(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

women-640x330

የሴት እንቁላሎች በሚያልቁበት ጊዜ እና የወር አበባ በሚቆምበትም ወቅት ማረጥ ተከሰተ ይባላል፡፡

በሴት ማኅፀን ውስጥ የሚገኘው የእንቁላል ብዛት ዕድሜ በጨመረ ቁጥር በየወሩ ከማቀፊው በመውጣት የወር አበባን በማስከትል ቁጥሩ እየቀነሰ ይሄዳል አንዳንዶቹ እንቁላሎች ደግሞ በራሳቸው እየሟሸሹ ይጠፋሉ፡፡ከ40 – 60 የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ የሚከሰትም ነዉ፡፡

አንዲት ሴት አረጠች ብለን መደምደም እንደንችል ቢያንስ ለ12 ተከታታይ ወራት የወር አበባ መቅረት እና ከዚህም በተጨማሪ ተጓዳኝ የማረጥ ምልክቶች እና ሁኔታዎች መታየት ይኖርባቸዋል፡፡

ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች የሚታዩ ሲሆን
• የወር አበባ መዛባት
• ከፍተኛ ሙቀት መሰማት
• በላብ መጠመቅ
• የእንቅልፍ መዛባት
• መናደድ እና ስሜታዊነት
• የሰዉነት ክብደት መጨመር
• ራስን መሳት
• በጆሮ ዉስጥ የሚጮህ ድምጽ መሰማት
• ማቅለሽለስ እና ማስመለስ
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ማስቀመጥ
• ቁርጥማት
• የድካም ስሜት መሰማት
• የራስ ምታት
• የሰውንት ክፍልች መደንዘዝ
• የአጥንት መሳሳት
• የወር አበባ መዛባት፤ቀስ በቀስ መቀነስ ወይንም በአንድ ጊዜ መቆም
• የጡት መጠን መቀነስና የሕመም ስሜት መሰማት
• ከፍተኛ እና ድንገተኛ የሙቀት ስሜት መሰማት ናቸዉ፡፡

ማረጥ የተፈጥሮ ሂደት ሲሆን ያረጡ ሴቶች መንፈሳቸዉን ማዝናናት፤አመጋገባቸዉን ማስተካከል፤ወተት መጠጣትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

ምልክቶቹ የዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታን የሚረብሹ ከሆኑ ሀኪምዎን በማማከር የህክምና እርዳታን ማግኘትም ይችላሉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.