ውሃ ያድናል፤ ውሃ ይገድላል

0

de8f352d9f6cce88542bceb7e04d356f_XLውሃን መጠጣት የምግብ ስልቀጣ ሂደትን ለማፋጠንና የሰመረ ለማድረግ እንዲሁም  ቆዳን ለማጥራት፣ ድካምን ለማብረድና ትኩረት የመስጠት ችሎታን ለመጨመር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከልክ ሲያልፍ ለሞት እንደሚዳርግ የእንግሊዝ ተመራማሪዎች በቅርቡ ይፋ ያደረጉት መረጃ አመልክቷል፡፡

ከመጠን ያለፈ ውሃ መጠጣት የኩላሊትን የማጣራት ተግባር እንደሚያውክና ደማችንን በማቅጠን የሰውነታችንን የጨው ክምችት ቀንሶ ለሞት እንደሚዳርግ የጠቆመው መረጃው፤ የውሃው መጠን እጅግ ሲበዛ የአዕምሮአችን የውስጠኛው ክፍል እንዲያብጥና የአዕምሮ ስራ እንዲስተጓጎል ያደርጋል ብሏል፡፡ የደም ዝውውራችንንና ትንፋሻችንን የሚቆጣጠረው የአዕምሮአችን ክፍል በእብጠቱ ሳቢያ በሚደርስበት ጉዳት ስራው ሲስተጓጎል በትንፋሽ እጥረትና በደም ዝውውር መዛባት ምክንያት ለህልፈት ልናደርግ እንደምንችል መረጃው አመልክቷል፡፡

አንድ ሰው በየሁለት ሰዓቱ ከአንድ ጊዜ በላይ ሽንቱን ለመሽናት ወደመፀዳጃ ቤት ከተመላለሰና የሽንቱ ቀለም ንፁህ ውሃ የሚመስል ከሆነ፣ የጠጣው ውሃ ከመጠን ማለፉን እንደሚያመለክትም ተማራማሪዎቹ ይፋ ያደረጉት መረጃ ይጠቁማል፡፡

ምንጭ – አዲስ አድማስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.