የሰዉነቴ ጠረን ተለወጠ/ሰዉነቴ ጠረን አመጣ ብለሁ አስበሁ/ተጨንቀዉ ይሆናል፡፡ ይህ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ነገር ግን የሰዉነትዎ ጠረን እንዲቀንስ/እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን 6 ምክሮች ይሞክሩዋቸዉ፡፡

1. ንፅህናዎን በደንብ አድርገዉ መጠበቅ፡- ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ሻወር በመዉሰድ የሰዉነት ላብንና በቆዳዎ ላይ ያሉ ባክቴሪያዎችን መቀነስ ይችላሉ (የቆዳ ድርቀት የሚያስቸግርዎ ከሆነ ወይም የቆዳ ችግር ካለዎ ቆዳዎ የበለጠ ለድርቀት እንዳይጋለጥ ሻወር በየቀኑ መዉሰድ አይመከርም)፡፡ ላብ በራሱ ሽታ የለዉም፡፡ ነገር ግን በቆዳችን ላይ የሚኖሩ ባክቴሪያዎች ከላብ ጋር በሚደባለቁበት ወቅት በፍጥነት ስለሚራቡ ላብ ጠረን እንዲያመጣ ያደርጉታል፡፡ ስለሆነም በተለይ ላብ በብዛት የሚያጠቃቸዉ ቦታዎችን በደንብ መታጠብ የሰዉነት ጠረንን ይቀንሳል፡፡ ላብ በጣም ከሚያልባቸዉ ሰዎች ይልቅ መጠነኛ ላብ የሚያልባቸዉ ሰዎች የሰዉነት ጠረን መለወጥ ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ ምክንያቱም ላብ በብዛት የሚያልባቸዉ ሰዎች ጠረንን ሊለዉጡ/ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በላብ ስለሚታጠቡ ነዉ፡፡

2. ባክቴሪያን መቀነስ የሚችሉ/ አንቲማይከሮቢያል ሳሙናዎችን መጠቀም፡- ሰዉነትዎን በሚታጠቡበት ወቅት ባክቴሪያን ሊያስወግዱ/ሊቀንሱ የሚችሉ ሳሙናዎችን መጠቀም፡፡ ይህን ማድረግ በሰዉነትዎ ላይ ያሉ ባክቴሪያዎችን መጠን ስለሚቀንሱ የሰዉነትዎን ጠረን ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡ ስለሆነም የሰዉነት ጠረን የሚያስቸግርዎ ከሆነ የገላ ሳሙና ሲገዙ ‘‘አንቲባክቴሪያል ” የሚል በሳሙናዉ መያዣ ላይ እንዳለ አይተዉ መሞከር ይችላሉ፡፡

3. ሻወር ከወሰዱ በኃላ ሰዉነትን በፎጣ በደንብ አድርጎ ማደራረቅ፡- ሰዉነትዎን ከታጠቡ በኃላ መላ ሰዉነትዎን በፎጣ በደንብ አድርገሁ ማደራረቅ፡፡ በተለይ ላብ በብዛት በሚያልብዎ ቦታዎች ላይ በደንብ መድረቁን ማረጋገጥ፡፡ ቆዳዎ በደንብ ከደረቀ የሰዉነትን ጠረን ሊለዉጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በቀላሉ በቆዳዎ ላይ ማደግ አይችሉም፡፡

4. ዶድራንቶችን ወይም የላብ መቀነሻዎችን መጠቀም፡- ሰዉነትዎን ከታጠቡና በደንብ ካደራረቁ በኃላ ዶድራንቶችን ወይም ላብ የሚቀንሱ ዶድራንቶችን በብብትዎ ስር መጠቀም፡፡ዶድራንቶች ላብን ባይከላከሉም በባክቴሪያ ምክንያት የሚመጡትን/የሚከሰቱትን መጥፎ ሽታዎች ይቀንሳሉ፡፡
የላብ መቀነሻዎች በዉስጣቸው አልሙኒየም ክሎራይድ ያላቸዉ ሲሆን ላብንና መጥፎ የሰዉነት ጠረን ለመቀነስ ያገለግላሉ፡፡ የሰዉነት ጠረን የሚያስቸግርዎ ከሆነ ጠንከር ያሉ ዲዎድራንቶችን ያለ ትዕዛዝ ሊገዙ የሚችሉ ሲሆን በሚገዙበት ወቅት ‘‘ከፍ ያለ ጥንካሬ ያለዉ” (higher strength due to ingredients) የሚል ፅሁፍ መዕቃዉ ላይ መኖሩን አይተሁ መግዛትና መሞከር ይችላሉ፡፡

5. የሚለብሱትን አልባሳት ንፅህና በደንብ መጠበቅ፡- በጣም የሚያልብዎ ከሆነ የሚለሱትን አልባሳት ቶሎ ቶሎ መቀያየር፡፡ አዳዲስ ልብሶች ( የታጠቡ) የሰዉነትዎን ጠረን ለመቀነስ ይረዱዎታል፡፡ የእግር ሽታ የሚያስቸግርዎ ከሆነም ካልሲዎንም ቶሎ ቶሎ መቀያየር ያስፈልጋል፡፡ የእግር ሽታን ለመቀነስ ዱቄት (ፓዉደር) ዲዎድራንቶችን በጫማዎ ዉስጥ መጠቀም፤የጫማዎን ሶል ቶሎ ቶሎ መቀያየርና ከቻሉ እግርዎን ለማናፈስ ባዶ እግር መሆን ይመከራሉ (ለምሳሌ በቤት ዉስጥ ሁሌ በነጠላ ጫማ/ ባዶ እግር መሆን)፡፡

6. ለሰዉነት ጠረን መለወጥ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ምግቦችንና መጠቶችን መቀነስ ወይም መተዉ፡- የሰዉነትዎን ላብ ሊጨምሩ የሚችሉ ምግቦች እንደ ቃሪያ ወይም ቅመማ ቅመም ያላቸዉ ምግቦች ለሰዉነት ጠረን መለወጥ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ሽንኩርት ወይም ነጭ ሽንኩርት ከተመገቡ ሽታቸዉ ከላብ ጋር ሊወጣ ስለሚችል መጥፎ ጠረን እንዲኖርዎ ያደርጋሉ፡፡ በዉስጣቸዉ ካፊን ያላቸዉ ነገሮች እንዲሁም አልኮሆል (መጠጥ) ሰዉነትዎን ብዙ እንዲያልብዎት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

 

10646750_443933555770870_8041868205657434354_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.