‹‹ባለቤቴን እጅግ እወደዋለሁ፡፡ አሁን ላይ ለእርሱ ያለኝ ስሜት ከ7 ዓመት በፊት ከነበረኝ ስሜት ጋር ሲነፃፀር ቢጨምር እንጂ ቅንጣት ያህል አልቀነሰም›› የሁለት ልጆቼ አባት የሆነው ባለቤቴ የወሲብ ቪዲዮዎችን እና ምስሎችን በስልኩ አማካኝነት ዘወትር እንደሚመለከት ደርሼበታለሁ፡፡ በእጅጉ ተቀይሮብኛል ወሲባዊ ግንኙነት እንደማልፈልግ ስነግረው ምንም ሳያነጋግረኝ እሺታውን ይሰጠኛል፡፡ ነገር ግን ለወትሮው እኔ እስክስማማ ድረስ እጅግ ይጎተጉተኝ ነበር፡፡ ያ ነገር አሁን የለም፡፡ ስልኩን ልጠቀምበት እንዲሰጠኝ ስጠይቀው ፈቃደኛ አይደለም፡፡ በአንድ አጋጣሚ እጄ ላይ ሲገባ በስልኩ ውስጥ በርካታ የወሲብ ፊልሞች እንደጫነ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ በአካባቢያችን በሚገኝ የኢንተርኔት ካፌ ውስጥ እስከ ምሽቱ 4 እና 5 ሰዓት ድረስ ቆይቶ ይመጣል፡፡ ባህሪውን (ማምሸቱን እና እኔን ትኩረት መንፈጉ) እንዲያስተካክል ብነግረውም ወደምጠላው ግጭት ከመግባት የዘለለ ውጤት ማምጣት አልቻልኩም፡፡ ባለቤቴ ለእኔ ያለው ፍቅር በፍፁም ቀንሷል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከእኔ ጋር ለመሆን ከቤተሰቦቹ ጭምር ለመለያየት ወደ ኋላ ያላለ ጀግናዬ ነው፡፡ ነገር ግን በይፋ እንኳን ለመወያየት ሞራሌ ከማይፈቅደው ድርጊት እንዴት ላወጣው እችል ይሆን? ስል ራሴን እጠይቃለሁ፡፡

በሌላ መልኩ ወጣትነቴ በማፈልገው መስመር እንዲያልፍ ምክንያት የሆነኝን የወሲብ ቪዲዮ እና የባለቤቴ ባህሪ የበታችነት እና የመከዳት ስሜት ውስጥ እንደከተተኝ ሳስብ ስለዚህ ግንኙነት ቆም ብዬ እንዳስብ እገደዳለሁ፡፡ ለማንም ያላዋየሁትንና ምክር እጠይቅበት ዘንድ ድፍረት ያሳጣኝ የባለቤቴ ልማድ ወደማልፈልገው ፍቺ እየመራኝ ነው››
ወ/ሮ ስሜ አይጠቀስ

መልስ፡-
በ2014 (እ.ኤ.አ) ትኩረቱን በመላው ዓለም ያደረገ ጥናት በእንግሊዛውያን የጥናት ባለሙያዎች ተደርጎ ነበር፡፡ በርካታ ወንድ እና ሴት በጎ ፈቃደኞችን ያሰባሰበው ፕሮጀክት ‹‹Sex›› የሚለው ቃል በስፋት በኢንተርኔት የሚፈለግ ቃል መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የቅርቡ የአሜሪካውያን ጥናት ደግሞ 68 ፐርሰንት የሚሆኑት ጎረምሶች እና 18 ፐርሰንት የሚገመቱት ሴት ኮረዶች በትንሹ በሳምንት አንድ ቀን የኮምፒዩተር መስኮት ላይ የሚገኙት የወሲብ ቪዲዮዎችን እና ምስሎች ለመመልከት እንደሆነ አሳይቷል፡፡

ያለንበት ወቅት ታዲያ የወሲብ እና የግንኙነት ቴራፒስቶች የወሲብ ቪዲዮዎች እና ምስሎችን መመልከት ሰዎች በመኝታ ክፍላቸው ከጓደኞቻቸው ጋር ምን እንዲያጋጥማቸው ያደርጋል በሚለው ላይ በይበልጥ ትኩረት አድርገው መስራት የመረጡበት ነው፡፡

የወሲብ ቪዲዮዎችና ምስሎችን መመልከት የወቅቱ መሰረታዊ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የዚህ ችግር ሰለባዎችም ቁጥራቸው ከፍተኛ ሆኗል፡፡ በተለይ ወጣት ወንዶች እና በከፍተኛ መጠን ቁጥራቸው እያደጉ የመጡት ሴቶች ለኢንተርኔት እጅ የሰጡ ሆነዋል፡፡

ችግሩ በወንዶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ግን አሁንም ጫን ያለ ነው፡፡ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የወሲብ ቪዲዮና ምስሎችን ማየት የጀመሩ ወንዶች በኋላ ላይ በግንኙነት (በትዳር) መታሰራቸው ነፃ የሚያወጣቸው ሰዎች ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ አዕምሮን የሚቆጣጠር ከባድ ልማድ ይሆናል ነው የስፔን የካታላን ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ሮድሪገዝ የምትለው፡፡ በርካታ ሚስቶች በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙት ባሎቻቸው ለትዳራቸው ያልታመኑ ያህል ሊቆጥሯቸው ይችላሉ የሚሉት ባለሙያዎች የመፍትሄ ጥረቶቻቸው ውጤታማ ላይሆን ይችላል፡፡

ፓርኖግራፊዎች የወንዶችን አዕምሮ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ከሚደረግ ወሲብ ይልቅ የወሲብ ቪዲዮ እና ምስሎች እርካታ ሊሰጡ እንደሚችሉ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
ለመሰል ወንዶች አንድም ሴት ከምታስገኝለት እርካታ በላይ ይሄ ሱስ በብዙ የተሻለ እንደሆነ እንዲያስብ በጊዜ ርዝመት በውስጡ የተሰራጨውና ቫሶፕሬሲን የተሰኘው ኬሚካል ያስገድደዋል፡፡

ባለሙያዎቹ መሰል ቪዲዮ እና ምስሎችን በድብቅም ሆነ በጋራ መመልከቱ በራስም ሆነ በትዳር አጋር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይስማማሉ፡፡ መደበኛ እና ትክክል የሆነ ባህሪ አይደለም፡፡ በግንኙነት ውስጥ ሲደረግ ደግሞ ለጓደኛ ክብር አለመስጠት እና ማዋረድ እንዲሁም ማመንዘር ወይም ለትዳር ታማኝ አለመሆን እንደሆነ ዶ/ር ሮድሪገዝ ይናገራሉ፡፡ በመሰል ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጋሮቻቸው ራሳቸውን መልከጥፉ፣ የተካዱና የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከማድረግ ባለፈ ልባቸው እና እምነታቸውን ይሰብራል፡፡ በርካታ ጥንዶች በሌላ መልኩ ድርጊቱን በወሲባዊ ህይወታቸው ላይ የሚጨምርላቸው ተግባር እንዳለ በማሰብ የህይወታቸው አካል ያደርጉታል፡፡ ከPom ብዙ እንደሚማሩ በማሰብም በጋራ ቪዲዮውን ምስሎችን መመልከት ያዘወትራሉ፡፡ ይሄኛው እርምጃ ቢያንስ አንዱ የሌለውን እምነት እንዲያጣና የሚሰብርም ልብ እንዳይኖር የተሻለው አማራጭ ይመስላል፡፡

ፓርን ምን አይነት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?
የወሲብ ቪዲዮ እና ምስሎች አቅርቦት እንደ ልብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የጎንዮሽ ጉዳትም በዛው መጠን አግዝፎታል፡፡ ጉዳቱም በየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል የሚገኝን አካል የሚመለከት ነው፡፡

ሙሉ ለሙሉ ከዚህ ልማድ ለመላቀቅ ወስነናል ያሉ በርካቶች ከማረጋገጫቸው ባሻገር በዛው ሱሳቸው ውስጥ የመዝለቅ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡
ሚስቶች ባሎቻቸው አዘውትረው ወሲባዊ ቪዲዮ እና ምስሎችን የሚመለከቱ መሰል ይዘት ያላቸውን ፅሑፎችም እንደሚያነቡ መረጃው ቢኖራቸው እንኳን  ርዕሰ ጉዳዩን አንስተው መወያየቱን አይመርጡም፡፡ ይሄም በሂደት በጥንዶች መሀከል የነበረው ግንኙነት እንዲሻክር ምክንያት ይሆናል፡፡

ሚስቶቻቸውን ስለማፍቀራቸው ማረጋገጫ የሚሰጡት እነዚህ አካላት ለልማዳቸውም ባሪያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ባንዴ ሁለት ግንኙነትን ማስቀጠል ማለት ነው፡፡ ያለ ውጤታማ የባለሙያ እርዳታ እና የግል ቁርጠኝነት በስተቀር መሀላና መገዘት የቱንም ያህል የመጨረሻ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡

የፓርን ሱሰኝነት መገለጫዎች ምንድናቸው?
1. ባሎች በወሲብ ላይ የነበራቸው ፍላጎት ይቀንሳል
ብዙዎቹ የዚህ ችግር ተጠቂዎች ሱሳቸውን ለማስቀጠል ራስን በራስ ማርካትን ደጋግመው ሊፈፅሙ ስለሚችሉ ከጓደኞቻቸው ጋር መደበኛው ወሲብ ላይ የነበራቸው ፍላጎት ይቀንሳል ለሌሎች የእርካታ አይነቶችም መደንዘዝም ይታይባቸዋል፡፡
2. ወንዶች በወሲብ ጊዜ የብልት መቆም ችግር ሊገጥማቸው ይችላል

የፓርን ሱሰኞች ከብልት መቆም ችግር ጋር መጋፈጣቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ በእነዚህ ሰዎች ችግሩ በኦርጋናቸው ውስጥ ሳይሆን በአእምሮአቸው ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ አዕምሯቸውን ለዚህ እርካታ ለማነቃቃት የወሲብ ቪዲዮ እና ምስሎችን መመልከት የግድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

3. ወንዶች ቀድሞ ከወሲብ ያገኙት የነበረው እርካታ ይቀየራል

ከትዳር አጋር ጋር ወይ ከፍቅረኛ ጋር ይደረግ የነበረው ፆታዊ ግንኙነት በፓርን አማካኝነት ሌላ ቅርፅ ሊይዝ ይችላል፡፡ ቪዲዮ እና ምስሎችን በመመልከት የተለያዩ የወሲብ ድርጊቶችን በተለይ ወንዱ የተመግበር ፍላጎት ሊያሳድር ይችላል፡፡ ሁኔታው ታዲያ የሴቷን ምቾት ከመንሳት ባለፈ በራስ መተማመኗን ሊያሳጣት ይችላል፡፡
4. ወንዶች ረጅሙን ጊዜያቸውን በኮምፒዩተር ላይ ማሳለፍ ይጀምራሉ

የፓርን ሱሰኞች ብዙ ጊዜ ከቴክኖሎጂዎች ጋር የተለየ ቁርኝት ይፈጥራሉ፡፡ ለብቻቸው ከኮምፒውተራቸው ስክሪን ላይ እንዳፈጠጡ ለሰዓታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

5. በስሜት ከጓደኛ እና ቤተሰብ መነጠል ይታይባቸዋል
ወንዶች ይበልጥ በፓርን ሱስ ሲተበተቡ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከሚስት እና ከልጆች ጋር እንዲሁም ከእውነተኛው ዓለም ጋር የነበራቸውን ግንኙነት እያጡ ይመጣሉ፡፡
እርዳታዎቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ::

Pom ከመመልከት ግለሰብን የሚታደግ አንዳችም መድሃኒት የለም፡፡ ብቸኛው አማራጭም ራስን እንደ ወሲብ ሱሰኛ ቆጥሮ ለዚህ ችግር የሚደረገውን የስነ ልቦና ህክምናን በቁርጠኝነት መከታተል ይሆናል አማራጩ፡፡ ይሄኛው መፍትሄ ችግሩ በግለሰቡ ላይ ስር የሰደደ እና ጥልቅ ጉዳይ መሆኑ ከታመነበት የሚገባበት ነው፡፡
በባለሙያዎች ሁለቱም ወገኖች ማለትም ወንዱ እና ሴቷ ግንኙነታቸውን ጤናማ ማድረጋቸው እና በችግሩ ላይ አብሮ ለመስራት ያላቸው ተነሳሽነት መሰረታዊ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ወሲባዊ ቪዲዮዎች እና ምስሎች አልፎ አልፎ መጠቀሙ ካለፉት ዓመታት አንፃር በዚህ ዘመን የተለመደ ተግባር ሆኗል፡፡ በባለሙያዎቹም ጤናማ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

አስተማሪ እና መረጃ ለማግኘት የተለያዩ ቪዲዮዎች እና የኢንተርኔት ሳይቶች ግንኙነት የሚደገፉ መሳሪያዎች ሆነው እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ከመደበኛ የህይወት ዑደት የሚነጥል እና በቀላል ሊገላገሉት ያለመሆኑ ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.