(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

► ጥርስ

ሲጋራን ማጤስ የጥርስዎን ቀለም በቀላሉ ሊለቅ ወደማይችል ቢጫነት ወይንም ወደ ቡናማ ቀለም እንዲለወጥ ያደርጋል፡፡ የአፍዎንም ጠረን የመለወጥ ባሕርይ አለው፡፡

2000px-No_Smoking.svg► ሳንባ

ሲጋራ ማጤስ ባዘወትርን ጊዜ ሳንባችን ሊደርሰው የሚገባውን ኦክስጂን ሳያገኝ ይቀራል ለመተንፈሰም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ሲጋራን በማጤስ ምክንያት ወደ ሳንባ የሚገቡ ኬሚካሎች ሳንባን እጅግ ስለሚጎዱ ለቫይረስ እና ባክቴሪያ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም በተደጋጋሚ ለጉንፋንና ለሳል ይዳርጋሉ፡፡ የአስም ሕመምንም ይቀሰቅሳሉ፡፡

► ልብ

በሲጋራ ውስጥ የሚገኘው ኒኮቲን የደም ቧንቧን በማጥበብ የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ወደ ልብ የሚደርሰውንም ኦክስጂን የያዘ የደም መጠን እንዲቀንስ በማድረግ ለተለያዩ የአካል ክፍሎች መድረስ ያለበት የኦክስጂን መጠን ይስተጓጎላል፡፡

► አንጎል

ለአንጎል የሚደርሰው የደም ኦክሲጂን መጠን መቀነስ ለአንጎል ሕዋሶች መሞት ስለሚዳርግ ስትሮክ ለሚባል የሕመም ዓይነት በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣል፡፡

► በፅንስ ላይ የሚከሰት ችግር

ሴቶች ሲጋራን የሚያጤሱ ከሆነ በሚወልዱት ልጅ ላይ አካል ጉዳት ሊከሰት ይችላል፡፡ የልብ ችግር እና የተለያዩ ተፈጥሮአዊ የአካል ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!
ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.