ጃኗሪ 28ቀን 2020..

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ / coronavirus ምንድን ነው/?

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ /Novel coronavirus (2019-nCoV) ከ ዲሴምበር 2019 ጀምሮ ወደሰዎች ሲተላለፍ የነበረ ቫይረስ ነው። ስለዚህ አዲሱ ቫይረስ ብዙ ስለማይታወቅ የጤና ባለሞያዎች ስጋት አላቸው። ይህ ቫይረስ በአንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ህመም እና ኒሞኒያ/pneumonia ይፈጥራል።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ/ coronavirus ምን ያክል ከባድ ነው?

ባለሞያዎቹ እስካሁን ይህ አዲሱ ቫይረስ ስለሚያስከትለው የህመም ደረጃ እየተማሩ ነው። የተዘገቡ ህመሞች ከቀላል (እንደ ጉንፋን ያሉ) ሃኪም ቤት እስከ መተኛትን የሚያደርሱ ከፍተኛ/ከባድ የኒሞኒያ/pneumonia ህመም ድረስ ያደርሳል። . እስካሁን በተለይ እድሚያቸው በገፋ እና ሌላ የጤና ችግር ባላቸው ሰዎች ላይ ሞት ማስከተሉ ተመዝግቧል።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ /coronavirus እንዴት ይዛመታል?

የጤና ባለሞያዎች እስካሁን ስለበሽታው የሚዛመትበትን መንገድ እያጤኑ/እየተማሩ ነው ። በሌሎች የኮሮናቫይረስ/coronaviruses ጉንፋን እንደተለመደው አይነት በበሽታው ከተያዘው ሰው ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፈው፦

 • በአየር አማካኝነት ሲሆን በማሳል እና በማስነጠስ ነው።
 • የተቀራረበ የሰው ለሰው ግንኙነት ለምሳሌ እንደ በመነካካት ወይም በመጨባበጥ ።
 • ቫይረሱ ያለባቸውን እቃዎችን ወይም ወለሎችን መንካት እና መልሶ አፍን ፣ አፍንጫን ወይም አይኖችን በመካት ።
 • አልፎ አልፎ ፊትን በመንካት።

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

አዲሱ የኮሮናቫይረስ/coronavirus የተገኘባቸው ሰዎች ከ2 እስከ 14 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከተሉት ምልክቶቹ ሊታይባቸው ይችላል ፦

 • ትኩሳት
 • ሳል
 • ለመተንፈስ መቸገር

ለአዲሱ የኮሮና ቫይረስ/coronavirus ተጋላጭ የሆነው ማነው?

በዚህ ሰአት ወደ ቻይና Wuhan ግዛት ተጉዘው የነበሩ ጥቂት ለበሽታው የተጋለጡ ሰዎች በአሜሪካ ይገኛሉ። በአሜሪካ የአዲሱ የኮሮናቫይረስ /coronavirus በሽታ በነዚህ ገጠመኞች ምክንያት ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ ሁኔታ አልተከሰተም። ስለዚህ እንደማህበረሰብ ጤና ስጋት የመሆን እድሉ ዝቅተኛ ነው። የመተላለፊያ ስጋቶችን ለመቀነስ የጤና ባለሞያዎች ከጤና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ጋር ተጠርጣሪ ታማሚ ሲገኝ በፍጥነት ምርመራ ለማካሄድ አብረው እየሰሩ ነው።

A Fairfax County, Va., publication. ጃኗሪ 28ቀን 2020 ዓ.ም.

ይህን መረጃ በሌላ አማራጭ መገድ ለመጠየቅ እባክዎ ወደ ጤና ክፍሉ/Health Department በ703-246-2411, TTY 711 ይደውሉ።

Health- Coronavirus Factsheet

Fairfax County የጤና ክፍል

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ/Coronavirus

(2019- nCoV)

ይህ በፍጥነት ግምገማ የማካሄድ ሁኔታ ስለሆነ መመሪያው ሊቀያየር ይችላል። ይመልከቱ wwwnc.cdc.gov/travel/notices ከ CDC የሚሰተውን ወቅታዊ የጉዞ መመሪያ ይመልከቱ ።

አዲሱን የኮሮና ቫይረስ/coronavirus እንዳይዘኝ እንዴት እራሴን መከላከል እችላለሁ ?

ወደ ውጪ የሚጓዙ ከሆነ (ቻይና እና ሌሎች ቦታዎች) የCDCን መመሪያ ይከተሉ wwwnc.cdc.gov/travel/notices.

ጉንፋን እና ሌሎች ተመሳሳይ በሽታዎች እንዳይተላለፍ የሚከላከሉበት መንገድ አዲሱን የኮሮና ቫይረስ/coronavirus ለመከላከል ይተቀማሉ።

 • እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ ታጠቡ:: ካልተገኘ የእጅ ማጽጃ/hand sanitizer ይጠቀሙ።
 • አይኖቾን ፣ አፍንጫዎን ፣ አፎን ባልታጠበ እጅዎ ከመንካት ይቆጠቡ።
 • ከታመሙ ሰዎች ጋር ያልዎትን ግንኙነት ያስወግዱ ።
 • ከታመሙ እቤት ይቆዩ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት አያድርጉ።
 • አፍዎን/አፍንጫዎን ይሸፍኑ ወይም ሲያስሎት እና ሲያስነጥሱ ይሸፍኑ።

በሁኑ ሰአት አዲሱን የኮሮና ቫይረስ/coronavirus ህመምን የሚከላከል ክትባት የለም።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ/coronavirus እንዴት ይታከማል?

አብዛኛው መለስተኛ የሆነ ቫይረስ/coronavirus ህመም ያለባቸው ሰዎች ብዙ ፈሳሽ በመጠጣት ፣ በማረፍ እና የህመም እና ትኩሳት ማስታገሻ መድሃኒት በመውሰድ ይድናሉ። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ኒሞኒያ/pneumonia ይይዛቸው እና ህክምና ለማግኘት ሃኪም ቤት መግባት ይኖርባቸዋል። ለአዲሱ ኮሮናቫይረስ/coronavirusl በተለየ ምንም አይነት መድሃኒት የለም።

Fairfax County የበሽታው መራባትን ለመከላከል ምን እያደረገ ነው ?

የFairfax County የጤና ክፍሉ በአካባቢው ካሉ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ፣ ከማእከላዊ መንግስት፣ ከክልሉ እና ከክፍለከተማው አጋሮች ጋር በጋራ በመሆን ሁኔታውን በቅርብ ሆኖ እየተከታተለ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን በፍጥነት ለመለየት እየሰራ ነው። በአሁኑ ሰአት ወደ ቻይና Wuhan ግዛት የተጓዙ ሰዎችን እና ትኩሳት ፣ ሳል እና/ወይም ለመተንፈስ የሚቸገሩ በተቻለ ፍጥነት ወደ ጤና አገልግሎት ደውለው ምን መደረግ እንዳለባቸው መመሪያ ማግኘት አለባቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.