የሴቶች ብልት ፈሳሽ አለ የሚባለዉ ከሴት ብልት ፈሳሽና ህዋሳት/ሴሎች ተደባልቀዉ ተከታታይነት ባለዉ መልኩ መፍሰስ ሲኖር ነዉ፡፡ የብልት ፈሳሽ መኖር ብልትን ለማፅዳትና ለመከላከል ያገለግላል:: አንዲት ሴት በወር አበባ ዑደቶቿ መሃከል መልኩና መጠኑ የተለያየ የፈሳሽ አይነት ሊኖር የሚችል ሲሆን ይህም ሊያጣብቅ ከሚችል ነጭ ፈሳሽ አንስቶ እስከ ንፁህ ሆኖ ዉሃማ ፈሳሽ አይነት ሊለያይ ይችላል፡፡ የተወሰነ የብልት ፈሳሽ መኖር ምንም ችግር የሌለዉና ኖርማል ነዉ፡፡ ነገር ግን የብልት ፈሳሽዎ ያልተለመደ ሽታ ካመጣ፣ መልኩን ከቀየረ አልያም ተያያዥነት ያለዉ ህመምና ማሳከክ ካለዉ የሆነ ችግር እንዳለ ማሳያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

ለብልት ፈሳሽ መከሰት ምክንያቶች

· ፈንገስ፣ ባክቴሪል ቫጂኖሲስ (የሴት ብልት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ ባክቴርያዎች መዛባት) እና ሴቶች ባረጡበት ወቅት የሚያሳዩት ምልክቶች ለብዙ ሴቶች የተዛባ የብልት ፈሳሽ መከሰት ምክንያት ሲሆኑ እነዚህ ምክንያቶች በተወሰነ መልኩ ጉዳት ባያስከትሉም ምቾት ላይሰጡ ግን ይችላሉ፡፡

· የተዛባ/ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ የተወሰኑ የአባለ ዘር በሽታዎች ሲኖሩም ሊመጣ ይችላል፡፡ የአባለዘር በሽታዎች ወደ የፍቅር/የትዳር ጓደኛዎ ሊተላለፉ አሊያም ወደ ማህፀን፣ እንቁልጢና የዘር መተላለፊያ ቱቡ ሊሰራጩ ስለሚችሉ በጊዜዉ ተመርምረዉ ህክምና ማግኘት አስፈላጊ ነገር ነዉ፡፡

· አንዳንዴ ፈሳሹ ቡናማ ወይም ደም የተቀላቀለበት ከሆነ የማህፀን አንገት ካንሰር ምልክትም ሊሆን ይችላል፡፡

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
· ቢጫ፣ አረንጓዴ ወይም ወፍራም አይብ የመሰለ ፈሳሽ ካለዎ
· ሽታ ያለዉ ፈሳሽ ከሆነ
· የመቅላት፣ የማሳከክ፣ የማቃጠል ወይም መቆጥቆጥ ስሜቶች በብልትዎ፣ በብልትዎ ዙሪያ ባለዉ ቆዳና በሽንት መዉጫ ቀዳዳ ዙሪያ ካለዎ
· ከወር አበባዎ ዑደት ጋር ያልተገናኘ ወይም ያልተዛመደ በብልትዎ ደም ወይም የደም ጠብታዎች ካለዎ

ህክምና እስኪገኙ ድረስ ሊተገብሩዋቸዉ የሚችሉት ነገሮች
· ከፈንገስ ጋር የተያያዘ ከሆነ በብልትዎ ሊገቡ የሚችሉ የፈንገስ መድሃኒቶችን መጠቀም
· ማሳከክ፣ ህመምም ይሁን ምቾት የሌለው ስሜት ካለዎ በበረዶ ወይም ዉሃ ዉስጥ በተነከረ ንፁህ ጨርቅ ቦታዉ ላይ መያዝ
· ህክምና እስኪገኙ ድረስም ይሁን ህክምና ከጀመሩ በኃላ ለመጀመሪያዉ ሳምንት የግብረስጋ ግንኙነት ሲያደርጉ ኮንደምን መጠቀም የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

11084055_467780246719534_7803437194143148560_o

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.