(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

1. ጭንቀት
ይህ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የልብ ህመም ምልክት ነው፡፡ ድንገተኛ የልብ ህመም ከመከሰቱ በፊት ፍርሀት ፍርሀት የማለት ስሜት ሊኖር ይችላለ፡፡
2. የደረት መጨምደድ
ደረት ላይ የመጨምደድ ስሜት እጅግ የተለመደ የልብ ህመም ምልክት ነው፡፡ ከልብ ህምም ጋር ያልተያያዘ የደረት መጨምደድ በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው የልብ ህመም መገለጫ ነው፡፡ ደረቶን በመጫን የመሸምቀቅ ወይም የመጨምደድ ሲሜት ሲሰማዎ ወደ ህክምና በመሄድ ሀኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
3. ሳል
የማያቆም ሳል ወይንም ሲሰርሲርታ የሚያስቸግሮ ከሆነ እንዲሁም በሚያስሉ ግዜ ደም የተቀላቀለበት አክታ ካሎት ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
4. ማዞር
ድንገተኛ የልብ ህመም የማዞር ስሜር እንዲኖር ያደርጋል ከዛም ባለፈ እራስን እስመሳት ሊደርስም ይችላል
✔ ድካም
ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ የድካም ስሜት መሰማት በቀጣይ ቀናት ውስጥ ድንገተኛ የልብ ህመም ለመከሰት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪሞን ማማከር ይኖርቦታል፡፡
5. ማቅለሽለሽ ወይንም የምግብ ፍላጎት መቀነስ –
ማቅለሽለሽ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ አልፎ አልፎ የድንገተኛ የልብ ህመም መከሰት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
6. በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚከሰት ህመም
ድንገተኛ ልብ ህመም ከመከሰቱ አስቀድሞ የህመም ስሜት የሚጀምረው ከደረት ከዛም ወደ ትከሻ(የግራ ትከሻ) ወደ ክንድ ፤ ጀርባ ፤ አንገት ፤ መንገጭላ አካባቢ ነው፡፡ ጨጓራ አካባቢ የማቃጠል ስሜትም ሊከሰት ይችላል፡፡
7. ትንፋሽ ማጠር
በቀላል አንቅስቃሴ ከፍተኛ የሆነ ትንፋሽ ማጠር የሚከሰት ከሆነ ከሳንባ ህመም በተጨማሪ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ችላ ሊባል አይገባም፡፡
8. ማላብ
በተቀመጡበት በላብ መስመጥ የድንገተኛ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡
9. የሰውነት እብጠት
የልብ ስራ በሚስተጓጎልበት ግዜ በሰውነታችን ውስጥ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል፡፡ ይህም የሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እንዲያብጡ ያደርጋል (እግር ፣ ቁርጭምጭሚት እና ሆድ አካባቢ) ፡፡ ፈጣን የሆነ ሰውነት ክብደት መጨመርም እንዲታይ ያደደርጋል፡፡
10. የልብ ምት መጨመር ወይም የተዛባ የልብ ምት
የልብ ምት መጨመር ከማዞር ፣ የድካም ስሜት ከመሰማት እና ትንፋሽ ከማጠር ጋር ተያይዞ ከመጣ ድንገተኛ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ወደ ሀኪም መሄድ ተገቢ ነው፡፡

ይህንን ጠቃሚ ምክር ለወዳጆ ያካፍሉ !
ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.