የመገጣጠሚያ ሕመምመገጣጠሚያዎ ላይ ሕመም ይሰማዎታል? ምን እንደሆነስ ያውቃሉ?
ይህ የመገጣጠሚያ ሕመም በአገራችን የብዙ ሰዎች ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡

የመገጣጠሚያ ሕመም በሕክምናው ቋንቋ አርተራይተስ (Arthritis) የምንለው ሲሆን የሚከሰትባቸው ምክንያቶች ደግሞ የተለያዩ ናቸው፡፡

የተለመደው የሕመም ዓይነት በዕድሜ ወይንም በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰተው የመገጣጠሚያ ሕመም ሲሆን ሌሎች የመገጣጠሚያ ሕመም ዓይነቶችም በሰውነታችን በሚከሰቱ አለርጂ (Autoimmune Related) ምክንያት ያመጣሉ፡፡
እነዚህም፡-
• ሮማተቶይድ አርተራይተስ (Rheumatoid Arthritis )
• ሶሪያቲክ አርተራይተስ (Psoritic arthritis) በመባል ይታወቃሉ፡፡

የመገጣጠሚያ ሕመም ያላቸው ሰዎች በተጠቃው መገጣጠሚያ ላይ ከፍተኛ የሕመምስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው በመገጣጠሚያው አካባቢ ባሉ ጡንቻዎች መቆጣት ምክንያት ነው፡፡

የመገጣጠሚያ ሕመም ምልክቶች
በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰትን የመገጣጠሚያ ሕመም ምልክቶች
• ትኩሳት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ላይ ሕመም (ውጋት)

በአለርጂ ምክንያት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ሕመም
• የመገጣጠሚያ ላይ ሕመም ከእብጠት ጋር
• በጣት፤በእጅ እና በእግር መገጣጠሚያዎች ላይ
• ሕመሙ በድንገት የሚከሰትና ምክንያቱ ያልታወቀ ከሆነ
• ሕመሙ ከትኩሳት ጋር የተያያዘ ከሆነ
• ከፍተኛ ሕመምና መገጣጠሚያ አካባቢ ላይ መውላት ካለ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና
ማዕከል መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡

ሕመምዎን ለማስታገስ
– አቀማመጥዎን መቀያየር
– በአንድ መገጣጠሚያ ላይ ብቻ ጫና አለማብዛት
– በየግማሽ ሰዓት ተነስቶ መራመድ
ከዚህ በተጨማሪ
– ክብደትዎን ማስተካከል
– ሲጋራ የሚያጤሱ ከሆነ ማቆም
– ቀላል እንቅስቃሴን ማድረግ የመገጣጠሚያ ሕመም እንዲቀንስ ያደርጋል

የመገጣጠሚያ ሕመም ካለብዎ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነገሮች ባያደርጉ ይመከራል
– መሮጥ
– መዝለል
– ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ አካል ብቃት እንቅስቃሴ

የመገጣጠሚያ ሕምዎን በተመለከተ ከሐኪምዎ ጋር መመካከር እና ያለብዎትን የመገጣጠሚያ ሕመም ዓይነት ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን መዘንጋት የለቦትም፡፡

ጤና ይስጥልኝ

(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.