አባት እና ልጅአባት: ከኔና ከእናትህ የምትወደው ማንን ነው?
ልጅ: ሁለታችሁንም
አባት: የበለጠ የምትወደው?
ልጅ: ሁለታችሁንም
አባት: አንተ አንዱን ተናገር?
ልጅ: ሁለታችሁንም
አባት: እሺ እኔ ባህርዳር ብሄድ እናትህ ደግሞ ሀዋሳ ብትሄድ
ወዴት ትሄዳለህ?
ልጅ: ሀዋሳ
አባት: አሀ. . .እናትህን ነው የበለጠ የምትወደው ማለት ነው
ልጅ: አደለም ሀዋሳ ስለምትመቸኝ ነው
አባት: እሺ እኔ ሀዋሳ ብሄድ እናትህ ደግሞ ባህርዳር ብትሄድ የት
ትሄዳለህ?
ልጅ: ባህርዳር
አባት: ለምን?
ልጅ: ሀዋሳ ሄጄ ነበራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.