የጡት ካንሰር ምልክቶች

በዳንኤል አማረ

የጡት ካንሰር ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታል፦

※ በወር አበባ ኡደት ጊዜ የሚቆይ በጡት ውስጥ፣ በጡት አካባቢ እና በብብት ስር መጠጠር ወይም አንኳር የሚመስል ምልክት
※ እንደ አተር ያነሰ እባጭ/አንኳር ነገር በጡት ላይ
※ ጡት ላይ የሚታይ የቅርፅ፣ መጠንና ይዘት ለውጥ
※ ከጡት ውስጥ የሚወጣ ደም የተቀላቀለበት ወይም ንጽህ ፈሳሽ
※ በጡት ቆዳ ላይ የሚስተዋል የእይታ ወይም የስሜት ለውጦች(ወደ ውስጥ ስርጉድ ማለት፣ መጨማደድ፣ መቅላት፣ ማበጥ)
※ የጡት ወይም የጡት ጫፍ መቅላት
※ ከሁለቱ ጡቶች መካከል በአንድ ወይም ሁለቱ ላይ ለየት ያለ እይታ ያለው ክፍል መኖር
※ በጡት ቆዳ ላይ ስንዳስሰው ጠንከር ያለ ክፍል ካለ።

እነዚህ ለውጦች ጡቶችን በማየት፣ በመዳሰስና በመነካካት በቤት ሆነን የምንለያቸው ናቸው።

መልካም ጤንነት!!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.