ሽንኩርት ስንከትፍ ለምን እናለቅሳለን?

 

ሽንኩርት ሲቆረጥ/ሲከተፍ ላችራማቶሪ ፋክተር ሲንቴስ (Lachrymatory-factor-synthase) የተባለሽንኩርት ስንከትፍ ለምን እናለቅሳለን ኢንዛይም ይለቃል ይህም እንባ እንዲፈጠር የሚያደርገውን ሂደት ያስጀምራል ይህ ኢንዛይም በሽንኩርት ውስጥ ካለው አሚኖ አሲድ ጋር ይዋሀዳል በዚህ ጊዜ አሚኖ አሲድ ወደ ሰልፈኒክ አሲድ ይቀየራል። የተቀየረው ሰልፈኒክ አሲድ በፍጥነት ራሱን በመቀየር ሲን ፕሮፓኒታል ኤስ ኦክሳይድ ይፈጠራል ይህ የተፈጠረው ኬሚካል ወደ አየር ይለቀቃል። ወደ አየር የተለቀቀው ኬሚካል ወደ አይን ሲደርስ የኮርኒያ ነርቭ ፋይበሮችን በማነቃቃት እንባ እንዲፈጠር ለማድረግ የእንባ እጢ/ከረጢት ያነሳሳል በዚህ ጊዜ ስቅስቅ ብለው ያለቅሳሉ ማለት ነው።

ሳይንቲስቶች የማያስለቅስ ሽንኩርት ለመፍጠር ሞክረዋል ነገር ግን እንባ እንዲፈጠር የሚያደርገው ኢንዛይም ለሽንኩርት ጣፋጭ ጣዕም እና ሽታ እንዲኖረው የሚያደርግ ወሳኝ ቅመም ሆኖ ስለተገኝ ጥናቱ ያልተሳካ ቢሆንም ምርምሩ ግን ተስፋ አስቆራጭ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።

ሽንኩርት ስንከትፍ እንዳናለቅስ የሚያደርጉ ዘዴዎች እነዚህ ናቸው ሽንኩርት ከመክተፋችን በፊት ማሞቅ፣ የላጥናቸውን ሽንኩርቶች ውሀ ውስጥ መክተት፣ ጐግል(የአይን መነፀር የሚመስል) ማድረግ ናቸው።

መልካም ጤንነት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.