(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የፕሮስቴት ዕጢ ከወንዶች የሥነ ተዋልዶ አካላት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ዕጢ የሚገኘው ከሽንት ፊኛ በታች ሲሆን የሽንት ቱቦ መሃከለኛ ክፍልን ዙሪያ ከቦ ይገኛል፡፡

New-Picture-622x330ይህ የፕሮስቴት ዕጢ ለወንድ ዘር ፈሳሽ የሚሆነውን ፈሳሽ ከሚያመነጩ
የሰውነት አካል ውስጥ አንዱ ሲሆን ዕድሜ በገፋ ቁጥር መጠኑም አብሮ ይጨምራል፡፡

✔ የፕሮስቴት ዕጢ መጠን መጨመር ምክንያቶች፡-
– የካንሰር ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት ዕጢ እድገት
– የፕሮስቴት ካንሰር

✔ የካንሰር ጠባይ የሌለው የፕሮስቴት ዕጢ ዕድገት

ከዕድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሲሆን የፕሮስቴት ዕጢ ከሚገባው በላይ የሚያድግበት መሠረታዊ ምክንያት ባይታወቅም የሆርሞን መለዋወጥ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

የፕሮስቴት ዕጢ በሽንት ቱቦ ዙሪያ ስለሚገኝ መጠኑ በጨመረ ቁጥር የሽንት የማጥበብ ሁኔታን ሊያስከትል ይችላል፡፡

✔ የፕሮስቴት ዕጢ ዕድገት ምልክቶች
• ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና፣
• በአንድ አንድ ሁኔታ ሽንት ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ መፍሰስ፣
• ሸንተው ከጨረሱ በኋላ ሽንት ጨርሶ ያልወጣ መስሎ መሰማት፣
• ሽንት ሸንተው ከጨረሱ በኋላ ማንጠባጠብ፣
• በሌሊት በተደጋጋሚ ከእንቅልፍ ለሽንት መነሳት፣
• ሽንት በሚሸኑበት ወቅት የፍሰቱ መጠን መቀነስ፣መቆራረጥና እንዲሁም ለመሽናት ማስማጥ፣
• ደም የቀላቀለ ሽንት መኖር፣
• የሽንት ቱቦ ሙሉ በሙሉ ከተዘጋ በታችኛው የሆድ ክፍል ከፍተኛ የህመም ስሜት መሰማት፣

✔ የፕሮስቴት ካንሰር

የፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ የሚታይ የህመም ሁኔታ ሲሆን መንስዔው በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡ የፕሮስቴት ካንሰር ቀስ በቀስ የሚያድግና የሚሠራጭ ስለሆነ አስከፊ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምንም ዓይነት የህመም ስሜት ላያስከትል ይችላል፡፡

✔ የፕሮስቴት ካንሰር ምልክቶች

የፕሮቴስት ካንሰር ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሊኖሩት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን መሰራጨት ከጀመረ በኋላ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሕመም ስሜቶችን ያስከትላል ወደ ጀርባና የጎን አጥንት፣ኩላሊት አና አንጎልም ይሰራጫል፡፡

እርስዎ ከላይ የተጠቀሱት የህመም ስሜቶች የሚኖሩት ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርቦታል፡፡

የህክምናዉ ሁኔታም እንደ ምርመራዉ ዉጤት የሚለያይ ሲሆን የተጠቀሱ ስሜቶች የሌላ ሕመም መገለጫ ሊሆኑ ስለሚችሉ ተገቢዉን ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.