· ከምግብ በኃላ ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ ከምግብ ጋር ባይያያዝም ጠዋትም ይሁን ማታ ማጨስ ለጤና ጠንቅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሲጋራ ኒኮቲንና ታር የመሳሰሉትን ጨምሮ ከ60 በላይ የሆኑ ለጤና ጎጂና ካንሰርን ሊያመጡ የሚችሉ ኬሚካሎች ያሉት ሲሆን ማጨስ አንጀት ላይ እንደ ኢሪተብል ባወል ሲንድረምንና አልስሬቲቭ ኮላይተስ የሚባሉ ህመሞችን እንዲባባሱ ከማድረጉም በላይ በትልቁ አንጀት ጡንቻዎች ላይ የሚያመጣዉ ችግር አለ፡፡

· ምግብ ከተመገቡ በኃላ ወዲያዉኑ ፍራፍሬዎችን መመገብ፡- ፍራፍሬን ከምግብ በኃላ መመገብ ሁሉም ሰዉ የሚመክረዉ ነገር ነዉ፡፡ይሁንና ፍራፍሬዎችን ከምግብ ጋር መመገብ ፍራፍሬዎቸቹ ከሌሎች የምግብ አይነቶች ጋር በጨጓራ ዉስጥ እንዲቆዩ/እንዲታገዱ ስለሚያደርግ ትንሹ አንጀት ጋ በሰዓቱ እንዳይደርሱ ያደርጋል፡፡ፍራፍሬዎች በቀላሉ በአንጀታችን የሚፈጩና ቀላል የስኳር አይነት የያዙ ስለሆነ እንዲመገቡ የሚመከረዉ ምግብ ከተመገቡ ከአንድ ሰዓት በኃላ ወይም ምግብ ከመመገብዎ አስቀድሞ ቢቻል ጠዋት በባዶ ሆድ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ሰዉነታችን ከፍራፍሬዎች የሚያገኘዉን ንጥረ ነገሮች በደንብ መጠቀምና ሀይል ማግኘት የሚችለዉ ጠዋት ላይ ስንመገባቸዉ ነዉ፡፡

· ሻይና ቡና ከምግብ በኃላ መጠጣት፡- በብዙ የምግብ ባለሙያዎች የሚመከረዉ ሻይና ቡናን ከምግብ በኃላ ያለመጠቀም ሲሆን ይህ ምክንያቱ እነዚህ ፈሳሾች በዉስጣቸዉ ፖሊፌኖልና ታኒስ የሚባሉና በምግብ ዉስጥ ካለዉ የብረት ማዕድን ጋር ዉህደትን ስለሚፈጥሩ የብረት ማዕድን ወደ ሰዉነታችን እንዳይመጠጥ ያደርጋሉ፡፡ ይህ በተለይ ለህፀናትና የብረት ባዕድን ዕጥረት ባላቸዉና የብረት ማዕድን ለሚያስፈልጋቸዉ ሴቶች ላይ ችግሩ ሊጨምር ስለሚችል ሻይና ቡናን ምግብ ከተመገቡ ከ 1 ሰዓት በኃላ ቢጠጡ ይመረጣል፡፡

· ምግብ ከተመገቡ በኃላ ሻወር መዉሰድ፡-ምግብ ለመፈጨት ብዙ ሃይል ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ጥሩ የሆነ የደም ዝዉዉወር ወደ አንጀት እንዲሄድ የሚፈለግ ሲሆን ምግብ ተመግበን ሻወር በምንወስድበት ወቅት ግን የሰዉነትን ሙቀት ለመጠበቅ ሰዉነታችን ብዙ ደም ወደ ቆዳችን እንዲመጣ/ እንዲዘዋወር ስለሚደረግ ጨጓራን ጨምሮ ሌሎች የአንጀት ክፍሎች በቂ የደም ዝዉዉር እንዳይኖራቸዉ ያደርጋል፡፡ ይህም ክስተት የምግብ መፈጨት ስርዓት ችግር ዉስጥ እንዲወድቅ ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛዉንም ምግብ ከተመገቡ በኃላ ሻወር መዉሰድ ከፈለጉ ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች መቆየት ይመከራል፡፡

· ምግብ ከተመገቡ በኃላ ወክ ማድረግ፡- ምግብ ከተመገቡ በኃላ ወዲያዉኑ ወክ ማድረግ ለምግብ ያለመፈጨትና ለአሲድ ወደ ላይ ተመልሶ ማቃጠል ( acid reflux) ያጋልጣል፡፡ ነገር ግን ምግብ ከተመገቡ ከ30 ደቂቃዎች በኃላ ወክ ማድረግ ለጡንቻዎች መፍታታትና ለምግብ መፈጫት ምቹ/ጥሩ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

· ምግብ ከተመገቡ በኃላ መተኛት፡- ከተመገቡ በኃላ ወድያዉኑ መተኛት ጥሩ አይደለም፡፡ ምክንያቱም በጨጓራችን ዉስጥ የሚገኙና ለምግብ መፈጨት የሚያገለግሉ ኬሚካሎች የአሲድነት ባህሪ ስላላቸዉ ወደ ጉሮሮ በመመለስ በጉሮሮ ላይና አፍ ዉስጥ የማቃጠል ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡በተጨማሪም ምግበ ከተመገቡ በኃላ በቀጥታ መተኛት ለሰዉነት ዉፍረት ሊያጋልጥ ስለሚችል ይህንን ለመከላከል ምግብ ከተመገቡ ከ2 ሰዓታት በኃላ መተኛት ይመከራል፡፡

10256208_455705854593640_2136122086148573414_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.