የፀጉር መመለጥ በተለምዶ ላሽ የምንጠራው

0

1509959_1575584452715418_5142327254248670011_n

የፀጉር መመለጥ በራስ ላይ አሊያም በመላ ሰዉነት ላይ ሊከሰት ይችላለል፡፡ ይህ ክስተት ከዘር፣ከሆርሞን መለዋወጥ፣የዉስጥ ደዌ ችግሮችና በመድሃኒቶች ምክንያት ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ በማንኛዉንም ሰዉ ላይ (ወንድ፣ሴት፣ ህፃን ሳይል) ሊከሰት ይችላል፡፡
ራሰበራነት የሚከሰተዉ የራስ ፀጉር መመለጡ ከመጠን በላይ ሲከሰት ሲሆን ከከዕድሜ ጋር የሚመጣ ከዘር ጋር ተያያዥነት ያለዉ መንስኤ አለዉ፡፡ ለፀጉርዎ መመለጥ መድሃኒት ከመጀመርዎ በፊት መንስኤዉ ምን እንደሆነ ለማወቅ ከህክምና ባለሙያዎ ጋር መወያየት ያስፈልጋል፡፡
የፀጉር መመለጥ ችግሩን እንዳመጣዉ መንስኤ በተለያየ መልክ ሊታይ ይችላል፡፡ አንዳንዴ በፍጥነት የሚታይ ችግር ሲሆን ሌላ ጊዜ ደግሞ ደግሞ ቀስ በቀስ የሚከሰት ችግር ነዉ፡፡ አንዳንዱ ጊዜያዊ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ሊድኑ የማይችሉ ችግሮች ናቸዉ፡፡

የፀጉር መመለጥ የህመም ምልክቶች
· ቀስ በቀስ የራስ ፀጉር መሳሳት፡- ይህ በጣም የተለመደና ወንዶች ላይም ይሁን ሴቶች ላይ ዕድሜያቸዉ እየጨመረ ሲመጣ የሚታይ ነዉ፡፡ በወንዶች ላይ የፀጉር መሳሳት የሚጀምረዉ በአብዛኛዉ ከፊት በኩል ሆኖ ወደ ኃላ ቀስ እያለ እየሸሸ የሚሄድ ነዉ፡፡

· ክብ መመለጥ፡- አንዳንድ ሰዎች ለስላሳ የሆነ የሳንቲም ቅርፅ ያለዉ መመለጥ ይታይባቸዋል፡፡ ይህ በተለምዶ ላሽ የምንለዉ ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ በብዛት የሚከሰተዉ በራስ ፀጉር ላይ ሲሆን አንዳንዴ በሰዉነት ቆዳ ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡

· ድንገታዊ የሆነ የፀጉር መመለጥ፡- ይህ አካላዊ ወይም ስነአእምሮያዊ ጉዳት በሚደርስብን ወቅት የሚከሰት ሲሆን ሰዎች ፀጉራቸዉን በሚያበጥሩበት ወይም በሚታጠቡት ወቅት ብዙ ፀጉር እየተነቃለ የፀጉር መሳሳት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ይህ አይነቱ ክስተት ሙሉ ጭንቅላት ላይ አጠቃላይ የፀጉር መሳሳት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡

· ሙሉ በሙሉ የፀጉር መመለጥ መኖር፡- የተወሰኑ የጤና ችግሮችና ለካንሰር ህክምና የሚደረጉ እንደ ኬሞቴራፒ ያሉ ህክምናዎች የሰዉነት ፀጉር ሙሉ በሙሉ እንዲመለጥ ያደርጋሉ፡፡ ከህክምና በኃላ ብዙዉን ጊዜ ፀጉሩ ተመልሶ ይበቅላል፡፡

· ክብ ክብ የሆኑ ቅርፊት መሳይ ነገሮች የፀጉር ቆዳ ላይ መከሰት፡- ይህ የፈንገስ ምልክት (ringworm) ሊሆን ይችላል፡፡

የፀጉር መመለጥን ሊያመጡ የሚችሉ ምክንያቶች፡-
ብዙ ሰዎች ላይ በየቀኑ ከ50 እስከ 100 ፀጉሮች ተነቅለዉ የሚወድቁ ሲሆን ይህም በአይን የሚታይ ለዉጥ ሳይኖረዉና ፀጉሩ ሳይሳሳ ያልፋል፡፡ ምክንያቱም በዚያኑ ቦታ አዲስ ፀጉር ስለሚተካ ነዉ፡፡ ምንም እንኳ ለፀጉር መመለጥ ይህ ነዉ የሚባል ቀጥተኛ መንስኔ ባይኖርም የሚከተሉት ከችግሩ መከሰት ጋር የተዛመዱ ምክንያቶች ናቸዉ፡፡ እነርሱም

ችግሩ በቤተሰብ ዉስጥ ያለ ከሆነ/በዘር የሚወረስ (heredity)
ይህ ለአብዛኛዉ የፀጉር መመለጥ ችግር መከሰት እንደ ምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን ከወንድ ጋር የተያያዘ የፀጉር መመለጥ (male-pattern baldness) ና ከሴቶች ጋር የተያያዘ የፀጉር መመለጥ (female-pattern baldness) ይባላል፡፡ ይህ ለወንዶች የፀጉር መሸሽና ለሴቶች የፀጉር መሳሳት መከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡

· የሆርሞን መለዋወጥ፡- የሆርሞን መለዋወጥና ያለመመጣጠን ጊዜያዊ የሆነ የፀጉር መመለጥ ችግር ሊያስከስት ይችላል፡፡ ይህ በእርግዝና ወቅት፣ ጡት ማጥባት ወቅትና ሴቶች ሲያርጡ ባሉ ሰዓታት ሊሆን ይችላል፡፡ የሆርሞን መጠን መለዋወጥ ለምሳሌ የታይሮይድ ሆርሞን ችግር ለፀጉር መመለጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

· የተወሰነ ቦታ የሚከሰት የፀጉር መመለጥ/Patchy hair loss፡- ይህ አይነቱ የፀጉር መመለጥ ላሽ/ አሎፔሺያ አሬታ የሚባለዉ ሲሆን የሚከሰተዉም የራሳችን የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች የፀጉር ስሮቻችንን በሚያጠቁበት ወቅት ነዉ፡፡ ይህ ቦታዉ ክብ የሆነ ለስላሳና ፀጉር አልባ መላጣ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

· የጭንቅላት ኢንፌክሽን፡- እንደ ጭርት ያሉ እንፌክሽኖች በጭንቅላት ፀጉርና ቆዳ ላይ በመዉጣትና ፀጉር እንዲነቃቀል በማድረግ በተወሰነ ቦታ ላይ ፀጉር እንዲመለጥ ያደርጋሉ፡፡ነገር ግን እንፌክሽኑ በአግባቡ ሲታከም ፀጉሩ ቀስ በቀስ ተመልሶ ይበቅላል፡፡

· ሌሎች የቆዳ ችግሮች፡- ጠባሳን የሚፈጥሩ የፀጉር መመለጥ ችግሮች በጠባሳዉ ቦታ ጭራሹኑ ፀጉር ተመልሶ እንዳይበቅል/ permanent loss/ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ እነዚህም እንደ ላይከን ፕላነስ፣ ሉፑስና ሳርኮይዶሲስ ያሉ የጤና ችግሮች ናቸዉ፡፡

· በተጨማሪም የፀጉር መመለጥ ለካንሰር፣ ለአርትራይትስ፣ ለድብርት፣ ለልብ ችግር፣ ለደም ግፊትና ለወሊድ መከላከያነት በሚወሰዱ መድኃኒቶች ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡

ለፀጉር መመለጥ የሚያጋለወጡ ነገሮች
· በቤተሰብዎ ዉስጥ ችግሩ ካለ
· እድሜ
· ያልተመጣጠነ አመጋገብ/ Poor nutrition
· እንደ ስኳርና ሉፑስ ያሉ የህመም አይነቶች መኖር
· ጭንቀት ናቸዉ፡፡

የፀጉር መመለጥን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የሚከተሉትን ምክሮችን በመተግበር ፀጉርዎን ከመመለጥ ሊያድኑ ይችላሉ፡፡
· የተመጣጠነ አመጋገብ መከትል/የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
· ጥብቅ ሊያድረግዎ የሚችሉ የፀጉር ስታይሎችን ያለመሰራት
· እንደልማድ ፀጉር የማፍተልተል፣ የማሻሸትና የመንቀል ባህሪይ ካለዎ ማስወገድ
· ፀገርዎን በሚያበጥሩበትም ሆነ በሚታጠቡበት ወቅት በቀስታ ቢሆን፡፡ ሰፋ ያለ ማበጠሪያዎችን በመጠቀም የፀጉር መነቃቀልን መከላከል
· ፀጉርዎን በሚሰሩበት ወቅት እንደ ፔስትራ፣ ሆት ኦይል ትሪትመንትና ፐርም የመሳሰሉትን ያለማዘዉተር፡፡

ከ Hello Doctor Ethiopia

 

Spread the love
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.