምናው ብቻውን ለህመሙ መፍትሄ አይሆንም፡፡

ነገር ግን እርጉስ ሴቶች በመጀመሪያው ሶስት ወራት ለጃርዲያ ተብለው የሚሰጡ መድሃኒቶችን መጠቀም አይገባቸውም፡፡ ይህንን በሽ በቀላሉ ለመከላከል እጅን ምግብ ከመብላት በፊት፣ ሽንት ቤት ከሄድን በኋላ፣ ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት በደንብ አሽተን በሳሙና መታጠብ ውሃን ማጣራትና ማፍላት /ነገር ግን በክሎሪን ብዙም መፍላት የለበትም/፣ ሰገራ በሜዳ ላይ መውጣት ካለበት መቀበር አለበት፣ ዋና በሚዋኝበት ጊዜ አፍን መዝጋት ያስፈልጋል፡፡

በቧንቧ ውሃም እንኳን አሜሪካንን የሚያክል ሀገር እንዲተማሙ አይመከርም፡፡ ምክንያቱም አልፎ አልፎም በአሜሪካም ሳይቀር የቧንቧ ውሃ በተለያየ ምክንያት ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ በአካባቢያችን የጃርዲያ በሽታ ከተቀሰቀሰ የታሸገ ውሃ መጠቀም ይመከራል፡፡ በጉዞ ጊዜ የታሸገ ውሃ መጠቀም ይመከራል፡፡ በፊንጢጣ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይህንን በሽታ ስለሚያመጣው ይህ አይነት ድርጊት በስፋት በሚኖርባቸው ሀገሮች ኮንዶም መጠቀም ይመከራል፡፡ አልያም ከነጭራሹ ይህን ተግባር አለመፈፀም የተሻለ ነው፡፡

ጃርዲያ በጣም በከፍተኛ ደረጃ የሚተላለፍ በሽታ በመሆኑ ይህ በሽ ያለበት ሰው ጠያቂያችንንም ጨምሮ እጁን በሳና በደንብ አድርጎ ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ ዋና አለመዋኘት ከዋኙም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩና ንፁህ ውሃ በተሞላ ገንዳ ወዘተ… መጠቀም ይመከራል፡፡

Source:: Zehabesha

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.