(በዳንኤል አማረ እና ዳግማዊ ዳንኤል©ኢትዮጤና)

vegiጤነኛ ኩላሊት ማለት ልክ እነደ ልብ ጥቅም አለው፡፡ ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱ፣ የማይፈለጉ፣ ከመጠን በላይ የበዙ እና መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ከደማችን በማጣራት በሽንት መልክ ከሰውነታችን ያስወጋዳል፡፡ በተጨማሪም ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን የኔጌቲቭ ቻርጅ መጠን እና የተለያዩ ፈሳሾችን መጠን ይቆጣጠራል፡፡
ጤናማ ያልሆነ ኩላሊት የሚከተሉት ችግሮች ያመጣል፡፡ እነሱም፦
• ሽንት የመሽናት ችግር
• በአይን አካባቢ እብጠት መፈጠር
• የእግር እና እጅ ማበጥ
• ከብዙ ጊዜ በኋላ የልብ ችግር ያመጣል
• ንጽህናው የተጠበቀና ለጤንነት ጥሪ የሆነ ምግብ መመገብ በሰውነታችን ጤንነት እንዲሁም በትክክል ስራውን እንዲሰራ ያደርጋል፡፡
• በአብዛኛው አንቲ ኦክሲዳንት(Antioxidant) የሆኑ ምግቦች ለምሳሌ፦ እንደ ፍላቮኖይድስ(Flavonoids)፣ ሊኮፔን(Lycopene)፣ ቤታ-ካሮቲን(Beta-carotene) እና ቫይታሚን ሲ(Vitamin C) ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን የኩላሊት ጤንነትን ይጠብቅልናል፡፡
• አንቲ ኦክሲዳን(Antioxidant) በሰውነታችን ላይ የሚካሄደውን ኦክሲዴሽን(Oxidation) በነፃ ኤሌክትሮን እነዚህ ትርፍ ወይም ነፃ ኤሌክትሮን ዋናው በኩላሊት በሽታ መንስኤ ነው፡፡
6 ለኩላሊት ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦች እነሆ፦


1. ጥቅል ጎመን
ጥቅል ጎመን የኩላሊት ስራን ያፋጥናል በተጨማሪም ኩላሊትን በመጠገንና ስራውን አቀላጥፎ እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች ጥቅል ጎመንን እንዲመገቡ ይመከራል፡፡

2. ቤሪስ/ፍራፍሬ(Berries)
የማንጋኒዝ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ፋይበርና ፎሌት በጣም ጥሩ ምንጭ ነው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የቤሪስ ፍራፍሬዎች እንጆሪ፣ ክሬን ቤሪስ፣ ራስፕ ቤሪስ፣ እና ብሉ ቤሪስ ለኩላሊት ጥሩ ናቸው፡፡
ቤሪስ ፀረ ኦክሲዳንት እና ኢንፍላሜሽን ባህሪ አላቸው ስለዚህ የሽንት ፊኛ ተግናሩን በትክክል እንዲወጣ ያግዙታል፡፡ እነዚህ የቤሪስ ፍሬዎችን ወዲያው የተቆረጡ(ትኩስ)፣ የቀዘቀዙ ወይም ደረቅ መጠቀም ሲቻል በጥሬው መመገብ ወይም በመደበኛ የምግብ ዝርዝር ውስጥ በማስገባት መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡

3. አሳ
የአሳ ስጋ ወይም መረቅ በውስጡ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ(Omega-3 fatty acid) የሚባል ንጥረ ነገር በውስጡ ይዟል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር የሰውነት ቆዳችን እንዳይጨማደድ ያገለግላል፡፡ ኩላሊትን ከተለያዩ በሽታዎች ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም አሳ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምንጭ ነው ይህ ፕሮቲን ለሰውነታችን አስፈላጊ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች አንዱ ነው፡፡
ለኩላሊት ጠቃሚ ከሆኑ የአሳ ዝርያዎች መካከል፦ ሳልሞን(Salmon)፣ ሬይንቦ ትሮት(Rainbow trout)፣ማክከረል(Mackere;)፣ ኸሪንግ እና ቱና ናቸው፡፡ እነዚህን አሳዎች ቀቅለን፣ አብስለን፣ ጠብሰን ብንመገብ ይመከራል፡፡

4. እንቁላል
የኩላሊት በሽታ ላለባቸው ሰዎች የእንቁላል ነጩ ክፍል(ከአስኳሉ ውጭ) ያለውን እንዲመገቡ ይመከራል የዚህ ምክንያት እንቁላል በውስጡ ዝቅተኛ የሆነ ፎስፈረስ እና ጥራት ያለው ከፍተኛ ፕሮቲን በውስጡ ስላለው ነው፡፡ እነዚህ ከፍተኛ ፕሮቲኖች ጠቃሚ የሆነ አሚኖ አሲድ በውስጣቸው አላቸው ይህም ኩላሊት መደበኛ ስራውን እንዲወጣ ያግዘዋል፡፡ እንቁላሉን ከአስኳል ውጪ ቀቅለን፣ ጠብሰን መመገብ ጥሩ ጥቅም ያስገኛል፡፡

5. የወይራ ዘይት
የወይራ ዘይት ለልብ እና ኩላሊት ጤንነት ከፍተኛ አስተዋጽዎ አለው፡፡ ይህ ዘይት የኦሊክ አሲድ(Antioxidant) ጥሩ ምንጭ ሲሆን ፀረ ኢንፍላማቶሪ አሚኖ አሲድ ነው ኦክሲዴሽንን በመቀነስ የኩላሊት ጤንነት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም በፖሊፌኖል(Polyphenol) እና ፀረ ኦክሲዳንት የበለፀገ ሲሆን ኢንፍላሜሽን(inflammation ) እና ኦክሲዴሽንን በመከላከል ይጠቅሙናል፡፡
የወይራ ዘይትን ከሰላጣ፣ ዳቦ፣ አሳና አትክልቶች ጋር በመቀላቀል መመገብ ጥሩ ውጤት ያስገኛል፡፡

6. ነጭ ሽንኩርት
ነጭ ሽንኩርት አንቲ ኦክሲዳንት እና የደም መርጋትን በመከላከል ከፍተኛ ከፍተኛ ከሆነ የኩላሊት በሽታ ይታደገናል፡፡ አንድ ወይም ግማሽ ራስ ነጭ ሽንኩርት በየቀኑ በባዶ ሆድ መመገብ ጎጂ የሆነ የኮሌስትሮል መጠንን እና ኢንፍላሜሽንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ኩላሊትን በከፍተኛ ብረት(Heavy Metal) የሚከሰትን ጉዳት ይቀናሳል፡፡

መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.