ዘመነ እርጠት (Menopause) በወንዶች ይኖር ይሆን? (በዳንኤል አማረ)

0

AgingMenየወንዶች ዘመነ እርጠት የሚከሰተው ቴስቴስትሮን የሚባለው ሆርሞን መመረት ሲቀንስ ነው። ከሴቶች ዘመነ እርጠት ጋር ሲነፃፀር በወንዶች ላይ የሂደቶቹ መገለጫዎች ዘግይተው ይጀምራሉ ከዚያም ለውጣቸው የዘገየ ይሆናል። እድሜያቸው ከ25-75 ዓመት ያሉ ወንዶች ላይ የፍትወተ ስጋ ስራ/አገልግሎት ቀስ በቀስ መቀነስ ይታይባቸዋል በዚህ ጊዜ የሚኖረን የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን በ 50% ይቀንሳል ይህ ቁጥር ከሰው ወደ ሰው ይለያያል።

የዚህ ችግር መገለጫ ምልክቶች የአቅምና አእምሮ መዳከም፣ ድብርት፣ በቀላሉ መበሳጨት፣ የባህሪ መለዋወጥ፣ የጡንቻዎች መቀነስ፣ የስብ(fat) መጨመር፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የስሜት ጣሪያ ላይ ለመድረስ መቸገር፣ የፍትወተ ስጋ ቀጥ ብሎ ለመቆም መቸገር ናቸው።

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ወንዶች የቴስቴስትሮን ሆርሞን ህክምና ያደርጋሉ ህክምና በመውሰዳቸውም የተሻለ ለውጥ ማምጣታቸውን ተናግረዋል። የዚህ ህክምና የጐንዮሽ ጉዳት ለፕሮስቴት ካንሰርና አርተሪዮ ስኬሌሮሲስ በሽታ የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።
ብዙ ኢክስፐርቶች እንደሚያምኑት ከሆነ ይህ ሁኔታ ከሆርሞን ውጪ ወይም በተፈጥሮ የዕድገት ሂደት ደረጃ የተፈጠረ ነው ይላሉ። የዕለት ከዕለት አኗኗር ዘይቤአችን አልኮልና አደንዛዥ እጽ መጠቀም፣ መድሀኒቶች፣ በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙን ችግሮች፣ የገንዘብ/ኢኮኖሚ እጥረት እና ጭንቀት ለዚህ ችግር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል።
የወንዶች ዘመነ እርጠት እና ይህን ችግር ለመከላከል የሚደረጉ ሆርሞንን የመተካት ህክምና አወያይና አከራካሪ ሀሳቦች ናቸው። በተለያዮ ቦታዎች ከወንድ እድሜ መጨመር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ለውጦችን የተለያየ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

መልካም ጤንነት!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.