አራት ጊዜ ጸንጻ ያልተሳካላት ኢትዮጵያዊት እናት በአንድ ጊዜ አራት ወንድ ልጆችን በቢሾፍቱ ሆስፒታል በሰላም ተገላግላለች፡፡

ነዋሪነቷ ምስራቅ ወለጋ ዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ ከተማ የሆነቺው ወ/ሮ ሽብሬ ቀደም ሲል አራት ጊዜ አርግዛ አራቱንም ተጨናግፎባታል፡፡

ቀደም ሲል አጋጥሟት በነበረው ጽንስ የማቋረጥ ችግር ሲጋት ያደረባት ሽብሬ ትኖርበት ከነበረው አከባቢ ወንድሟ ወደ ሚኖርበት ዱከም ከተማ መሄዷን ትናገረለች፡፡

ባጋጠማት ችግር ምክንያት ልቧ ያዘነው ሽብሬ በአምስተኛው እርግዝናዋ እድል ቀንቷት 4 ልጆችን በሰላም ለመታቀፍ በቅታለች፡፡

ክስተቱ ከ60 ሺህ ወሊድ አንድ ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑን የቢሾፍቱ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ ገልጸዋል ፡፡

በሆስፒታሉ በተደረገላቸዉ በቂ ህክምና እናትና አራቱም ህጻናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ከቢሾፍቱ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመተማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.