ከፍቅረኛዬጋ ወሲብ ስናደረግ የመጀመሪያውን ዙር አብዛኘውን ጊዜ እኔ ነኘ ምቀድማት ይሄስ ችግር አለው እንዴ ከጤና አኮያ?

ስለወንዶች ብልት ያለመቆም ችግር የተወሰኑ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ማዉጣታችን ይታወሳል፡፡ብዙዎቻችሁ ፖስታችንን ካነበባችሁ በኃላ ስለ የወንዶች ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር መረጃ እንድንሰጣችሁ አስተያየቶቻችሁን ኢንቦክስ ባደረጋችሁልን መሰረት በወንዶች ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር ላይ የተወሰኑ መረጃዎች እነሆ:-

የወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ
የወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ የሚከሰተዉ አንድ ወንድ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እራሱ ወይም የትዳር/የፍቅር አጋሩ ሳይፈልጉ ቀድሞ ማፍሰስ ካለ ነዉ፡፡ ግምቶች ቢለያዩም ይህ ሁኔታ ከ3 ወንዶች ዉስጥ በአንዱ ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ ችግሩ ሁልጊዜ የማይከሰት ከሆነ ግን አሳሳቢ አይደለም፡፡

የወንድ የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር አለ የምንለዉ
• ሁሌ ወይም ብዙዉን ጊዜ የወንዱ ብልት በሴቷ ብልት ዉስጥ በገባ በአንድ ደቂቃ ዉስጥ የወንድ ዘር ከፈሰሰ
• ሁሌ ወይም ብዙዉን ጊዜ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንድ ዘር መፍሰስን ማቆየት/ማዘግየት ካልተቻለ
• ጭንቀትና በራስ ያለመተማመን ስሜት በመፈጠሩ ፆታዊ ግንኙነት ላለማድረግ መፈለግ ካለ

ስነልቦናዊና ባዮሎጂካል ጉዳዮች ለወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ መከሰት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳ ብዙ ወንዶች ስለ የወንዶች የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር ለማዉራት ቢያፍሩም/ቢያሳፍራቸዉም ይህ ጉዳይ በጣም ብዙ ጊዜ የሚከሰትና በቀላሉ ሊታከም የሚችል ነዉ፡፡ መድሃኒቶች፣የምክር አገልግሎትና የግብረስጋ ግንኙነት ቴክኒክ ወይም የእነዚህ ድብልቅ የወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡

ምልክቶች
ቀዳሚ ምልክቶቹ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንድ ዘር ፈሳሽን ከአንድ ደቂቃ በላይ ማዘግየት ያለመቻል ሲሆን ይህ ሁኔታ እራስ በራስን ከማርካት አንስቶ በየትኛዉም የግብረስጋ ግንኙነት ሁኔታዎች ዉስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡
የወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር በሰዉየዉ የህይወት ዘመን ያለ(ፕራይመሪ) ወይም አኳየርድ(ሰከንደሪ) ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡ በህይወት ዘመን ያለ(ፕራይመሪ)የወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር የሚጀምረዉ አንድ ወንድ የመጀመሪያዉን የግብረስጋ ግኑኙነት ካደረገበት/ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለ ሲሆን ሁለተኛዉ አይነት ደግሞ በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ያለምንም ችግር የግበረስጋ ግንኙነት ሲያደርግ ቆይቶ ከጊዜ በኃላ የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር ሲገጥሞት የሚመጣ ነዉ፡፡
ብዙ ወንዶች ምንም እንኳ ከላይ በተገለፀዉ መሰረት የወንድ ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር ባይኖራቸዉም ይህ ችግር እንዳላቸዉ አድርገዉ ይወስዳሉ፡፡

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?

ብዙዉን ጊዜ/በተደጋጋሚ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት የወንድ ዘር ፈሳሽዎ እርስዎ ካቀዱት ጊዜ በፊት አስቀድሞ የሚወጣ ከሆነ ምንም ሳያፍሩ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብቻ/አልፎ አልፎ የሚከሰት የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር ምንም ችግር የሌለዉ ስለሆነ መጨነቅ አያስፈልጎትም፡፡

ለወንድ ዘር ቀድሞ መፍሰስ ችግር ምክንያቶች
ለዚህ ችግር ምክንያት የሆነ ይህ ነዉ የሚባል ትክክለኛ መንስኤ የለዉም፡፡ ነገር ግን የሚከተሉት ምክንያቶች ይጠቃሳሉ፡፡

ስነልቦናዊ ምክንያቶች
የተወሰኑ የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ቀድሞ የነበረ የግብረስጋ ግንኙነት ልማድ ለመቀየር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ እነሱም:-
• ማንም እንዳያዮት በመፈለግና በቶሎ የእርካታ ጣሪያ ላይ ለመድረስ መቸኮል
• በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት በፍጥንት እንዲያደርጉ የሚያደርግዎ የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ

ሌሎች ለወንዶች ዘር በቶሎ መፍሰስ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች፡-
• የወንዶች ብልት ያለመቆም ችግር ካለ
• መረበሽ/ ጭንቀት ካለ
• ከትዳር ወይም ፍቅር አጋርዎ ጋር የመስማማት ችግር ካለ

ባዮሎጂካል ምክንያቶች
የሚከተሉት ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡-
• የሆርሞን መጠን መዛባት
• በጭንቅላት/አዕምሮ ዉስጥ ያሉ ኒዩሮትራንስሚተርስ መጠን መዛባት
• የወንዶችን የዘር ፈሳሽ መረጨትን የሚቆጣጠረዉ ዘዴ ላይ ችግር መኖር
• የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት
• በፕሮስቴት ዕጢ ወይም በዩሬትራ ላይ ኢንፌክሽንና መቆጣት መከሰት
• በዘር የሚወረስ
• በአደጋ ወይም ቀዶ ጥገና ምክንያት የነርቮች መጎዳት
ምንም እንኳ የወንዶች የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ችግር ብቻዉን በጤናዎ ላይ የሚያመጣዉ ጉዳት ባይኖርም/ባይጨምርም በግል በህይወትዎ ላይ የሚያጣው ከፍ ያለ እንደ
• ጭንቀትንና የትዳር/ፍቅር ግንኙነትዎን ማወክ
• የልጅ ያለመዉለድ ችግርን ሊያስከትል ይችላል፡፡

የሚደረጉ የጤና ምርመራዎች

• የጤና ባለሙያዎ ከሚጠይቅዎ የግብረ ስጋ ግንኙነት ታሪክዎ በተጨማሪ ከዚህ በፊት ስለነበርዎ የጤና ታሪክና አካላዊ ምርመራ ሊያደርግልዎ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የሽንትና የደም ምርመራና የሆርሞን ምመራዎችን ሊያደርግልዎ ይችላል
• አንዳንዴ ደግሞ ወደ የስነ አዕምሮ ስፔሻሊስት ባለሙያና ዩሮሎጂስትጋ ሊልኮት ይችላል፡፡

የወንዶች ዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ህክምና ለወንዶች የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስ ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች ብዙ ምርጫዎች ያሉት ሲሆን እነዚህም ባህሪን የመለወጥ ዘዴ፣ ቶፒካል አንስቴቲክስ፣ በአፍ የሚዋጡ መድሃኒቶችና የምክር አገልግሎትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ መገንዘብ የሚገባዎት ነገር ቢኖር የትኛዉ የህክምና ዘዴ ለእርስዎ እንደሚሰራ ለማወቅ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡

የባህሪ ዘዴ
የህክምና ባለሙያዎ በእርስዎ ላይ በግንኙነት ወቅት ያለዉን ጫና ለመቀነስ ለተወሰነ ጊዜ የግብረስጋ ግንኙነትን እንዲተዉና በሌሎች የወሲባዊ ጨዋታዎች እንዲተኩት ሊያደርጎት ይችላል

ዘ ፖዝ ስክዊዝ ቴክኒክ/ዘዴ
ይህን ዘዴ እርስዎና የትዳር/ፍቅር አጋርዎ በሚከተለዉ መንገድ ሊተገብሩት ይችላሉ፡-
1. እንደተለመደዉ የግብረ ስጋ ግንኙነትን መጀመርና የዘር ፈሳሽዎ ለመዉጣት እስከሚሰማዎ ድረስ መቀጠል
2. የዘር ፈሳሹ ሊመጣ ሲል ብልትዎን ከአጋርዎ ብልት ዉስጥ በማውጣት የትዳር/ፍቅር አጋርዎ የብልትዎ ጭንቅላትና አንጓ በሚገናኝበት ቦታ ላይ የዘር ፈሳሹ የመዉጣት ስሜት እስኪጠፋሎት ድረስና የዘር ፈሳሹ እንዳይወጣ ለተወሰነ ሰከንዶች ተጨምቆ እንድያዝልዎት ማድረግ
3. የዘር ፈሳሹ የመዉጣት ስሜት ካለፈልዎ በኃላ ለ30 ሰኮነዶች ያህል መቆየት፤ከዚያን እንደገና ለግብረስጋ ግንኙነት መሟሟቅ (foreplay)፤ብልትዎ በሚጨመቅበት ወቅት የመቆሙ ጥንካሬ ሊቀንስ ይችላል፡-ይህ ግን የግብረስጋ ግንኙነት መነቃቃት በሚፈጠርበት ጊዜ አንደገና ስለሚጠነክር ሊያሳስቦት አይገባም
4. አሁንም በድጋሚ ግንኙነትዎን ከጀመሩ በኃላ የዘር ፈሳሹ የመዉጣት ስሜት ሲሰማዎ በድጋሚ ብልትዎን ከአጋርዎ ብልት ዉስጥ በማዉጣት በድጋሚ ጨምቆ ስሜቱ እስኪያልፍ ድረስ መያዝ ይህን መንገድ በተደጋጋሚ በመሞከር በግንኙነት ወቅት ብልትዎን ወደ ትዳር/ፍቅር አጋርዎ ዉስጥ በሚያስገቡበት ወቅት የዘር ፈሰሽ በቶሎ መፍሰስን ከመከላከሉም በላይ ከተወሰኑ ልምምዶች በኃላ እንዴት የወንድ ዘር የመፍሰስን ስሜት ብልትዎን ከትዳር/ፍቅር አጋርዎ ብልት ዉስጥ አዉጥተዉና ጨምቀሁ መያዝ ሳያስፈልግዎ ማዘግየት እንደሚችሉ ልምድ እየሆነ እንዲመጣ ይረደዎታል፡፡

የምክር አገልግሎት
ይህ ቶክ ቴራፒ የሚባለዉ ሲሆን ስለራስዎ የግብረስጋ ግንኙነት ሁኔታና ልምድ ከስነአዕምሮ ባለሙያዎ ጋር የሚወዩበት ህክምና ዘዴ ነዉ፡፡ ይህ በእርስዎ ላይ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት የሚከሰተዉን ጭንቀት(ፐርፎርማንስ አንዛይቲ) ለመቀነስና ከጭንቀት ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን ችግሮች ለመቀነስ የተሻለ መንገድ እንዴት መፈለግ እንደሚችሉ ያግዞታል፡፡ ይህ የህክምና ዘዴ ከሌሎች የህክምና ዘዴዎች ጋር አብሮ ቢሰጥ የተሻለ ዉጤት ያስገኛል፡፡

መድሃኒቶች
የወንዶችን የዘር ፈሳሽ ቀድሞ መፍሰስን ችግር ሊያዘገዩ የሚችሉ የተለያዩ መድሃኒቶች ያሉ ሲሆን እነርሱም በብልት ላይ የሚቀቡና በአፍ የሚዋጡ ናቸዉ፡፡ የትኛዉ መደሃኒት ቢሰጥዎ ዉጤት እንደሚያመጣ ለማወቅ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.