የፀጉር ሽበት እንዴት ይከሰታል?

ዳንኤል አማረ

Africans-168ሽበት በእድሜያቸው የገፉ ወይም ያረጅ ሰዎች ላይ መመልከት የተለመደ ሲሆን በፊት ሰምተነው በማናውቀው ሁኔታ በወጣቶችም ላይ መከሰት/መታየት የተለመደ እየሆነ ነው ይህም የሚከሰተው በተፈጥሮ ፀጉር ጥቁር ቀለም እንዲኖረው የሚያደርጉት ሴሎች መመረት ሲያቆሙ ወይም ሲቀንሱ ነው።

የሽበት መንስኤዎች

ዘረመል/የዘር ሀረግ፣ሲጋራ ማጨስና የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ በወጣትነት ፀጉራችን ነጭ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽዎ ያደርጋሉ።
ዘረመል ወይም የዘር ሀረግ ለፀጉር ነጭ መሆን የመጀመሪያውን ድርሻ ይወስዳል ይህም ከወላጆች የዘር ሀረግ ወደ ልጆች በቀላሉ ይዛመታል ማለት ነው። የቫይታሚንና ሜኔራሎች በተለይም ቫይታሚን ቢ12፣ ኮፐር(copper) እና ዚንክ(zinc) እጥረት የአንድን ሰው የፀጉር ቀለም ይቀይራሉ። የቫይታሚን ሲ እና ኢ እጥረት ፀጉራችን በአፋጣኝ ነጭ እንዲሆን የደርጋል።
ሲጋራ ማጨስ በሰውነታችን ውስጥ ፍሪ ራዲካልስ(free radicals) እንዲፈጠሩ በማድረግ ጥቁር ፀጉር እንዲኖረን የሚያደርገውን ሜላኒን(melanin) የተባለውን ኬሚካል ስራ ያስተጓጉላል ወይም ይቀንሳል። ቶሎ የሚዘጋጅ(fast foods) ምግቦች በሰውነታችን ውስጥ የኦክስጂን ውጥረት በመፍጠር ቶሎ እንድናረጅና ፀጉራችን የተፈጥሮ ቀለሙን እንዲያጣ ያደርጋሉ።

እንዴት ልንከላከለው እንችላለን

ሽበትን ለመከላከል አንድ ሰው ማድረግ ያለበት
– ለቀጥታ የፀሀይ ብርሀን/ጨረር አለመጋለጥ
– ኒኮቲናማይድ(Nicotinamide) መጠቀም
– ዚንክ እና ኮፐር መጠቀም
– ቅጠላ ቅጠሎች የሆኑ አትክልቶችን መጠቀም
– ከስጋ አትክልትና ሩዝ በመቀላቀል የተዘጋጅ ምግቦች የሜላኒን መመረትን ስለሚጨምሩ ይጠቀሟቸው
– የባህር ውስጥ ምግቦች በዚንክ እና ኮፐር የበለፀጉ ስለሆኑ እነሱን መጠቀም
በመጨረሻም ማንኛውንም መከላከያ መንገዶች ተጠቅመን ሽበት ቢከሰትም ሽበት ተፈጥሮአዊ ክስተት መሆኑን አውቀን በፀጋ ልንቀበለው ይገባል።

ጤና ይስጥልኝ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.