ፀጉርዎ እየሳሳ ነው….?

0

8d100cd2ee9a9e5acce2e9d17cc3718d_Mየፀጉር መሳሳት የበሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ የታይፎይድ እጢና የስኳር በሽታዎች የፀጉር መሳሳትን የሚያስከትሉ በሽታዎች ናቸው፡፡ ችግሩ ከመባባሱና አስከፊ ሁኔታ ላይ ከመድረስዎ በፊት ሃኪምዎን ያማክሩ፡፡
አመጋገብዎን ያስተካክሉ፡፡ የተስተካከለ አመጋገብ ጤናዎንና አካልዎን ብቻ ሳይሆን በፀጉርዎ ላይም የራሱን አሉታዊና አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ማሳረፍ ይችላል፡፡ ስለዚህም ስለሚመገቡት ምግብ ምንነትና ጠቀሜታ አብዝተው ይጨነቁ፡፡
አዕምሮዎንም ሆነ ሰውነትዎን ያሳርፉ፡፡ ድካምና እረፍት ማጣት የፀጉር መመለጥን (መሳሳትን) ከሚያስከትሉ ምክንያቶች ዋንኞቹ ናቸው። ህይወትዎ ምንም ያህል በውጥረት የተሞላ እንኳን ቢሆን ለራስዎ ጊዜና እረፍት መስጠት ይኖርብዎታል፡፡  እንደ ዮጋና ሜዲቴሽን፣ ያሉ ነገሮች ጭንቀትና ውጥረትን ለማስወገድ እጅጉን ይረዳሉ፡፡ ለፀጉርዎ የሚጠቀሟቸውን ሻምፖና ኮንድሽነሮች እንዲሁም የሚቀቧቸውን ቀለማት ምንነትና አጠቃቀም በደንብ ይረዱ፡፡ በአግባቡ ያልተረዷቸውን ምርቶች ከመጠቀም ይቆጠቡ፡፡
በሻምፖ፣ በኮንድሽነሮችና በፀጉር ማቅለሚያዎች ውስጥ ያሉት ኬሚካሎች የፀጉር መሳሳትና መመለጥን ከሚያፋጥኑ ነገሮች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ከእነዚህ ይልቅ ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን ያልለቀቁ ንጥረነገሮችን አዘውትረው ይጠቀሙ።ምንጭ – አዲስ አድማስ

 

Spread the love
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.