“የልብ ድካም”

0

የልብ ድካም ማለት በልብ የአካል ክፍል ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም አግባባዊ ያልሆነ የልብ አሰራር ለውጥ ምክንያት ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በልብ አማካኝነት የሚረጨው ደም በቂ ሳይሆን ሲቀር የሚከሰት የጤና መታወክ ነው፡፡

ሀ, የልብ ድካም ችግር እንዴት ሊከሰት ይችላል?
=============================
1ኛ. በልብ መቆጣጠሪያ ቫልቮች መጥበብና መስፋት(Chronic Rheumatic Valvular Heart Disease)
2ኛ. በልብ ደም ስሮች(Vein) መጥበብ(Coronary Artery/ Ischemic Heart Disease)
3ኛ. በልብ ጡንቻዎች ማቀፊያ መዛል(Damage of Heart Muscelse) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ልዩልዩ ዓለማቀፋዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአለም ላይ ከሚሞቱት ሰዎች መካከል 30% የሚሆኑት በልብ ችግር ነው፡፡
በሀገራችን የጥናት መረጃ መሰረት የልብ ህክምና ክትትል ካላቸው ውስጥ 40% የሚሆኑት የቫልቭ(የልብ መቆጣጠሪያ መስፋትና መጥበብ) ችግር ያለባቸው ናቸው::

ለ, የልብ ድካምን ሊያመጡ የሚችሉ ዋናዋና መንስዔዎች
====================================
❖ሲጋራ ማጨስ
❖አልኮል አብዝቶ መጠጣት
❖የደም ግፊት ችግር መኖር
❖የምግብ ጨውን አብዝቶ መጠቀም
❖በቂ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
❖ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ(ስብና ቅባታማ ምግቦችን ማዘውተር)

ሐ, የልብ ድካም ዋናዋና ምልክቶች
=====================
በቀላሉ መድከምና አቅም ማጣት
በቀላል እንቅስቃሴ እስትንፋስ ማጠርና መቆራረጥ
የምኝታ ትራስን ደራርቦ መጠቀም
አልፎ አልፎ ከፍተኛ ሳልና እራስን መሳት
የደረት ህመምና የልብ ትርታ መጨመር
የሆድ መነፋትና ማቅለሽለሽ
=>የፊትና የእግር ማበጥ

መ, አስፈላጊ የልብ ምርመራዎች
=====================
ኢሲጅ(ECG…Echo Cardio Graphy)…….የልብ ምርመራ
Chest X..Ray..የደረተ እራዥ
Echo Cardiografy …የልብ ምርመራ
ሌሎች ተጨማሪ የደም ምርመራዎች

ሰ. የልብ ድካም ህክምና
===============
★ጨው የሌለበት ምግብ መጠቀም
★ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ቶሎ መታከም
ለምሳሌ፡
ሳምባ ምች…Pneumonia
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን….Urinary Tract Infection
ደም ማነስ….Anemia
ደም ግፊት….Hypertencive
★በጤና ባለሙያ የታዘዙ አጋዥ መድሃኒቶችን በአግባቡና በሰዓቱ መጠቀም
ለምሳሌ፡
❖ላሲክስ……Lasix
❖ኢነላፕሪል……Enelaprile
❖ሜቶፕሮሎል….Metoprolol
❖ፕሮፕራኖሎል….Propranolol
❖አስፕሪን…Asprine
❖አቴኖሎል…Atenolol
❖ዲጎግሲን….Degoxine e.t.c
ልብ በሉ የመድሃኒቶቹ መጠንና አዎሳሰድ ባዘዛቸው ጤና ባለሙያ ይወሰናል፡፡

አስታውሱ ሀገር ወገንን ለመርዳትና ለመታደግ የኪስ ድቃቂ ሳንቲም ብቻ በቂ አይደለምና ሁላችንም በየመክሊታችን ለጥሩ ነገር እንትጋ ስለዚክ ይሄን ፅሁፍ *ሸር ሸር ሸር* በማድረግ ትምህርቱን ለሁሉም ወገን እናዳርስ አመሰግናለሁ፡፡
መልካምና የተሟላ ጤና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ..!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.