የዛሬዉ ርዕሳችን ፎሮፎርን በተመለከተ ይሆናል እነሆ፡፡

ፎሮፎር እጅግ በጣም የተለመደ የፀጉር ቆዳ ችግር ነው፡፡ በፀጉር ቆዳ ላይ የሚታይ ነጭ የተፋቀ የሞተ ቆዳ ፎሮፎር ሲሆን አልፎ አልፎም የማሳከክ ሁኔታ ሊኖረው ይችላል፡፡

✔ ፎሮፎርን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች

11165298_1580709068869623_2707125790487872622_n• ደረቅ ቆዳ፡- በቆዳ መድረቅ ምክንያት የሚመጣ ከፀጉር ቆዳ በተጨማሪ በእጅ እና በእግር ቆዳዎች ላይም ይታያል፡፡
• ቅባታማ የቆዳ መቆጣት ፡- የቆዳ መቅላት፣ቅባታማ ቆዳ በነጭ እና ቢጫ ቅርፊት መሳይም ነገርም በፀጉር ቆዳ ላይ ይታያል፡፡ ይህ ዓይነቱ የፎሮፎር ዓይነት በቅንድብ እና በጆሮ ጀርባ ላይም ይገኛል፡፡

• የፀጉር ንፅሕና ማጣት፡- ፀጉርዎን በመደበኛ ሁኔታ የማይታጠቡ ከሆነ ለፎሮፎር ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡
• ፈንገስ ፡- በፈንገስ ምክንያት የሚመጣ የፎሮፎር ዓይነትም ያለ ሲሆን አንዳንዶች ለቆዳቸው ተስማሚ ያልሆኑ የፀጉር መዋቢያዎችን በመጠቀም ምክንያት ይከሰትባቸዋል፡፡

✔ ለፎሮፎር ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች

• ዕድሜ፡-በአብዛኛው በልጆችና በወጣቶች ላይ ይታያል፡፡
• ፆታ፡- አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ባህርይ አለው፡፡
• ተጓዳኝ በሽታዎች መኖር ናቸዉ፡፡

✔ፎሮፎርን ለመከላከል

• በመደበኛ ሁኔታ የፀጉር ንፅሕና መጠበቅ
• ለፀጉርዎ የሚጠቀሙትን መዋቢያዎች መቀነስ

ፎሮፎር በአብዛኛው ንፅሕናን በመጠበቅ እና አመጋገብን በማስተከካል የሚድን ሲሆን ችግሩ ለሳምንታት የሚቆይ፣የሚያሳክክ እና በፀረ ፎሮፎር የማይታገስ ከሆነ ወደ ሐኪም በመሄድ ሕክምና ማግኘት ተገቢ ነው፡፡ ሕክምናውንም በሐኪምዎ ትዕዛዝ መሠረት በመጠቀም ከፎሮፎር ነፃ መሆን ይችላሉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.