ሺሻ የማጨስ አደጋዎች –

shishaመቀመጫውን በአሜሪካው ጆርጂያ ክፍለ ግዛት ፣ አትላንታ ከተማ ያደረገው በአለም ታዋቂው የጤና የምርምር ተቋም Centers for Disease Control and Prevention (CDC) ሺሻ የማጨስን አደገኛነት አስመልክቶ ያወጣው ሊነበብ የሚገባው መረጃ። በኢትዮትዩብ የዝግጅት ክፍል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
 እንደ ሲጋራዎች ሁሉ፣ ሺሻ ማጨስ ኒኮቲን የተባለውን ሱስ የሚያሲዝ እጽ የሚያስተላልፍ ከመሆኑም ባሻገር በትንሹ፣ ሲጋራ የማጨስን ያህል መርዛማ ነው። ብዙ የሺሻ አጫሾች ድርጊቱ ከሲጋራ ያነሰ ጉዳት ያስከትላል ብለው ቢያስቡም፣ ሺሻ ማጨስ የሲጋራ ማጨስ የሚያስከትላቸውን አብዛኛዎቹን የጤንነት ስጋቶች ያዘለ ነው።
ሺሻዎች ጣእም እንዲኖረው ተደርጎ ለየት ባለ መልክ የተሰራ ትምባሆን ለማጨስ የሚያገለግሉ የውሀ ቱቦዎች ናቸው። የተለያየ ስያሜም አላቸው፣ ሁካ፣ ሺሻ እና የመሳሰሉት። አብዛኛውን ጊዜ ሺሻ የሚጨሰው በህብረት ሲሆን፣ አንዱ ሰው አፉ ውስጥ ያስገባውን ለሚቀጥለው ሰው ያስተላልፋል።
ከቅርብ አመታት ወዲህ፣ የሺሻ ተጠቃሚ ብዛት በአለም ዙሪያ ጨምሯል፣ በተለይ በወጣቶች እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዘንድ።

ስጋቱ

በ2012 እ.ኤ.አ የታተመው የCDC Preventing Chronic Disease ጥናት እንደሚጠቁመው፣ አብዛኞቹ የሺሻ አጫሾት ሺሻን ማጨስ ከሲጋራ ባነሰ ሁኔታ ከትምባሆ ጋር ተያያዥ ጉዳት ያስከትላል የሚል እምነት አላቸው። ነገር ግን፣ የሺሻ ጭስ የሲጋራ ጭስ ውስጥ የሚገኙትን በርካታ መርዛማ እፆች በውስጡ ከመያዙም በላይ፣ ከሳንባ ነቀርሳ(lung cancer)፣ የአተነፋፈስ ጋር የተያያዘ ህመም(respiratory illness)፣ የተወለደ ህፃን ክብደት ማነስ(low birth weigh)እና የጥርስ በሽታ(periodontal disease) ጋር የተቆራኘ ነው። የአለም የጤና ድርጅት(WHO) እንደዘገበው፣ በሺሻ ማጨስ ወቅት አንድ አጫሽ ሲጋራ ቢያጨስ ከሚያጋጥመው ረዘም ላለ ጊዜ ለበለጠ ጭስ ሊጋለጥ ይችላል። በተጨማሪም፣ ለማጨስ ከሚጠቀሙበት ዘዴ የተነሳ – የአሳሳቡን ድግግሞሽ፣ የምገቱን ጥልቀት እና የማጨሻ ጊዜ ርዝመቱን ጨምሮ – የሺሻ አጫሾት በሲጋራ ጭስ ውስጥ የሚገኘውን መርዛም እፅ ከፍ ያለ መጠን ወደ ውስጣቸው ያስገባሉ።

የሺሻ ጭስ እና ነቀርሳ (Cancer)

– ሺሻ ውስጥ የሚገኘውን ትምባሆ ለማሞቅ ጥቅም ላይ የሚውለው ከሰል ከፍተኘ መጠን ያላቸውን ካርቦን ሞኖክሳይድ፣ ብረት እና ነቀርሳ(cancer)-አስከታይ ኬሚካሎችን በማመንጨት የጤና ስጋቶችን ይጨምራል።
– ለ1 ሰአት  በቆየ መደበኛ የሺሻ ማጨስ ወቅት 200 ምገቶች ሲኖሩ፣ ሲጋራ በአማካይ 20 ምገቶች ይኖሩታል። በመደበኛ የሺሻ ማጨስ ወቅት የሚሳበው ጭስ መጠን ወደ 90000 ሚሊሊትር የሚጠጋ ሲሆን፣ በአንፃሩ ሲጋራ በማጨስ ጊዜ ከ500-600 ሚሊሊትር ይሳባል።
– ትምባሆ ለማጨስ ሺሻ መጠቀም ለአጫሾች እና ወደ ውጭ የሚወጣው ጭስ ለሚደርሳቸው ሰዎች አደገኛ የሆነ የጤና ጠንቅ ነው።

ወጣቱን ስለ አደጋዎቹ ማስተማር

Opportunities for Policy Interventions to Reduce Youth Hookah Smoking in the United States በሚል ርእስ የCDCው Preventing Chronic Disease ያሳተመው ጥናት እንደሚያሳየው፣ የወጣቶችን ሺሻ ተጠቃሚነት መቀነሻ መንገድ አንዱ ሺሻ ማጨስ ስለሚያስከትለው የጤና ቀውስ ትምህርት መስጠት ነው። የአለም የጤና ድርጅት (WHO) የሚከተሉት የማህበረሰብ ጤና ድህንነት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አጥብቆ ይመክራል፦
  • ሺሻዎች ሲጋራዎች በሚገዙባቸው ህግጋት ስር እንዲውሉ
  • ሺሻዎች ጥብቅ የሆነ ማስጠንቀቂያ እላያቸው ላይ እንዲለጠፍ
  • የጤና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት መሆኑን ለማሳነስ የሚሞክሩ ጽሁፎች ሺሻዎች ላይ መለጠፍ እንዲከለከል
  • ሲጋራ ማጨስ ክልክል የሆነባቸው ቦታዎች ላይ ሺሻ ማጨስም እንዲከለከል።
Source- ethiotube.net

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.