ጤናማ ጥርስ ከፈለጉ አንዳንድ ምግቦችን መመገብ እንደሌለቦዎት ሰምተው ሊሆን ይችላል፡፡

በዚህም ጨውና ስኳር ለጥርስ መቦርቦር ምክንያት በመሆናቸው ሰዎች እንዳያዘውትሯቸው በጥርስ ህክምና ባለሙያዎች  ይመከራል።

በዛሬው የጤና አምድ ለጥርስ  ጤና መልካም የሆኑ ስድስት ምግቦችን እንመለከታለን።

ወተት

ወተት በካልሺየምና በሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ስለሆነ ለጤናማ ጥርስ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም በአፍ ውስጥ ያለውን የአሲድ ደረጃ የሚቀንስ በመሆኑ የጥርስ መበላትን ይከላከላል፡፡

በመሆኑም ወተትን መጠቀም የጥርስ ጤናን ለመጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ ወተትን  ማዘውተር ይመከራል።

አሳ

አሳ ቫይታሚንና ሌሎችን ማዕድናት በውስጡ የያዘ በመሆኑ ለጤና  ጠቃሚ ነው፡፡ በአሳ ውስጥ ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ስለሚገኙበት እንዲጠቀሙ ይበረታታል፡፡

የስጋ አይነቶች  ለአፍ ጤና መልካም እንደሆኑ ይነገራል ፤ አሳ በተለየ  የተሻለ ጠቀሜታ አለው፡፡

ትኩስ ፍራፍሬ

ትኩስ ፍራፍሬ አብዝቶ መመገብ ለጥርስ ጠቃሚ ነው፡፡ በሲትሪክ አሲድ የበለፀጉትን አለመመገብ ቢኖርብዎትም የብርቱካን የአሲዱ መጠን ዝቅተኛ  በመሆኑ ከሌሎች በተሻለ መጠቀሙ መልካም ነው።

ጥርስን ለማንጣት የሚረዳ ስትሮቤሪ እና አፕል የመሳሰሉትን  መመገብ ጠቃሚ ነው፡፡

እርጎ

እርጎ ፣ ከድድና መንጋጋ በሽታ የሚከላከሉ  ካልሺየምና ፕሮባዮቲክስ ስላለው ለአፍ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡ ስለዚህ በየቀኑ እርጎን  ከገበታ አለመለየት ይመከራል።

ነጭ ሽንኩርት

ነጭ ሽንኩርት ለአፍ ጤና ጠቃሚ ከሆኑ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ነጭ ሽንኩርት በውስጡ ባለው አሊሲን ንጥረ ነገር በአፍ ውስጥ ያለን ባክቴሪያ ይገድላል።

እነዚህ ባክቴሪያዎች አብዛኛውን ጊዜ የጥርስ መበላትና የአፍ በሽታ የሚያስከትሉ ናቸው፡፡

ሽንኩርት

ሽንኩርትም በአፍ ውስጥ ያሉ በሽታ አምጪ ባክቴሪያዎችን  ይከላከላል። ለዚህም  ሽንኩርት ጥሬውን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

መሰረታዊ ጉዳይ

ለጥርስ ጤና  የአፍ ንፅህና አጠባበቅ ልምምድ ማዳበር እና የተጠቀሱትን  ምግቦች መመገብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ካልሆነ የጥርስ  እንደ ብሬስ፣ ጥርስ ተከላ እና ሌላም ከፍ ያለ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here