የማስታወስ ችሎታዎን ለማሻሻል የሚመከሩ 7 ምክሮች

1

17428_476449622519263_2171741067179038545_nየማስታወስ ችሎታ እንዳይቀንስ ለመከላከል የሚረዳ ይህ ነዉ የሚባል አስተማማኝ መንገድ ባይኖርም የሚከተሉትን መንገዶች ቢተገብሩ የማስታወስ ችሎታዎን ለመጠበቅና ለማሻሻል ሊረዳዎ ይችላል፡፡

ንቁ አዕምሮ እንዲኖርዎ ማድረግ፡- ልክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰዉነትዎን ቅርፅ ለመጠበቅ እንደሚረዳዎ ሁሉ አዕምሮዎን ሊያነቃቁ የሚችሉ ድርጊቶች/ባህሪያት ማከናወን አዕምሮዎ ንቁ ሁኖ እንዲቆይ ሊደርግዎ ይችላል፡፡

ከሰዎች ጋር ያለዎ ተግባቦት በመደበኛ ሁኔታ እንዲኖርዎ ማድረግ፡- የማስታወስ ችሎታዎን ሊቀንሱ የሚችሉ እንደ ጭንቀትና ድብርት ያሉ ሁኔታዎችን ለመመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች አንዱ እለት ከእለት ከሰዎች ጋር ያለዎ ግንኙነት ነዉ፡፡ ስለሆነም በተለይ ብቻዎን የሚኖሩ ከሆነ በተቻለዎ መጠን ከሚወዱት ጋር፣ ከጓደኞችዎ ወይም ከሌሎች ጋር ሊያገናኝዎ የሚችሉ እድሎችን መፈለግና መጠቀም፣ የተለያዩ ግብዣዎች ( ምግብ አብሮ መመገብ፣ ሲኒማ መግባትም) ላይም ይሁን ሌሎች ሁነቶችም ካሉ መሄድ/መካፈል

እራስን አስቀድሞ ማዘጋጀት/ Get organized፡- የሚኖሩበት ቤትዎ ወይም የሚይዙት ማስታወሻ የተተራመሰ/የተዘበራረቀ ከሆነ ነገሮችን በቀላሉ እንዲረሱ ያደርግዎታል፡፡ ስለሆንም የሚሰሩ ስራዎች ፣ ቀጠሮም ይሁን ሌሎች ጉዳዮች ካሉ ለየት ባለ ማስታወሻ ደብትር፣ ካላንደር ወይም ኤልክትሮኒክ ማስታወሻ መያዣ ላይ መያዝ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ የመዘገቡትን ነገሮች ደጋግመው ማለት፡፡ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ነገሮችን በየግዜዉ መለየት፡፡ የኪስ ቦርሳዎን፣ ቁልፎችንና ሌሎች ጠቃሚ ነገሮችን የሚስቀምጡበት የተወሰነ ቦታ ይኑርዎ፡፡ በቀላሉ በነገሮች መረበሽን/ መወሰድን መቀነስ፣ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን ያለማከናወን፡፡ ሊረሱት የማይፈልጉትን ነገር ከሌላ ከሚወዱት ነገሮች ጋር አዛምዶ መያዝ፡፡

በደንብ መተኛት፡- አንቅልፍ መተኛት ነገሮችን በደንብ ለማስታወስ እንዲችሉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም መልካምና በቂ እንቅልፍ እንዲኖርዎ ያድርጉ

ጤናማ አመጋገብ እንዲኖርዎ ማድረግ፡- ጤናማ አመጋገብ መኖር ለአዕምሮ መልካም ነገር ነዉ፡፡ ስለሆነም ጥራጥሬ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ማዘዉተር፡፡ ምርጫዎ ብዙ ስብነት የሌላቸዉ የፕሮቲን ምንጭ የሆኑ እንደ አሳ፣ ቀይ ስጋ እና ዶሮ ይሁን፡፡ የሚጠጡትም ነገሮች ወሳኞች ናቸዉ፡፡ በቂ ዉሃ ካላገኙ ወይም አልኮሆል በብዛት ከወሰዱ ለግራ መጋባትና ለመርሳት/የማስታወስ ችሎታ መቀነስ መከሰት ይዳረጋሉ፡፡ ስለሆነም በቂ ዉሃ መዉሰድና አልኮልን መቀነስ የመስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ይረዳዎታል፡፡

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከል፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የደም ዝዉዉር አዕምሮዎን ጨምሮ ወደሌሎች የሰዉነት ክፍሎች እንዲሰራጭ ያደርጋል፡፡ ይህ የማስታወስ ችሎታዎ እንዲዳብር ያደርጋል፡፡ ሙሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ካልቻሉ እንኳ ቢያንስ ለ10 ደቂቃዎች ወክ ማድረግ መልመድ ያስፈልጋል፡፡

ለረጅም ጊዜ የቆዩ ችግሮች ካለዎ መፍትሄ እንዲኖረዉ ማድረግ፡- ለረጅም ጊዜ የቆዩ እንደ ድብርት፣ የኩላሊትም ይሁን የታይሮይድ ዕጢ ችግሮች ካለዎ የህክምና ባለሙያዎ ዘንድ ክትትል በማድረግ ህክምና ማግኘት፡፡ በተሻለ ሁኔታ ለራስዎ እንክብካቤ ማድረግ የማስታወስ ችሎታዎ እንዲሻሻል ያግዝዎታል፡፡ በተጨማሪም የሚወስዱዋቸዉ መድሃኒቶች የማስታወስ ችሎታዎን ሊቀንሱ ስለሚችሉ መደበኛ በሆነ መንገድ የሚወስዱዋቸዉን መድሃኒቶች ከህክምና ባለሙዎ ጋ በመነጋገር ክትትል ማድረግ፡፡

የህክምና ባለሙያ ማየት የሚጠበቅብዎ መቼ ነዉ?
የማስታወስ ችሎታዎን በሚመለከት ስጋት ካለዎ፡- በተለይ የማስታወስ ችሎታዎ መቀነስ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ላይ ጫና ከፈጠረ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ የህክምና ባለሙያዎ አስፈላጊዉን የአካልና የማስታስ ችሎታ መርመራ ካደረገልዎ በኃላ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጨማሪ ምርመራዎችን ያደርግልዎታል፡፡
ለማስታወስ ችሎታ መቀነስ የሚደረጉ ህክምናዎች ይህንን ችግር እንዳመጣብዎ ሁኔታ ይለያያሉ፡፡

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.