መሠረታዊ የጥርስ እንክብካቤ ምክሮች

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)
teethመሠረታዊ የጥርስ ጤንነት በመደበኛ ሁኔታ ጥርስን መፋቅ/መቦረሽ እና በጥርሶቻችን መሃል ያሉትን ቆሻሻዎች ማስወገድን፣ በመደበኛ ጊዜ የጥርስ ህክምና ክትትል ለማድረግ የጥርስ ሃኪም መጎብኝትን እና ለጥርስ ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦችን መመገብ ያጠቃልላል፡፡ ምግቦች ስንል ጥራጥሬዎች፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎች እንዲሁም የወተት ተዋጽኦዎች ማለታችን ነው፡፡
መሠረታዊ የጥርስ እንክብካቤ ለምን አስፈለገ?
መሠረታዊ የጥርስ እንክብካቤን መተግበር የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኝልናል፦
• የጥርስ መበስበስን ይከላከላል
• የድድ በሽታን ይከላከላል- የድድ ስጋን እና ጥርስን የሚደግፉ አጥንቶችን ይጎዳል ከረጂም ጉዳት በኋላ ደግሞ የጥርስ መነቀል እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
• የጥርስ ሃኪም የምንጎበኝበት ጊዜ እንዲቀንሰ ያደርጋል፡፡
• ገንዘብን ይቆጥባል(ለህክምና የሚያወጡትን ወጪ ይቀንሳል)
• መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል ይረዳናል –
• ጥርስን በምግብ፣ በመጠጦች እና በሲጋራ ከመበላሸት ጠብቆ ነጭ እንዲሆን ያደርጋል
• አጠቃላላይ ጤንነታችን እንዲሻሻል ያደርጋል
• ጥርሳችን እስከ ዕድሜ ልክ እንዲቆይ ያደርጋል
የጥርሳችንን ችግር ለማስወገድ የሚረዱ መንገዶች
ጤናማ ጥርስ እና ድድ እንዲኖረን ለማድረግ ተመጣጣኝ ምግብ እና ጥርስን መፋቅ እና መቦረሽን ይጠይቃል
• ጥርስዎን በቀን ሁለት ጊዜ ይቦርሹ – ጠዋት እና ከመኝታ በፊት – በቀን አንድ ጊዜ ደግሞ በጥርስዎ መሃል ያሉ ቆሻሻዎችን ያውጡ፡፡ ይህ ጥርስን፣ ድድን እና በአካባቢ ያሉ አጥንቶች እንዳይጎዱና እንዳይበሰብሱ ያደርጋል፡፡
• የጥርስ መበስበስን ለመከላከል ፍሎራይድ ያለው የጥርስ ሳሙና ይጠቀሙ፡፡
• የስኳር መጠን በብዛት ያለቸው ምግቦች አለመመገብ፡፡ ስኳር ጥርስን ለሚያበሰብሱ ባክቴሪያዎች ምግብ ነው፡፡
• የትንባሆ ምርቶችን አለመጠቀም፡፡ እነዚህ ምርቶች የድድ በሽታ እና የአፍ ካንሰር ያስከትላሉ፡፡
• ምላስዎን ማጽዳት መልመድ አለብዎት፡፡ የምላስ ማጽጃ ወይም ለስላሳ የጥርስ ቡርሽ መጠቀል ተመራጭ ነው፡፡ በተለይ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ምላሳቸውን ማጽዳት አለባቸው፡፡
• ወደ ጥርስ ሃኪምዎ የሚሄድበት መደበኛ ጊዜ ይኑርዎት፡፡
ህፃናቶች ወደ ጥርስ ሃኪም መሄድ ያለባቸው መቸ ነው?
ህፃናት ዕድሜያቸው 6 ወር ሲሆን የጥርስ ሃኪም ጋር ቢሄድ መልካም ነው ምንም በኛ ሀገር ደረጃ ከባድ ቢሆንም፡፡ ከዚያም የጥርስ ሃኪሙ የልጅዎን የወደፊት የጥርስ እጣ ፋንታ ይወስናል ማለት ነው፡፡ የመጀመሪው ጥርስ ከወጣ ከ 6 ወር በኋላ ጀምሮ በየ 6 ወር ልዩነት ወይም ሃኪምዎ በመከረዎት የጊዜ ልዩነት ክትትል እንዲጀምሩለት ይመከራል፡፡
መልካም ጤንነት!!

 www.facebook.com/EthioTena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.