ውድ የሳይቴክ ወዳጆች… በአስተያየት መስጫ ሳጥን በጠየቃችሁን መሰረት ዛሬ ስለኮሌስትሮል መረጃ ይዘን መጥተናል (ሼር)

ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ ሆርሞኖችን፣ ቫይታሚን ዲ እና ሀሞትን ለማዘጋጀት ይረዳል፡፡ የሰውነታችን ነርቮችንም ይጠብቃል፡፡ እነዚህንም ለማምረት ጥቂት የኮሌስትሮል መጠን ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ይህንንም የኮሌስትሮል መጠን ጉበታችን ከሚያዘጋጀው ወይንም ከምንመገበው ምግብ ልናገኝ እንችላለን፡፡ እንደ ሥጋ፣ እንቁላልና የወተት ተዋጽኦ ከሆኑ የምግብ ዓይነቶች ኮሌስትሮል ይገኛል፡፡ አትክልት፣ ፍራፍሬና ጥራጥሬ ከኮሌስትሮል ነፃ የሆኑ ምግቦች ናቸው፡፡

በልብ በሽታ የመያዝ ዕድላችን በደማችን ካለው የኮሌስትሮል መጠን ጋር ከፍተኛ የሆነ ግንኙነት አለው፡፡ አንደኛውና ትልቁ የልብ ሕመም መንስኤ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን በደማችን ውስጥ መኖር ነው፡፡

የኮሌስትሮል /የደም ቅባት/ መጠን ማለት ምን ማለት ነው?

ዕድሜው 20 እና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ቢያንስ በአምስት ዓመት አንዴ የኮሌስትሮል መጠኑን መለካት አለበት፡፡ ይህም የደም ምርመራ የሚደረገው ምግብ ሳይወሰድ ከ9-12 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ነው፡፡

በደም ምርመራ ወቅት የሚገኙ ውጤቶች፡-

• አጠቃላይ የኮሌስትሮል መጠን ‹‹LDL (low density lipoprotenins), bad›› ኮሌስትሮል፡- ዋነኛ የኮሌስትሮል አካል ሲሆን መጠኑ ከፍ ሲል የደም ቧንቧን ይዘጋል፡፡
• ‹‹HDL (high density lipoproteins) good,›› ኮሌስትሮል፡- ኮሌስትሮል የደም ቧንቧን እንዳይዘጋ የሚረዳ ነው፤ ትራይግሊሴራድስ (Triglycerides):- በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ሌላኛው የቅባት ዓይነት ነው፡፡

ከፍተኛ የኮሌስትሮል /የደም ቅባት/ መጠን ምልክቶች

ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን የሕመም ስሜት ሆነ ምልክት የለውም፡፡ የደም ቅባት መጨመር የሚታወቀው በላብራቶሪ ምርመራ ብቻ ነው፡፡ በኮሌስትሮል መጨመር ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ ልብ ባሉ ችግሮች ወቅት በምርመራ ሊታወቅ ይችላል፡፡ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን የደም ቧንቧን በመዝጋትና የደም ዝውውርን በመቀነስ ልባችን ጥቂት ደምና አየር እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ልብን በማዳከም የልብ ጉዳት ያስከትላል፡፡

ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ለመከላከል የሚከተለውን ማድረግ ይገባል፡፡
የኮሌስትሮል መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ምግብ መመገብ፣ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የሰውነት ክብደት መቆጣጠር፣ አለማጨስ፤
የኮሌስትሮል መጠን ከዕድሜ ጋር ሊጨምር ስለሚችል የምንመገበው ምግብ እንዲሁም የሰውነት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት መስጠት ተገቢ ነው፡፡

ከፍተኛ የኮሌስትሮል /የደም ቅባት/ መድኃኒቶች

ከፍተኛ የደም ቅባት ለመቀነስ አብዛኛውን ጊዜ ስታቲኖች (Stains) የተባሉ የመድኃኒት ዓይነቶችን እንጠቀማለን፡፡ የልብ በሽታ ክስተትንም ይቀንሳሉ፡፡ የደም ቅባትን የሚቀንሱ ሌሎች መድኃኒቶችም አሉ፡፡ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን ብንጠቀምም የሰውነት እንቅስቃሴና የአመጋገብ ሥርዓት አብሮ ሊታከል ይገባል፡፡

ለወዳጆቻችሁ ሼር አድርጓቸው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.