ይህ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ/ ክሮኒክ ችግር ሲሆን ሰዎች ከአንድ የሰዉነት ክፍል በላይ አካላዊ የህመም ስሜት ኖሮዋቸዉ በአካላዊ ምርመራ ወቅት ለህመሙ መከሰት ምንም አካላዊ ምክንያት ካልተገኘ ነዉ፡፡ ሰዎች የሚሰማቸዉ ህመምና የሚያሳዩት ሌሎች ምልክቶች ሰዎቹ ሆን ብለዉ ያልፈጠሩትና ትክክለኛ ምልክቶች ቢሆኑም በአካላዊ ምርመራ ግን ምንም የሚገኝ ነገር የለም፡፡

የህመሙ ምክንያቶች
ይህ ችግር ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ዕድሜያቸዉ ከ30 ዓመታት በላይ በሆኑት ሰዎች ላይ ሲሆን ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ ይበዛል፡፡
ሶማቲክ ሲምፕተም ዲስኦርደር ያላቸዉ ሰዎች የህመም ስሜታቸዉ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን በህመሙ ላይ መጨነቅ ከተጨመረ የማይሰበር የህመም አዙሪት/ cycle ዉስጥ ይከታቸዋል፡፡
ምንም እንኳ ሁሌም በደል የደረሰባቸዉ ሰዎች ይህ የጤና ችግር ባይከሰትባቸዉም ከዚህ በፊት አካላዊና ፆታዊ ጥቃት/በደል የደረሰባቸዉ ሰዎች ከሌሎቹ አንፃር ሲታዩ ችግሩ በብዛት ሊከሰትባቸዉ ይችላል፡፡
አጥኚዎች የአዕምሮንና የሰዉነት ግንኙነትን በሚያጠኑበት ወቅት የስሜትዎ ደህንነት ሰዎች ህመምንና ሌሎች ምልክቶችን እንዴት እንደሚረዱት ሊወስን እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

ምልክቶች
ይህ ችግር ያለባቸዉ ሰዎች ለአመታት በተለያዩ አካላዊ ቦታዎች ላይ የህመም ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ህመሙ ለረጅም ጊዜ የቆየ/ክሮኒክ ሲሆን የአንጀት ግፍሎች፣ የነርቭና የመራቢያ አካላት ህመሞች/ችግሮች ይበዛሉ፡፡
ብዙዉን ጊዜ ህመሙ የቀን ተቀን ስራዎትንና ግንኙነትዎን ከማወኩም በላይ የተለያዩ የጤና ድርጅቶችን/ባለሙያዎችን እንዲጎበኙ ያደርጎታል፡፡ ጭንቀት ካለ ደግሞ ችግሩ እንዲባባስ ያደርጋል፡፡
ከብዙ ጥቂቶቹ አካላዊ ህመሞች/ somatization disorder ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
• የሆድ ህመም
• የመርሳት ችግር
• የጀርባ ህመም
• የሆድ መነፋት
• የደረት ህመም
• ተቅማጥ
• የመዋጥ ችግር
• መደበት
• የራስ ምታት
• ስንፈተ ወሲብ
• የመገጣጠሚያ ላይ ህመም
• ማቅለሽለሽና አንዳንዴ ማስታወክ
• በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም መኖር
• ሽንት ሲሸኑ ህመም መከሰት
• በእግርዎና እጅዎ ላይ ህመም መኖር
• የልብ ትርታ
• የትንፋሽ ማጠር ናቸዉ

ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች
ሙሉ አካላዊና የላቦራቶር ምርመራ በማድረግ አካላዊ ምክንያቶችን መፈለግ ያስፈልጋል፡፡ የሚደረጉት ምርመራዎች እንደ ህመሙ ምልክቶች ይለያያል፡፡ተያያዥ ችግሮች መኖር ያለመኖራቸዉን ለማወቅ የስነልቦና/የስነአዕምሮ ምርመራ ይደረጋል፡፡ ሙሉ ምርመራ አድርገዉ ለችግሩ ምንም አካላዊ ምክንያት ካልተገኘ ሶማቲክ ሲምፕተም ዲስኦርደር እንደላለዎ ይታወቃል ማለት ነዉ፡፡

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
የህክምናዎ ዋና አላማ ህመምዎን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ መረዳት ነዉ፡፡
ከጤና ባለሙያዎ ጋር ሊረዳዎ የሚችል ግንኙነት መፍጠር የህክምናዎ ዋና አካል ነዉ፡፡ ስለሆነም
• በጣም የበዛና የተደጋገመ ምርመራ እንዳያደርጉ ህክምናዎን ከአንድ ሀኪም ጋር ማድረግ/መቀጠል
• ስለህመምዎ ምልክቶችና እንዴት እየተቋቋሙት እንደሆነ ለመወያየት ከሀኪምዎ ጋር መደበኛ ክትትል ማድረግ
• ለህክምና ባለሙያዎ እስከዛሬ ድረስ ሲወስዱ የነበሩትን የህመም ማስታገሻዎች ማሳየት፡፡
• ህመምዎን ምን ምን ነገሮች እንደሚያባብሱት መለየት
• ምልክቶቹን ወይም ህመሙን እንዴት እንደሚssሟቸዉ ዘዴዎችን ማወቅ/መፈለግ
• ህመም እየተሰማዎ ባለበትም ጊዜ እንኳ ቢሆን ንቁ ለመሆን መሞከር

10458890_492401784257380_1009154486895602314_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.