ዉድ የ8896 ሃሎ ዶክተር ወዳጆቻችን፣-እንደምታዉቁት ከሳምንታት በፊት ስለሞሪንጋ ጥቅምና አጠቃቀሙ ዉይይት እንዲደረግበት በፌስ ቡክ ድረገጻችን ላይ ለጥፈን የሞቀ ዉይይት እንደተደረገበት ይታወሳል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ላይክ፣ኮሜንት ላደረጉና፣በዉይይቱ ላይ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነዉ፡፡ ስለሞሪንጋ ተጨማሪ መረጃ እንድንሰጣችሁ በጠየቃችሁን መሰረት ለዛሬ በሞሪንጋ ላይ ተጨማሪ መረጃ እነሆ፡፡ እያነበቡ ይዝናኑ!!
ሞሪንጋ ከፊል ሂማሊያን አካባቢ በሚባሉ እንደ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ባንግላዲሽ እና አፍጋንስታን በብዛት የሚገኝ ሲሆን በሰሃራ አካባቢዎችም ይበቅላል፡፡ የሞሪንጋ ቅጠል፣ ቅርፊት፣ አበባዉ፣ ፍሬዉና ስሩ ለመድሃኒት መቀመሚያነት ያገለግላል፡፡
የሞሪንጋ ጥቅም፡- ሞሪንጋ ይሰጣል ተብሎ ለሚገመቱት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ጥቅሞች ተጨማሪጥናቶች በብዛት የሚያስፈልጉ ቢሆንም ሰዎች ሞሪንጋን ለተለያዩ ነገሮች ይጠቀሙበታል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ:-
ሞሪንጋን ሰዎች ለደም ማነስ፣ለመገጣጠሚያ ህመም(arthritis)ና ለሌሎች የመገጣጠሚያ ህመሞች (rheumatism)፤ ለአስም፣ ለካንሰር፣ ለድርቀት፣ ለስኳር ህመም፣ ለተቅማጥ፣ ለጨጓራና አንጀት አልሰሮች(ቁስለቶች)፣ ለሆድ ቁርጠት፣ ለራስ-ምታት፣ ለልብ ችግሮች፣ ለደም ግፊት፣ ኩላሊት ጠጠር፣ ለፈሳሽ መጠራቀም(እብጠት)፣ ለእንቅርት ችግር፣ ለፈንገስ፣ ቫይረስና ለፓራሳይት እንፌክሽኖች ይጠቀሙበታል፡፡
በተጨማሪም ሰዎች ሞሪንጋን እብጠትን ለመቀነስ፣ የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎትን ለመጨመር፣ እርግዝናን ለመከላከል፣ የሰዉነት የበሽታ መከላከልን ለማጎልበት እና የጡት ወተትን የመመረት ሂደት ለመጨመር ይገለገሉበታል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሞሪንጋን ለተጨማሪ ምግብነትም ይጠቀሙበታል፡፡

ሞሪንጋ በቆዳ ላይ በቀጥታ በመያዝ ጀርሞችን ለመግደልና ቁስልን ለማድረቅ(astringent) ይገለገሉበታል፡፡ በተጨማሪም የተወሰኑ እንፌክሽኖችን ለማከም፣ የእግር ፈንገሶችን፣ ፎረፎርን፣ የድድ ህመምን፣ ዋርት(ኪንቶሮትን)፣ ቁስልንና የእባብ መነደፍን ለማሻሻል ይረዳቸዋል፡፡
ከሞሪንጋ ፍሬ የሚገኘዉ ዘይት ለምግብነት፣ ለሽቶ፣ ለፀጉር እንክብካቤ ዉጤቶችና የማሽን ማለስለሻዎች መስሪያነትያገለግላል፡፡ ሞሪንጋ ለደም ማነስ፣ ለመገጣጠሚያ ህመም(arthritis)ና ለሌሎች የመገጣጠሚያ ህመሞች (rheumatism)፤ ለአስም፣ ለካንሰር፣ ለድርቀት፣ ለስኳር ህመም፣ ለተቅማጥ፣ ለጨጓራና አንጀት አልሰሮች(ቁስለቶች)፣ ለሆድ ቁርጠት፣ ለራስ-ምታት፣ ለልብ ችግሮች፣ ለደም ግፊት፣ ኩላሊት ጠጠር፣ ለፈሳሽ መጠራቀም(እብጠት)፣ ለእንቅርት ችግር፣ ለፈንገስ፣ ቫይረስና ለፓራሳይት እንፌክሽኖች ያገለግላል፡፡
በተወሰኑ የአለማችን ክፍሎች ሞሪንጋ ለምግብነት የሚያገለግል ሲሆን በቀላሉና ርካሽ በሆነ መንገድ ማምረት ስለሚቻልና ቅጠሎቹ ሲደርቁ ብዙ ቫይታሚኖችንና ሚኒራሎችን ስለሚይዝ በአፍሪካና በህንድ በምግብ ፕሮግራሞች ላይ የምግብ ዕጥረት ያለባቸዉን ለመመገብ ያገለግላል፡፡
ሞሪንጋ ፕሮቲን፣ቫይታሚንና ሚኒራሎችን የያዘ ነዉ፡፡ ሞሪንጋ አንታይ ኦክሲዳንት ስለሆነ ሴሎቻችን እንዳይጎዱም ይከላከላል፡፡
ሞሪንጋ በትክክል ከተወሰደ የሚያስከትለዉ ምንም የጤና ችግር የለም፡፡ ቅጠሉ፤ ፍሬዉና ዘሩ ለምግብነት አገልግሎት ከዋለ የሚያስከትለዉ ጉዳት የሌለዉ ሲሆን የሞሪንጋ ስሩንና ከስሩ የሚገኙ ነገሮችን መመገብ ግን ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ለምግብነት መዋል የለበትም፡፡ ስሩንና የስሩ ዉጤቶች መርዛማ ኬሚካሎች ስላሉት ሰዉነትን ፓራላይዝ(ማስነፍ)ና ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ ይችላል፡፡
ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባዎ
ነፍሰጡር ከሆኑና ጡት የሚያጠቡ ከሆነ፡- የሞሪንጋን ስር፣ቅርፊት ወይም አበባዉን እርግዝና ካለዎ ወይም እያጠቡ ከሆነ መመገብ ለአደጋ ሊያጋልጥዎ ስለሚችል መመገብ የለብዎም፡፡ በስሩ፣ በቅርፊቱና አበባዉ ዉስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ማህፀን እንዲኮማተር ስለሚያደርገዉ ለዉርጃ ሊያጋልጥዎ ይችላል፡፡ ሌሎቹን የሞሪንጋ ዘሮችን ለምሳሌ ቅጠሉን በእርግዝና ወቅት መጠቀም ጉዳት እንደሚያመጣና እንደማያመጣ የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ስለሆነም በእርግዝና ወቅት ማንኛዉንም የሞሪንጋ አካል ያለመጠቀም ይሻላል፡፡
ምንም እንኳ ሞሪንጋ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ሊያገለግል እንደሚችል ቢገለፅም በምንም መልኩ የህክምና ባለሙያዎች ለተለያዩ ህመሞች የሚያዙትን መድሃኒቶች አይተካም፡፡ ስለሆነም ህሙማን በህክምና ባለሙያዎቻቸዉ የታዘዘላቸዉን መድሃኒቶች ሳያቋርጡ በአግባቡ መዉሰድ አለባቸዉ/ይጠበቅባቸዋል፡፡

10945021_438731996291026_8796821315127049413_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.