የዓለም የጤና ድርጅት የስኳር ህመም ቆሽት የተሰኘዉ የዉስጥ አካል ኢንሱሊን የተባለዉን ተፈላጊ ቅመም በበቂ ማምረት ሲሳነዉ ወይም፤ ቆሽት ያመረተዉን ኢንሱሊን ሰዉነት በአግባቡ መጠቀም ሲያቅተዉ ሊከሰት እንደሚችል ያመለክታል።

 እንዲህ ያለዉ እክል ሰዉነትን ሲያጋጥም ደግሞ ደም ዉስጥ በርከት ያለ የስኳር ፈሳሽ/ግሉኮስ/ ይከማቻል። ይህ የመጀመሪያዉ ዓይነት የስኳር ህመም ሲሆን፤ ሁለተኛዉ ዓይነት ደግሞ፤ በተመሳሳይ ሰዉነት ተገቢ ያልሆነ የኢንሱሊን አጠቃቀም ሲኖረዉ የሚከሰት ሆኖ፤ መጠን ያጣ ክብደት ሲኖርና በአግባቡ የሰዉነት እንቅንቃሴ ባለመደረጉ እንደሚከሰት መረጃዉ ያብራራል። የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማኅበር ፕሬዝደንትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ሃኪም ቤት በተለይ የስኳር ህመምን የሚከታተሉት ባለሙያ ዲክተር አህመድ ረጃ ይህ የጤና እክል የእድሜ ዘመን ህመም መሆኑን ያመለክታሉ። የስኳር በሽታ ታማሚዎች ቁጥር ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየጨመረ እንደሚገኝ ጥናቶች እያመለከቱ ነዉ። እንዲያም ሆኖ ጥናቱ እንደሚለዉ የህመሙ ተጠቂ ከሆኑ ግማሽ ያህሉ ገና ተገቢዉን ምርመራ አላደረጉም።

የሰዉነት ክብደትን መቆጣጠር

ከአንድ ዓመት በፊት 366 ሚሊዮን የነበረዉ በዓለማችን የስኳር በሽታ ታማሚዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 371 ሚሊዮን መድረሱን በቅርቡ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ዓለም ዓቀፍ የስኳር ህመም ፌዴሬሽን እንደሚለዉም ከሆነም በጎርጎሮሳዊዉ 2030ዓ,ም ቁጥሩ ወደ552 ሚሊዮን ማሻቀቡ አይቀርም። ቻይና ዉስጥ ብቻ 92,3 ሚሊዮን ህዝብ ለዚህ የጤና ችግር ሲጋለጥ የጤና አገልግሎቱ ባልተስፋፋበት በአፍሪቃም እንዲሁ ቁጥሩ ሊበረክት እንደሚችል ይገመታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.