ለቆዳ ውበትና ጤንነት ተመራጭ የሆኑ 11 ምግቦችን ያውቋቸዋል?

3

የተተርጉሞው፦ በሳሙኤል ዳኛቸው

1. እስፒናች
key sirእስፒናች ቆስጣ መሰል ቅጠል ያለው የአትክልት ዘር ሲሆን፥ ቅጠሎቹ ከቆስጣ አነስ ይላሉ፡፡ እስፒናች በዋነንነት በውሰጡ የቫይታሚን ኤ (ቤታ ካሮቲን) እና ሲ ክምችት ያለው ሲሆን እነዚህ ሁለቱም ዓይነት ቫይታሚኖች የአንቲኦክሲዳንት አይነት ባህሪ ስላላቸው ቆዳችንንም ሆነ ሰውነታችንን በአጠቃላይ ከጉዳት ይከላከላሉ፡፡ ከማዕድናት ደግሞ ማግኒዥያም፣ ሴሌኒየም፣ እና ዚንክን ይዟል፡፡ እነዚህ ማዕድናቶች ደግሞ ለቆዳ መወጠር፣ ለደም ዝውውር፣ ለቆዳ ወዝ ቁጥጥር ወዘተ ትልቅ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡

2. አቮካዶ
አቮካዶን በሚመለከት ብዙ ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፡፡ ይኸውም አቮካዶ ቅባትነት ስላለው ለጤና ጥሩ አይደለም ብለው ያስባሉ? ነገር ግን ይህ ስህተት ነው፡፡ ሁሉም የቅባት አይነቶች ለጤና ጥሩ አይደሉም የሚል ካለ ይህም ስህተት ነው፡፡
ለጤና ከመስማማት አልፈው መድሃኒት የሚሆኑ በተፈጥሮ የሚገኙ የቅባት አይነቶች እንዲሁም ለጤና የሚስማሙ የቅባት አይነቶች አሉ፡፡ ለጤና ከሚስማሙ የቅባት አይነቶች ውስጥ የሚገኙ ለጤና በጣም ተስማሚ የሆኑ ፋቲ አሲዶች ቆዳን የማለስለስ፣ የማጥራት እና ሙሉ የማድረግ ችሎታ አላቸው፡፡

3. የስጎ ቅጠል(ፓርስሊ)
የስቆ ቅጠል ወይም ፓርስሊ በውስጡ በጣም ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል፡፡ የቫይታሚን ሲ ይዘቱ በተለይ ከፍተኛ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በውስጡ የያዘው ጠቃሚ ዘይት በባህሪው የማሸናት ችሎታ ስላለው ይህ ደግሞ በውሃ ውስጥ የሚሟሙ ቆሻሻዎች እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡ የኩላሊት ስራንም ቀልጣፋ ማድረግ የሚችል ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች እንደ ሊቲዮለን የመሳሰሉ የአንታይኦክሲዳንት አይነቶችን በውስጡ ይዟል፡፡

4. ሽንኩርት (ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባሮ)
ሽንኩርቶች አንድ የጋራ የሆነ የማዕድን ይዘት አላቸው፡፡ እርሱም ሰልፈር ነው፡፡ ሰልፈር የተባለው ማዕድን ደግሞ ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና እንዲወጠር የሚያደርጉትን ኮላጅንን እና የቆዳችን መዋቅር የተሰራበት ክፍልን ለመስራት የሚያገለግል ነው፡፡ ስለዚህ በቂ የሆነ ኮላጅንና ይህ መሰል መዋቅር መመረት ከቻለ እና በጥሩ ሁኔታ ካለ ቆዳችን ውጥር ያለና ውብ ይሆናል፡፡

5.ቲማቲም
ቲማቲም የተለያዩ አንቲኦክሲዳት አይነቶችን ለምሳሌ ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አጭቆ ይዞ ሊፈነዳ የደረሰ የምግብ አይነት ነው፡፡ ስለዚህ ቲማቲም ህዋሶቻችንን ከፍሪ ራዲካል ጥቃት ሊታደግ የሚችል በቀላሉ የሚገኝ አትክልት ነው፡፡ በመሆኑም ቲማቲም ባለው አንታይኦክሲዳንት ብዛት እና አይነት ሳቢያ የቆዳን እርጅና ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮላጂንን ጥንካሬ እና የመለጠጥ ችሎታ የመጨመር ኃይል ስላለው የቆዳ መሸብሸብን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡

6. ቀይ ስር
ቀይ ስር በውስጡ ቤታ ሳያኒን የተባለ ቅመም የያዘ ሲሆን፥ ይህ ቅመም ለቀይ ስር ደማቅ ሀምራዊ ቀለም መያዝ ምክንያትም ነው፡፡ ይህ የአትክልት አይነት በዋነኛነት ከሚያከናውናቸው ስራዎች ውስጥ የጉበትን ቆሻሻ የማስወገድ ሥራ ማገዝ ነው፡፡ ይህም ማለት በሰውነት ውስጥ የሚገኙ መርዛማ የሆኑ ቆሻሻዎችን በመሰባበር ከሰውነት እንዲወገዱ ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዚያክሳቲን የተባለ አንታይኦክሲዳንት በመያዙ ቆዳ ቶሎ እንዳይሸበሸብ፣ ውብ እና ብሩህ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

7. ስኳር ድንች
ስኳር ድንች በውስጡ ቆዳ አፍቃሪ የሆነውን የአንቲኦክሲዳንት አይነት ቤታ ካሮቲንን በብዛት የያዘ ነው፡፡ ቤታ ካሮቲን ደግሞ በተደጋጋሚ በብዛት እንደተመለከትነው በቆዳችን ስባማ ክፍል ውስጥ በመጠራቀም የቆዳችንን ኮላጂንን እና ኢላስቲን የተባሉ ቆዳን የመለጠጥ እና የመወጣር ባህሪን የሚያላብሱ ክፍሎችን ከፍሪ ራዲካሎች ጥቃት ይከላከላል፡፡ በዚህም ሳቢያ ቆዳ ቶሎ እንዳይሸበሸብ እና እንዳያረጅ ያግዛል፡፡ ሌላው ቤታ ካሮቲን በ”አንቲ ኢንፍላማቶሪ” ባህሪው ምክንያት የቆዳን መቅላት፣ ማበጥ እና ህመም የማከም ችሎታ አለው፡፡

8. አጃ
አጃ የቫይታሚን ቢ ቤተሰቦችን አሰባስቦ የያዘ የምግብ አይነት ነው፡፡ የቫይታሚን ቢ አይነቶችን ሰብስቦ መያዙ በቆዳ ውስጥ ለሚከናወኑ ሥራዎች ለምሳሌ፣ ለቀልጣፋ የደም ዝውውር፣ ለቆዳ ውበት እና ለቁስል መዳን እንዲሁም የወዝ መጠን ቁጥጥር ወዘተ በተጠናከረ መልኩ እንዲከናወን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ምግብ የቫይታሚን ቢ አይነቶችን በውስጡ ከያዘ ቆዳ በተሟላ ሁኔታ ስራውን እንዲያከናውን፣ ውብ እና ጤናማ እንዲሆን ይረዳል፡፡

9. ተልባ
ተልባ ኦሜጋ ስሪ ፋቲ አሲድ በውስጡ የያዘ በመሆኑ ቆዳን የማለስለስ፣ የቆዳ መቅላትና ማበጥ እንዲሁም ህመምን መከላከል የሚችል ምን አለፋችሁ ሁለገብ የምግብ አይነት ነው፡፡
ስለዚህ ተልባን በምግባችን ውስጥ አካተን መመገብ ስንጀምርና ስናዘወትር ወዙ የሚያምር፣ ለስላሳ እና ሙሉ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳናል፡፡

10. የዱባ ፍሬ
የዱባ ፍሬ ለቆዳ ጤንነት እና ውበት ከሚጠቅሙ ማዕድናት ውስጥ ዚንክን የያዘ ሲሆን የበሽታ መከላል አቅምን ከፍ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም እንደ ብጉርና በኢንፌክሽን አማካኝነት የሚፈጠሩ የቆዳ ችግሮችን ይዋጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኦሜጋ 3 እና 6 ፋታ አሲድን በውስጡ ይይዛል፡፡

11. ሽንብራ
ሽንብራ በውስጡ ዚንክ የሚባል ንጥረ ነገር የያዘ ሲሆን የቆዳን ወዝ መጠን ለመቆጣጠር እና ሚዛኑን እንዲጠብቅ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ዚንክ የቆዳ ወዝ ሲበዛም ሆነ ሲያንስ ሚዛኑን የጠበቀ የወዝ መጠን የወዝ ዕጢዎች እንዲያመነጩ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡

ሌላው በሽንብራ ውስጥ የሚገኝ ጠቃሚ ነገር ደግሞ ፋይበር ነው፡፡ ፋይበር ደግሞ እንደሚታወቀው አንጀትን ለማፅዳት ይጠቅማል፡፡ ይህም ማለት የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ቆሻሻ ቶሎ ቶሎ እንዲወገድ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ቆሻሻ በአንጀት ውስጥ በቆየ ቁጥር እነዚህ መርዞች በደም ስር ውስጥ ተመልሰው ሰርገው በመግባት ወደ ሰውነታችን ይሰራጫሉ፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት ደግሞ ጤንነታችንን ከማወኩ በተጨማሪ ቆዳችንን ህይወት የሌለው እና አመዳም፣ ድካም የተላበሰ አይነት ፊት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

ምንጭ፦ http://www.zehabesha.com

3 COMMENTS

  1. hay endet nachehu programachu betam arif new
    ene metyek yemfelgew sele goiter ( enkert) new
    lemehonu beshetaw yale kedo tegena medan yechel yehon?
    kadege behulas beshetawen lematfat madreg yaleben neger mendnew?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.