የእርግዝና ክትትልና ወሊድ

የአራስ ህፃናት ሞት ቁጥር በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የኑሮ ደረጀ፣ የጤና ጥበቃ አገልግሎቶችና የህክምና እድገት በተጨማሪም ለቤተሰቦችና ልጆች የህብረተሰብ ዋስትናዎችና አንዳንድ የመኖር ዋስትና ድጋፎች ተፅኖ ያደርጋሉ። በዛሬው ጊዜ በኖርዌይ የአራስ ህፃናት ሞት ቁጥር ከሌሎች ብዙአገሮችና ከበፊቱ ጊዜ ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። እርጉዝ ሴቶች በኖርዌይ ውስጥ ነፃ የፅንስ ክትትልና የማግኘት መብት አላት። የፅንስ ክትትል የሚያደርጉትም ወይ የጤና ጣቢያዎች አልያም የግል ሀኪሞች ናቸው። ክትትሉም የሚደረገው በፍላጎት ሲሆን አላማውም የናትየውንና የፅንሱን ጤንነት በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በሗላ ለማረጋገጥ ነው። በኖርዌይ አንድ ሰው ከስምት እስከ አስራ ሁለት ጊዜ የፅንስ ክትትል እንዲያደርግ ይመከራል። ብዙዎች በሀኪም ቤቶች ሲወልዱ፣ ይህም ነፃ ነው።

ልጆችና ጤና

c9 (1)የአራስ ህፃናት ሞት ቁጥር በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የኑሮ ደረጀ፣ የጤና ጥበቃ አገልግሎቶችና የህክምና እድገት በተጨማሪም ለቤተሰቦችና ልጆች የህብረተሰብ ዋስትናዎችና አንዳንድ የመኖር ዋስትና ድጋፎች ተፅኖ ያደርጋሉ። በዛሬው ጊዜ በኖርዌይ የአራስ ህፃናት ሞት ቁጥር ከሌሎች ብዙአገሮችና ከበፊቱ ጊዜ ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። እርጉዝ ሴቶች በኖርዌይ ውስጥ ነፃ የፅንስ ክትትልና የማግኘት መብት አላት። የፅንስ ክትትል የሚያደርጉትም ወይ የጤና ጣቢያዎች አልያም የግል ሀኪሞች ናቸው። ክትትሉም የሚደረገው በፍላጎት ሲሆን አላማውም የናትየውንና የፅንሱን ጤንነት በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በሗላ ለማረጋገጥ ነው። በኖርዌይ አንድ ሰው ከስምት እስከ አስራ ሁለት ጊዜ የፅንስ ክትትል እንዲያደርግ ይመከራል። ብዙዎች በሀኪም ቤቶች ሲወልዱ፣ ይህም ነፃ ነው።

ሁሉም ህፃናትና ወጣት ልጆች በኖርዌይ የሚኖሩ በየጊዜው የጤና ቁጥጥር የማግኘት እድል ያገኛሉ። ልጆች ከአራስነታቸው እስከ ትምህርት ሲጀምሩ ይህ የጤና ቁጥጥር በጤና ጣቢያዎች ይካሄዳል። ልጆች ትምህረት ከጀመሩ በሗላ ክትትሉን የሚያደርግላቸው የትምህርት ቤቱ የጤና አገልግሎት ሰጪ ክፍል ነው።በተጨማሪም በሁሉም ወረዳ የወጣት ልጆች ጤና ጣቢያዎች ይገኛሉ። በጤና ጣቢያዎችና በትምህርት ቤት የጤና አገልግሎት ሰጪ ክፍል የሚሰጡ አገልግሎቶቸ ነፃ ናቸው።

በጤና ጣቢያዎችና ሰዎች የልጆችን እድገት ማለትም እያደጉ ያሉት እንደተለመደው ማደግ እንዳለባቸው፣ አይናቸውና ጆሮአቸው በትክክል መስራቱንና ህፃኑም መረዳትና መናገር መማሩን ይቆጣጠራሉ። በህፃኑ እድገት ላይም ችግር ካለ ጤና ጣቢያው እርዳታና ምክር እንዲያገኙ ያመቻቻል።
ሁሉም ህፃናትና ወጣት ልጆች በኖርዌይ የሚኖሩ ለአደገኛ በሽታዎች የሚሰጡ ክትባቶችንም የማግኘት እድል አላቸው። ክትባቶቹም በቀላል፣ ውጤታማና አደገኛ ባልሆነ መልኩ በሽታዎቹን ይከላከላል። ክትባት መወሰድ በበጎ ፍቃደኝነት ሲሆን መንግስትም ግን ቤተሰቦች ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ በጥብቅ ይመክራል።
በክትባት እቅዶች ውሰጥ ያሉ ክትባቶች ነፃ ናቸው። ተጨማሪ ክትባቶች ለምሳሌ ወደ ውጭ አገር ሲጓዙ ለሚወስዱት ክትባቶቸ እራስዎ መክፈል አለብዎት።

Source: Samfunnskunnskap

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.