eating fishአሳን መመገብ ከጣፋጭ ጣዕሙና ጥሩ ሽታው በተጨማሪ ብዙ የምግብነት ይዘቶች አሉት። አሳ ለህፃናትና ማንኛውም ሰው በየዕለቱ እንዲመገቡት ይመከራል በውስጡ ፕሮቲን፣ ጠቃሚ አስፈላጊ ዘይቶች፣ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ፣ ካልሲየምና ሌሎች ሜኔራሎችን ይይዛል።

አሳ የፕሮቲን ገነት በመባል ይታወቃል ቆዳችን ለስላሳ፣ ተለጣጭና ያማረ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን ኮላጅን ለተባለው የፕሮቲን አይነት ጥሬ ዕቃ ያቀርባል።

የባህር ውስጥ ምግቦች በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የበለፀጉ ናቸው ይህ ጠቃሚ ፋት በደም ውስጥ ያለውን ትራይግላይሴራይድ በመቀነስ የልብ እና የአእምሮ ጤናን ይጠብቃል።
የባህር ውስጥ ምግቦች በቫይታሚን እና ሚኒራሎች የበለፀጉ ሲሆን ለተሻለ የአይን እይታ ያገለግሉናል። እነዚህ የባህር ውስጥ ምግቦች ድብርትን ለመከላከል ይረዳል። አንዳንድ አሳዎች ሪቦፍላቪን እና ኒያሲን የተባሉ ቫይታሚኖችን እንዲሁም አይረን(ብረት)፣ ፎስፈረስ እና ፓታሲየም የተባሉ ሚኒራሎችን ይዘዋል እነዚህ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰቱ እንደ አርትራይተስ፣ ካታራክት(የአይን ህመም) እና የልብ ህመሞችን ይከላከላሉ።

በመጨረሻም የተለያዮ አይነት የአሳ ዝርያዎች ሲኖሩ የሚይዙት የቫይታሚን እና ሚኒራሎች ዓይነት እና መጠን ይለያያል ስለዚህ የሚሰጡትም የጤና ጥቅም እንደዚሁ ይለያያል።

ጤና ይስጥልኝ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.