የጨጓራ መቁሰል

1

የጨጓራ መቁሰል ምንድን ነው?
stoበጨጓራ የውስጠኛው ክፍል እና በትንሹ አንጀት የመጀመሪያው ክፍል (duodenuml) የሚፈጠር ቁስል ነው፡፡ ጨጓራ ከአፍ የሚላክለትን ምግብ ለመፍጨት ሀይድሮክሎሪክ (hydrochloric acid) የሚባል አሲድ ያመነጫል፡፡ ይኼ አሲድ ምግብ ከመፍጨት ባለፈ በጨጓራችን ላይም ጉዳት የማድረስ አቅም አለው፡፡ ከአሲዱ ራሳችንን ከምንጠብቅባቸው መንገዶች መካከል ዋነኛው የጨጓራችንን የላይኛው ክፍል ሸፍኖ የሚገኘው ወፍራም ፈሳሽ (mucus) ነው፡፡ከጨጓራችን ውጭ በቆሽት እና በመጀመሪያው የአንጀት ክፍል የሚመረቱ ሆርሞኖች የአሲዱን አመራረት በመግታት ጨጓራችንን ከአደጋ ይጠብቃሉ፡፡ ስለዚህም የጨጓራ በሽታ የሚከሰተው የነዚህ የሁለቱ ነገሮች ማለትም የአሲድ አመራረት እና ከአሲዱ የሚጠብቁን ነገሮች አለመጣጣም ሲኖር ነው፡፡

የጨጓራ ቁስል እንደማስመለስ ፣ ማቅለሽለሽ እና የሆድ ህመም የመሳሰሉ ምልክቶችን ቢያሳይም አንዳንዴ ግን ምልክት አልባ ሆኖ ለረዥም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ምልክቶቹን በተለያዩ ምግቦች መቆጣጠር ቢቻልም ዶክተር ጋር ሄዶ ትክክለኛው ክትትል መደረግ ግን አለበት፡፡

የጨጓራ ቁስለትን የሚያመጡ ነገሮች ምንድን ናቸው?
የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ (H.pylori) ባክቴሪያ የመጀመሪያው እና ዋናው ለቁስሉ የሚዳርግ ምክንያት ነው፡፡በጤነኛ ሰው ውስጥም የሚገኝ ባክቴሪያ ሲሆን ለዚህ በሽታ ለመጋለጥ ከእሱ በተጨማሪ ሌላ መንስኤዎች አብረውት ሊገኙ ይገባል፡፡ አስፕሪንን የመሳሰሉ የተለያዩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በብዛት መውሰድ የጨጓራን የላይኛው ክፍል በመጉዳት ሊያቆስለው ይችላል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ኢንፌክሽኖች እና ኬሞቴራፒ ሊያመጡት ይችላሉ፡፡

የጨጓራ መቁሰል ምልክቶች ምንድን ናቸው?
የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም አንደኛው ምልክት ነው፡፡ ይህ ህመም ምግብ ከበሉ ከ2-3 ሰአት ባለው ጊዜ የሚብስ እና ትንሽ ሲበሉበት ወይም ደግሞ የአሲድ መከላከያ (anti acid) ሲወሰድ የሚተው አይነት ሊሆን እና በብዛት ከእንቅልፍ ሊቀሰቅስም ይችላል፡፡ የዚህ አይነቱ ህመም በአብዛኛው ከትንሹ አንጀት የመጀመሪያው ክፍል መቁሰል ጋር ይያያዛል፡፡

ሌላኛው ደግሞ ምግብ ሲበላ የሚብስ አይነት ህመም ሲሆን ይሄኛው ከጨጓራ መቁሰል ጋር ይያያዛል፡፡ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ቶሎ መጥገብ፣ የሆድ መነፋት የመሳሰሉ ምልክቶችም አሉት፡፡ እነዚህ ምልክቶች ሁሉም የጨጓራ ቁስል ምልክቶች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ በሽታም ምልክቶች ናቸው፡፡ በሽታው ኖሮባችው ምንም ምልክት የማይታይባቸው እና ህይወታቸውን በደህና የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎችም አሉ፡፡

በጨጓራችን የሚመረተው አሲድ በጨጓራ ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ የደም ስሮችን ሊጎዳና ሊያደማቸው እና ደም እንዲያስመልስ ሊያደርግ ይችላል፡፡ከጨጓራ የወጣው ደም በትለቁ እና በትንሹ አንጀት አልፎ በጣም ጥቁር እና የሚያጣብቅ አይነት ሰገራ ሆኖ ሊወጣም ይችላል፡፡ እነዚህ ምልክቶች ካሉ በሽታው ላቅ እንዳለ ስለሚየሳይ ወዲያው ወደሆስፒታል መሄድ አለብህ፡፡

የጨጓራ ቁስል ሊደማ፣ ጨጓራን አልፎ ቆሽትን ወደመሳሰሉ አካላቶች ሊሄድ፣ ጨጓራን ሊቀድ እና አሲዱን ወደተለያዩ የሆድ አካላት ሊያፈስ እንዲሁም ከጨጓራ ወደ ትንሹ አንጀት የሚተላለፈውን ቱቦ በማጥበብ ጨጓራን ከትንሽዋ አንጀት ጋር የሚያገናኘውን ክፍል ሊዘጋ ይችላል፡፡የጨጓራ ቁስል ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳዩ የተለያዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እነዚህም፤

ድንገት የተነሳ በጣም ሀይለኛ የሆድ ህመም
ጥቁር እና የሚያጣብቅ ሰገራ
ማቅለሽለሽ እና ደም የቀላቀለ ትውከት
ድሮ በምግብ የሚተው ህመም አሁን በምግብ አልተውም ማለት የመሳሰሉትን መጥቀስ እንችላለን፡፡ እነዚህ ምልክቶች ካሉብህ ወደሆስፒታል መሄድን የመጀመሪያ ስራህ አድርገው፡፡
የጨጓራ ቁስል ምርመራ ምንድን ነው?
ሆስፒታል ከሄድክ በኋላ የተለያዩ ምርመራዎች ይታዘዙልሃል፡፡ የተለያዩ የደም ምርመራዎች ይደረጉልሃል፡፡ በተጨማሪም ‹Gastroscopy› ሊሰራልህ ይችላል፡፡ በትንሽ ካሜራ የጨጓራህን ውስጥ በማየት ቁስል እንዳለብህ ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ይህ ካሜራ በአፍህ በኩል የሚገባ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት አያስከትልም፡፡ በዚህ አይነት ቁስሉ እንዳለብህ ሲረጋገጥ እና የትኛውን አይነት መድሃኒት መጠቀም እንዳለብህ ይታወቃል፡፡

የጨጓራ ቁስል ካለብኝ ምን ማድረግ አለብኝ?
ከላይ የተጠቀሱ የበሽታው ምልክቶችን ስታይ ሁልግዜም አስቀድመህ ዶክተርህን ማማከር አለብህ፡፡ አሲድ የሚቀንሱ እና ባክቴሪያውን የሚገድሉ መድሃኒቶች ባንድ ላይ ሊታዘዝልህ ይችላል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የማሻል አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ በሽታ ከተያዝክ አስፕሪን እና ዲክሎፌናክን የመሳሰሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ የለብህም፡፡ እነዚህን መድሃኒቶች መውሰድ ካለብህ ደግሞ በቅድሚያ ዶክተርህን አማክር፡፡በቁስሉ ምክንያት ጨጓራው ከተቀደደ ኦፐሬሽን መሰራት ሊኖርብህም ይችላል፡፡

እንደወተት፣ የበሰሉ ምግቦች እና ሾርባ የመሳሰሉ ምግቦች ህመሙን ጋብ በማድረግ ሊረዱህ ይችላሉ፡፡

የጨጓራ መቆጣት (Gastritis)
የጨጓራ መቆጣት ምንድን ነው?
ይህ በሽታ በሚያቃጥሉ ምግቦች፣ ጨው፣ የተጠበሱ ምግቦች፣ ቡና፣ ጭንቀት፣ አልኮል፣ ሲጋራ፣ አንዳንድ መድሃኒቶች በተለይ የህመም ማስታገሻዎችን በመሳሰሉ የተለያዩ ምክንያቶች የሚመጣ ሲሆን ጨጓራን ያጠቃል፡፡ ሁሉም ሰዎች የተለያዩ የበሽታው ምልክቶችን የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የማቃጠል ስሜት፣ ቶሎ የመጥገብ፣ የሆድ መነፋት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማግሳትን ያጠቃልላል፡፡ በብዛት ይኼ ነው የሚባል መነሻ ምክንያት የሌለው ሲሆን ከአንድ ምክንያት ይልቅ በብዙ እና ተደራራቢ ምክንያቶች ይመጣል፡፡በሚኖራቸው የጊዜ ቆይታ ጋስትራይተስ በሁለት አይነት ይከፈላል፡፡ በአጭር ጊዜ የሚከሰተው ከኢንፌክሽኖች ጋር ይያያዛል፡፡ ሌላኛው አይነት እና ረዘም ላለጊዜ የሚቆይ እና ከሁለቱ ውጪ የሆኑና ብዙም የማይታዩ አይነቶችም አለው፡፡

ከ50 አመት በላይ ከሆንክ፣ አዳዲስ ምልክቶች እያየህ ከሆነ፣ መዋጥ ካስቸገረህ እና ክብደት ከቀነስክ በቶሎ ወደሆስፒታል ሄደህ ተመርመር፡፡

እራሴን እንዴት ልንከባከብ?
ዋናው ነገር በሽታውን ከሚያባብሱብህ ነገሮች እራህን መቆጠብ ነው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ ሁሌም በአንድ አይነት ሰአት ተመገብ፡፡አልኮል እና ሲጋራን አቁም፡፡ ልክ ህመሙ ሲጀምርህ ትንሽ ነገር ብላበት፡፡ ጨጓራህ የለመደውን ምግብ የመፍጨት ስራውን ስትሰጠው ይረጋጋል፡፡

Spread the love
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.