የሰውነት ብቃት እንቅስቃሴ ላረጡ ሴቶች፣ ጥቅሞቹ እና ጥቆማዎች

 

ማረጥ (menopause) ማለት አንዲት ሴት የመጨረሻዉን የወር አበባ ዑደት ካየች በኃላ ለ12 ተከታታይ ወራት የወር አበባ ዑደት ያላየች ከሆነ ሲሆን ይህ ሁኔታ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ሴቶች በ40ዎቹና በ50ዎቹ የዕድሜ ክልል ሲደርሱ ነዉ፡፡ ሴቶች በሚያርጡበት ወቅት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ብዙ ጥቅም አለው:: ይህን ማድረግ ሊኖረዉ ከሚችለዉ ጥቅሞች ዉስጥ፡-
· ክብደት እንዳይጨምሩ ይከላከላል፡- ሴቶች በሚየርጡበት ወቅት የሰዉነት ጡንቻዎቻቸዉ መጠን እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን በተቃራኒዉ ስብ በሆዳቸዉ ላይ እየተጠራቀመ ይመጣል (ቦርጭ እየጨመረ ይመጣል)፡፡ በዚህን ወቅት ትንሽ እንኳ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ/ቢጨምሩ የሰዉነት ክብደትዎ እንዳይጨምር ያደርጋሉ፡፡
· የጡት ካንሰርን መቀነስ ይችላሉ፡- ሴቶች በሚያርጡበትም ይሁን ካረጡ በኃላ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቢያዘወትሩ ከመጠን ያለፈ ክብደትን ለመቀነስ ወይም ጤናማ ክብደት ካላቸዉ ባለበት እንዲቆይ ያደርጋል። ይህ ደግሞ የጡት ካንሰር የመከሰት እድሉን ለመቀነስ ያግዛል።
· አጥንትዎን ለማጠንከር ይችላሉ፡- ሴቶች በሚያርጡበት ወቅት ሊከሰቱ ከሚችሉ የጤና ችግሮች ዉስጥ አንዱ የአጥንት መሳሳትና ስብራት ሲሆን ይህን ለመከላከል / ለመቀነስና የአጥንትዎን ጥንካሬ ለመጠበቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘዉተር ያስፈልጋል፡፡
· ለሌሎች ህመሞች ያለዎን ተጋላጭነት ይቀንሳሉ፡- ከማረጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉ የክብደት መጨመር የስኳር ህመምን ጨምሮ ለተለያዩ አሳሳቢ ለሆኑ የጤና ችግሮች ሊዳርግዎ ስለሚችል መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ይህንን ተጋላጭነትዎን እንዲቀንሱ ይረዳዎታል፡፡
· ስሜትዎን ከፍ ለማድረግ/ ለመገንባት ይረዳዎታል፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ስነልቦናዊ ጤንነትዎን በየትኛዉም ጊዜ ለማሻሻል / ከፍ ለማድረግ ይረዳዎታል / ያግዝዎታል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዴት ከማረጥ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ችግሮች ለመቀነስ ይረዳዎታል?ለብዙ ሴቶች መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያርጡበት ወቅትና ካረጡ በኃላ ማድረግ ጭንቀትን ለመቀነስና ጥራት ያለዉ ኑሮ ለመኖር ያግዛቸዋል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሰዉነት ወበቅ/ሙቀት እና የእንቅልፍ መዛባትን ለመቀነስ የተረጋገጠ መንገድ ባይሆንም ሊረዳ ይችላል።

በሚርጡበት ወቅት የሚደረጉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ግብ

ለብዙ ጤናማ ሴቶች በሚያርጡበት ወቅት ሊያደርጉዋቸዉ ከሚችሉት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ኤሮቢክስና የጤንካሬ ትሬይንግ የሚመደቡ ሲሆን
መካከለኛ ኤሮቢክስ እንቅስቀሴ የሚያደርጉ ከሆነ በሳምንት ለ150 ደቂቃዎች በቂ ሲሆን ጠንከር ያለ ኤሮቢክስ ከሆነ ደግሞ በሳምንት ለ75 ደቂቃዎች በቂ ይሆናል። በሃገራችን የቴሌቪዥን ጣብያዎች የሚተላለፉ የኤሮቢክ ስስልጠናዎችን መከታተል በጣም ቀላሉ ዘዴ ነው።
በሃገራችን ብዙ ባይለመድም የሚሰሩት የጥንካሬ ትሬይንግ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት ሁለቴ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡

ሊሞክሩዋቸዉ የሚችሉዋቸዉ ምርጥ እንቅስቃሴዎች

· የኤሮቢክስ እንቅስቃሴ፡- ኤሮቢክስ እንቅስቃሴ ለብዙዎቹ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የመሰረት ድንጋይ ነዉ፡፡ ሰለሆነም ወክ ማድረግ፣መዋኘትና የዉሃ ዉስጥ ኤሮቢክሶች ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም ማንኛዉም እንቅስቃሴ ሆኖ ትላልቅ የሰዉነት ጡንቻዎችን የሚጠቀምና የልብ ትርታዎን የሚጨምሩ እንቅስቃሴዎች በዚህን ወቅት ይመከራሉ፡፡
የጥንካሬ ትሬይንግ (ክብደት በማንሳት ጡንቻን ማዳበር)፡- መደበኛ የሆነ የጥንካሬ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የሰዉነት ካሎሪን ለማቃጠል፣ ስብን ለመቀነስና ጡንቻዎችን ለማጠንከር ይረዳል፡፡
የመወጠር ትሬይንግ/ስትሬቺንግ ፡- የመወጣጠር ትሬይንግ የመተጣጠፍ ብቃትዎን ይጨምራል

ማስታወስ የሚገባዎ ነገር ቢኖር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማካሄድ የግድ ወደ ጅም መሄድ እንደማይገባዎ ነዉ፡፡ ጤናዎትን ሊያሻሽሉ የሚችሉ እንደ ዳንስ፣ ከበድ ያሉ ስራዎችና የጓሮ አትከልትን ለመንከባከብ መትጋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎን ያግዛሉ። እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሁል ግዜ መጀመሪያ ማሟሟቅ እና ሲጨርሱ ግዜ ወስደው ሰውነቶን ማቀዝቀዝ አይዘንጉ።

11042677_459167440914148_3722697374696257741_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.