የጥቁር ሻይ የጤና በረከቶች!

2

1922250_710033722420703_4143346665940057258_nበየእለት ኑሯችን ከቤታችን የማይጠፋው ሻይ ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል። ይኸው ጥቁር ሻይ ከቻይናውያኑ ቢጫ ሻይ እና አረንጓዴ ሻይ የተለየ ጣዕምና የጤና በረከቶች አሉት። ጥቁር ሻይ፦

1. የመስማት ችግርን ለመፍታትና ፓርኪንሰን የተባለውን በሽታ ለመከላከል ፈዋሽ ነው።

2. በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያሳድጋል ጥቁር ሻይ አልካላሚን የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ ስለሚይዝ በቀላሉ ሊያጠቁን ከሚችሉ እንደ ጉንፋን ካሉት በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል።

3. ጭንቀትን ያቃልላል ጥቁር ሻይ በውስጡ በያዘው ኤል ቲያናይን የተባለ ውህድ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ የጭንቀት ሆርሞኖችን ቁጥር ይቀንሳል። በዚህም ዘና እንድንልና የማስተዋል አቅማችን እንዲጎለብት ያስችላል።

4. የምግብ ውህደትን ያፋጥናል

5. የአፍ ውስጥ በሽታዎችን ይከላከላል ጥቁር ሻይ በተለይም የጥርሳችንን ጤና በመጠበቅ ረገድ አይነተኛ ሚና እንዳለው ነው የሚነገረው። በጥቁር ሻይ ውስጥ የምናገኘው ፖሊፔኖለስ ጎጂ ባክቴሪያዎችን በመግደል ጥርሳችን ጤነኛ እንዲሆን ይረዳል።

6. የልብ ጤናን ይጠብቃል

7. ጉልበት ይሰጣል ጥቁር ሻይ ወደ አዕምሯችን የሚሄደውን የደም ዝውውር እንዲፋጠን በማድረግ የተነቃቃ ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል።

8. ካንሰርን ይከላከላል በጥቁር ሻይ ውስጥ የምናገኘው ቲኤፍ 2 የተባለ ውህድ የካንሰር ህዋሳቶችን ይገድላል።

9. ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል

10. የኮሊስትሮል መጠን ይቀንሳል በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚነገርለትን ጥቁር ሻይን ለማጣፈጥ ሲባል ብዙ ስኳርን ከመጠቀም ማርን በአማራጭነት መጠቀም እንደሚገባ ይመከራል።

ምንጭ፦homeremedy.com

2 COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.