(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

10941313_1516444315247112_6062601849117393795_n1. ንጹህ ማር በቫይታሚን እና በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ሲሆን እነዚህ ቫይታሚኖች እና ንጥረ ነገሮችም ሰውነታችንን ከባክቴሪያዎች ይከላከላሉ፡፡

• ማር የሰውነታችንን የበሽታ መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡
• ጉንፋን ሲይዘን እና የሚያስለን ከሆነ አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር በትኩስ ውሃ ውስጥ መበጨመር አንዲሁም የተወሰነ ሎሚ እና ቀረፋ በማድረግ መጠቀም ይቻላል፡፡

2. ማርን በትኩስ ውሀ ውስጥ ከሎሚ ጋር በመጨመር ጠዋት ምግብ ከመውሰዳችን በፊት ከወሰድን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ቆሻሻን እና ቅባትን ያስወግዳል፤ የሰውነት ክብደትንም እንድንቀንስ ይረዳል፡፡

3. ማርን ከቀረፋ ጋር በመደባለቅ የምንወስድ ከሆነ የሰውነታችንን የኮሌስትሮል መጠን በ10 በመቶ መቀነስ የምንችል ሲሆን ፤ በሚገባ ከወሰድን ለልብ በሽታ ያለንን ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
• አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ ጋር በትኩስ ውሃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡

4. በሀይል ሰጪነቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ማር ከቡና ባልተናነሰ ሰውነታችን ያነቃቃል፡፡

5. ማር ለቆዳችን ልስላሴ እና ጥራት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
• ማር ባክቴርያን እና ፈንገስን መከላከል ስለሚችል ለበርካታ የቆዳ ችግሮች መፍትሄ የሚሆን የምግብ አይነት ነው፡፡
• በተጎዳው ቆዳ ላይ በመቀባት አንድ ሌሊት ማሳደር እና ጠዋት ጠዋት በንጹህ ውሃ መታጠብ ፡፡ ይህንን በተደጋጋሚ የምናደርግ ከሆነ ለስላሳ እና ንጹህ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፡፡

6. የምግብ አለመፈጨትን ይቀንሳል ፡፡
አንድ ወይም ሁለት የሾርባ ማንኪያ ማር ከበድ ያሉ ምግቦችን ከመመገባችን በፊት ብንወስድ አሊያም ምግብ ተመግበን የመክበድ ስሜት ከተሰማን በኋላ መውሰድ የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.