ዳንኤል አማረ

Front-image_drinking-water1አብዛኞቻችን ፈሳሽ ነገሮች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ሻይ እና የመሳሰሉትን መጠጣት ለሰዉነታችን የሚያስፈልገዉን ዉሃ እንደሚተካ እናስባለን፡፡ እዉነታው ግን እነዚህ ፈሳሾች ስኳር እና ጨው በውስጣቸው ስለሚይዙ በሰውነታችን ተመጠው በዉሃ እርዳታ ከእንሽርሽሪት ይወገዳሉ፡፡ በየቀኑ 8 ያህል ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ለጤና ተስማሚ ነው የአፍና ጉሮሮ ድርቀት እንዳይከሰት ከማድረጋቸው በላይ የተለያዩ በሽታዎችና ህመሞችን ይከላከላል፡፡

በአሜሪካ በአንድ ወር ውስጥ 3.9 ትሪሊዮን ጋሎን ውሃ ሲጠቀሙ በቀን በአማካይ 176 ጋሎን ውሃ ይጠቀማሉ፡፡ ምንም አይነት ምግብ ሳንመገብ በአማካይ ለአንድ ወር መቆየት ስንችል ዉሃ ሳንጠጣ መቆየት የምንችለው አንድ ሳምንት አካባቢ ብቻ ነው፡፡ ሰውነታችን በአማካይ 75% ውሃ ሲሆን ከደም ውስጥ 92% ፣ ከአጥንታችን ውስጥ 22% ፣ ከጡንቻችን ውስጥ 75% ውሃ ነው፡፡ በጣም አስገራሚው ግን ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም የሚወሰነው በምንጠቀመው የውሃ መጠን መሆኑ ነው፡፡

ሰውነታችን የፈሳሽ እጥረት/ድርቀት የሚያጋጥመን ውሃ ከመጠማታችን በፊት ነው፡፡ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ቀኑን ሙሉ ትንሽ ትንሽ ውሃ መጎንጨት በውሃ እንዳንጠማ እና የፈሳሽ እጥረት እንዳይከሰት ይረዳናል፡፡ ንጹህ ቀዝቃዛ ውሃ ሁሌም ከእንቅላፋችን ስንነሳ መጠጣት የደም ግፊታችንን ከማስተካከል በተጨማሪ ሆዳችን ምግብ ለመፍጨት ዝግጁ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ብዙ ፈሳሽ እንዲኖር ማድረግ ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ነው ነገር ግን የዚህ ፈሳሽ አለመኖር ደማችን እንዲወፍር በማድረግ የደም ፍሰት እንዲስተጓጎል ያደርጋል የዚህም ዉጤት የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በደም ውስጥ ኮሌስትሮል እንዲጨምር ያደርገዋል ይህ ሂደት ሰዉነታችን በሴሎቻችን ውስጥ የውሃ እጥረት እንዳይፈጠር የሚከላከልበት መንገድ ነው፡፡ ከፍተኛ የኮሌስትሮል እና ከፍተኛ የደም ግፊት ኮሮናሪ ለተባለው የልብ በሽታ የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል፡፡
የሰውነታችን ፈሳሽ እጥረት/ድረቀት ከመጠን ላለፈ ውፍረት፣ ለአይነት 2 የስኳር በሽታ፣ ለከፍተኛ የደም ግፊት እና ካንሰር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል፡፡ ቢሆንም ግን ሁለት ብርጭቆ ውሃ ከቁርስ፣ ምሳ እና እራት በፊት መጠጣት እነዚህን ችግሮች ለመከላከል ይረዳናል፡፡ በመደበኛ ሁኔታ ውሃን መጠቀም ምግብ የመፍጨት ሂደትን በማፋጠን ሙሉ የጤናማነት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል ከዚያም የተስተካከለ የሰውነት አቋም፣ ጤናማ አእምሮና የተስተካከለ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

መልካም ጤንነት!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.