ሎሚ በቫይታሚን ሲ እና ቢ፣ፎስፈረስ፣ኘሮቲንና ካርቦሀይድሬት የበለፀገ የፍራፍሬ ነው።ሎሚ ፍላቮይድ የተባለ ንጥረ በውስጡ ይዟል ይህ ንጥረ ነገር የካንሰር በሽታን ይከላከላል። ሎሚን በብዙ መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን።ከነዚህም መካከል የሎሚ ሻይ፣የሎሚ ኬክ፣ የሎሚ ዘይትና የሎሚ ሳሙና ይጠቀሳሉ።ከነዚህም በተጨማሪ የህክምና ጥቅሙም ላቅ ያለ ነው። ህክምናዊ ጥቅሞቹ እንደሚከተሉት ናቸው
1. የጉሮሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል
ሎሚ የጉሮሮን ኢንፌክሽን ከሚከላከሉልን ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን የፀረ ባክቴሪያ (ባክቴሪያን የመከላከል) ሀይል አለው እናም የሎሚ ጭማቂ ከውሀ ጋር ቀላቅለው ወይም በሻይ መልክ ቢወዱት ጥቅሙ ላቅ ያለ ነው።
2. ምግብን ለማንሸራሸርና የሆድ ድርቀትን ለመከላከል
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ የምግብ አለመፈጨትንና የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። በምግብዎ ውስጥ ትንሽ ጠብታ ሎሚ መጨመር ተገቢ ነው ነገር ግን ሎሚ ከወተት ጋር መቀላቀል እንደሌለብዎት እንዳይዘነጉ።ሎሚ ደምን ያጣራል በተጨማሪም ጥሩ ማፅጃ( ማጠቢያ) በመሆን ያገለግላል።
3. ትኩሳትን ለማስታገስ
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ በብርድ፣በሳልና በትኩሳት ለሚሰቃዩ ሰዎች ፍቱን መድሀኒት ነው።የሰውነታችንን ትኩሳት ቶሎ ቶሎ እንዲያልበን በማድረግ ያስታግሳል። እኩል መጠን ያላቸውን የተፈጥሮ ማርና የሎሚ ጭማቂ በመቀላቀል ወይም የሎሚ ሻይ በመጠቀም ሳልን መቀነስ የሚቻል ሲሆን ከባድ የጉሮሮ በሽታን ለማስታገስ ይረዳናል።
4. ለጥርስ እንክብካቤ ይጠቅመናል
የሎሚ ጭማቂ ለጥርስ እንክብካቤና ህክምና ያገለግላል። የጥርስ ህመምበሚያጋጥምበት ጊዜ ትኩስ(fresh) የሎሚጭማቂ በህመሙ ቦታ ላይማድረግ ፍቱን ማስታገሻነው።በተፈጥሮ የሎሚ ጭማቂ ድድን ማሸት ከድድ መድማት ችግርና ከመጥፎ የአፍ ጠረን ይታደግዎታል በተጨማሪም ሁልጊዜ ጥርስዎን ቢቦርሹበት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
5. የቆዳ እብጠትን ለመቀነስ
የሎሚ ጭማቂ የቆዳ እብጠትን የሚቀንስ ሲሆን ሰውነታችን ላይ ባለው እባጭ ላይ ያድርጉት በተጨማሪም ከዉሀ ጋር የተቀላቀለ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ለኩላሊት ጠጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
6. የተቃጠለ ቁስልን ያስታግሳል
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ በተቃጠለው የሰውነታችን ቁስል ላይ ማድረግ ጠባሳ (scar) እንዳይዝ (እንዳይኖር) ያደርጋል። ሎሚ ሰውነታችንን የማቀዝቀዝ ባህሪ ስላለው በቃጠሎ ምክንያት የሚመጣን የመለብለብ(የማቃጠል) ስሜት ያስታግሳል።                                                                                              

 7. ውስጣዊ የደም መድማት
የሎሚ ጭማቂ ውስጣዊ መድማትን ይከላከላል ምክንያቱም ሎሚ ፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላሉት ነው። የአፍንጫ መድማትን ለመከላከል በሎሚ ጭማቂ የተነከረ ጥጥ በአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ከተው ለትንሽ ደቂቃዎች ማቆየት ይመከራል።
8. የወባና አተት(Cholera) በሽታዎችን ለመከላከል
ሎሚ ደምን የማጣራት አቅም ስላለው እንደ ወባና አተት ያሉ በሽታዎችን ይከላከላል።
9. እግር ዘና እንዲል ያደርጋል
ሎሚ ጠንካራ ሽታና ፀረ ባክቴሪያ ኬሚካላዊ ባህሪ አለው ስለዚህ ለብ ባለ ውሀ ውስጥ የሎሚ ጭማቂ አድርገው እግርዎን መንከር እግርዎ ዘና እንዲል ያደርገዋል።
10. ለቆዳ እንክብካቤ
የሎሚ ጭማቂ እርጂናን የሚከላከል ሲሆን የቆዳ መሸብሸብና ቆዳ ላይ ያሉ ትንንሽ ጥቁር ነጠብጣቦችን እንዲሁም የተለያዩ ችግሮችን የፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው እንዲወገድ በማድረግ ይሳተፋል። የፀሀይ ጨረርን ለመከላከል ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ ፊትን መቀባት ጠቃሚ ነው።ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ ከማርና ውሀ ጋር በመቀላቀል መጠጣት ጥርት ያለ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል።
11. ለመገጣጠሚያና ጡንቻ ህመሞች
ይህ ህመም ብዙ ጊዜ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን ሎሚ የማይፈለጉ የሰውነት ፈሳሾችን እንዲወገድ በማድረግ የመገጣጠሚያና ጡንቻ ህመሞችን ያስታግሳል ከዚህም በተጨማሪ በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን ባክቴሪያና መርዛማ ነገሮች እንዲወገድ ያደርጋል።
12. ክብደት ለመቀነስ
የሎሚ ጭማቂን ለብ ካለ ውሀና ማር ጋር በመቀላቀል መጠጣት የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳናል። የሎሚ ጭማቂ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳናል ብላችሁ ብትጠይቁኝ አዎ በትክክል ይቀንሳል እልዎታለሁ።
13. የአተነፋፈስ ችግርን ያስተካክላል
ሎሚ የአተነፋፈስ ችግርን ያስተካክላል። ሎሚ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ የአስምና የመተንፈሻ አካላት ችግር ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው።
14. ደም ግፊት
ወዲያው የተዘጋጀ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት በውስጡ ፓታሲየም ስላለው በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚ ነው። ከፍተኛ ደም ግፊትን፣ መንገዳገድ(ማዞር)ና ማቅለሽለሽን በመቆጣጠር አእምሮና ሰውነታችን ዘና እንዲል ያደርጋል።
15. ለፀጉር እንክብካቤ
የሎሚ ጭማቂ ፀጉርን በማከም ከፍተኛ ድርሻ አለው እንደ ፎረፎር፣ የፀጉር መነቃቀልና ከራስ ቅል ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከል የሎሚ ጭማቂን የራስ ቆዳ አናት ላይ መቀባት ጠቃሚ ነው። የሎሚ ጭማቂ ፀጉርን መቀባት ፀጉራችን አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል።

መልካም ጤንነት!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.