(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የጆሮ ኢንፌክሽን በባክቴሪያ ወይንም በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ችግር ሲሆን ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህመሙ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡

ear-660x330በአብዛኛው ከጉንፋን በኋላ የሚመጣ ችግር ሲሆን ምክንያቱም የመካከለኛው የጆሮ ክፍል ከኋለኛው የአፍንጫ ክፍል ጋር በቱቦ የተያያዘ ስለሆነ ነዉ፡፡

✔ የጆሮ የኢንፌክሽን ምልክቶች
• የጆሮ ሕመም
• የጆሮ መደፈን ስሜት
• የራስ ምታት
• ከጆሮ የሚወጣ ፈሳሽ
• ጆሮ ውስጥ የሚጮህ ስሜት
• የመስማት ብቃት መቀነስ እና ማቆም
• አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ደግሞ በእጃቸው ወደ ጆሮ አካባቢ በተደጋጋሚ ይነካካሉ
• መቅለሽለሽ እና ማስመለስ
• ማስቀመጥ
• ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት መጠን መጨመር

✔ ከዚህም በተጨማሪ
• በጆሮ አካባቢ ያለው አጥንት ኢንፌክሽን መፈጠር
• የአንጎል ሽፋን የሆነው የመነንጂስ ኢንፌክሽንም ያስከትላል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ከተከሰቱ ወደ ህክምና ማዕከል በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

✔ የጆሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል
• ጡት ማጥባት
• ጡጦ በጀርባ አስተኝቶ አለማጥባት
• ክትባቶችን ማስከተብ
• እጅን በሚገባ መታጠብ
• ልጅዎ ባለበት አካባቢ ሲጋራን አለማጤስ ናቸዉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.