ምግብ ከተመገቡ በኃላ በፍጽም ሊያደርጓቸው የማይገቡ ተግባሮች

1. ትኩስ ሻይ መውሰድ

ሻይ የበላነውን ምግብ እንዳይዋሀድ ያደርጋል። ሻይ በውስጡ ያለው ቁስ ነገር ብረት(iron) የተሰኝውን ንጥረ ነገር ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድ ለብረት እጥረት እና ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል።

በተጨማሪም ሻይ (Tannin) የተሰኝውን ንጥረ ነገር በመያዙ ሰውነታችን ፕሮቲን እንዳይመጥ ያደርገዋል። ስለዚህ ሻይን ምግብ ከተመገቡ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በኃላ መውሰድ ለጤናዎ እጅግ አስፈላጊ ነው።

2. አትክልቶችን (ፍራፍሬዎችን) መመገብ

ፍራፍሬዎችን ከምግብ በኃላ መመገብ ከሌሎች ምግቦች ጋር በማጋጨት ወደ ጨጓራችን እንዳይደርስና ብሎም ከርሳችን እንዲነፋ ያደርጋሉ። በመሆኑም ፍራፍሬዎችን ከምግብ በኃላ ከመመገብ ይልቅ በጠዋት መመገብ ንጥረ ነገራቸውን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረድናል።

3. ሲጋራ ማጨስ

ትንባሆ ከምግብ በፊትም ሆነ በኃላ ማጨስ ጤናማ አይደለም። ትምባሆ በውስጡ እስከ 60 የሚደርሱ ካርሲኖጅን(Carcinogen) የተሰኝ ካንሰርን የሚያስከትሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል። በተጨማሪም ትንባሆ ኒኮቲንና ታር የተሰኙ ጤናን የሚጎድ ነገሮችን ይዟል። ከምግብ በኃላ ትምባሆ ማጨስ ማለት 10 ሲጋራዎችን ከምግብ ሰዓት ውጪ በማጨስ ከሚከሰተው ካንሰርን እና የመተንፈስ ስርዓትን ለሚያውክና ለመሳሰሉ በሽታዎች የማጋለጥ አቅም ይኖረዋል።

4. ቀዝቃዛ ውሀ መውሰድ

ቀዝቃዛ ውሀ ከምግብ በኃላ መውሰድ ምግብን አንድ ላይ በማሰባሰብ የምግብ እንሽርሽሪት ጤናማ እንዳይሆን ያደርገዋል። ቀዝቃዛ ውሀ ከመጠቀም ይልቅ ሞቅ ያለ ውሀ ያለ ውሀ መጠቀም ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን እንዲመጥ ያግዘዋል። ከዚህ በተጨማሪም ውሀን ከምግብ በፊት መውሰድ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮች እንዲዘገዩ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራሉ።

5. መተኛት

ምግብ ከተመገብን በኃላ ወዲያው መተኛት የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ያደርጋል። በሌላ በኩልም ስርዓተ እንሽርሽሪትን በማስተጔጎል የከርስና የሆድ ችግር ያስከትላል።

6. ሰውነትን መታጠብ

ሰውነትን መታጠብ የደም ዝውውር በተለይ በእጅ እና እግር አካባቢ እንዲፋጠን ያደርገዋል። ይህም በሆድ አካባቢ የሚገኝን የደም ክምችት እንዲቀንስ እና የምግብ እንሽርሽሪት እንዲዳከም ያደርጋል ከዚህ ባሻገር የልብ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

7. ውዝዋዜ

የሰውነት እንቅስቃሴና ውዝዋዜ ማድረግ ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን በአግባቡ እንዳይመጥ(እንዳይዝ) ያደርገዋል።

8. የእግር ጉዞ

ከምግብ በኃላ የእግር ጉዞ ማድረግ ተገቢ አይደለም። እንሽርሽሪት ስርዓት እንዳይኖረውና ያልተለመደ የአሲድ ኡደት በብዙዎች ዘንድ እንዲፈጠር ያደርጋል። ስለሆነም የእግር ጉዞን ከ 20 ደቂቃ የምግብ ሂደት በኃላ ቢደረግ ይመከራል።

9. ቀበቶ መፍታት/ማላላት

ምግብ ሳይመገቡ ቆይታ ማድረግ ጤናማ ያልሆነና ልማዳዊ ድርጊት መሆኑ ይታወቃል ይህም ለምግብ አመጋገብ ጥሩ የማይባል ስርዓት ነው።ስለዚህ ምግብን በመጠኑና በአግባቡ ቀበቶዎትን ሳያላሉና ሳይፈቱ መመገብ ከአቅም በላይ በመመገብ የሚከሰትን ችግር መከላከል ይቻላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.