የጡት ካንሰር  ካንስር ምንድነው?

የጡት ካንሰር በጡት ውስጥ ካሉ ሴሎች የሚጀምር ነው። የጡት አካል በውጪ ከምንመለከተው የበለጠ ሰፋ ያለ አካልን ይሸፍናል። የጡት አካል አንገት ስር እና ከደረት መካከል ካለ አጥንት እስከ ብብት ድረስ የሚያጠቃልል ነው። ጡት የጎድን አጥንትን በሚሸፍን ጡንቻ ላይ የተቀመጠ አካል ነው። እያንዳንዱ ጡት ከዕጢዎች፤ ወተት ማስተላለፊያ ቱቦዎች (ducts) እና ስብ (fatty tissue) የተሰራ/የያዘ ነው። ሎቡልስ (lobuls)የሚባሉት ደግሞ ወተት የሚያመነጩ ዕጢዎች ስብስብ ነው። ወተት ከሎቡልስ ውስጥ በተጠላለፉ የወተት ማስተላለፊያ ቱቦዎች (network of ducts) በኩል/አማካኝነት ወደ ጡት ጫፍ ይፈሳሉ። የጡት ጫፍ በጡት ላይ  ቀለሙ ጥቁርና ክብ በሆነ ቆዳ አርኦላ(areola) ተብሎ በሚጠራው መካከል የሚገኝ ነው። ስብ የሆነው የጡት አካል በዕጢዎችና ወተት ማፍሰሻ ቱቦዎች መካከል የሚገኝና ለእነርሱ ጥበቃ የሚያደርግ ነው። breast Cancer የሴት ጡቶች በተለያየ የወር አባባ ጊዜ የተለያየ ስሜትን ሊሰጡ ይችላሉ። አንዳንዴ ከወር አባባ በፊት እብጠት ሊያሳዩ ይችላሉ። በጡት ውስጥ ያለ አካልም ከእድሜ ጋር ይለዋወጣል። በወጣት ሴቶች ላይ ጡት አብዛኛውን ጊዜ ዕጢዎችና ወተት ማፍሰሻ ቱቦዎች ይገኛሉ። ነገር ግን በእድያቸው ገፋ ያሉ ሴቶች ጡቶች በአብዛኛው የተሞላው በስብ ነው።  ከዚህ በተጨማሪ ጡቶች የዕጢ ሙሉ አካልን ይህም የዕጢ ከረጢቶች (vessels) እና ዕጢዎችን (lymph nodes) የያዘ ነው። የዕጢዎች ሙሉ አካልን ከኢንፌክሽን (በሴሎች ላይ የሚደርስን ቀውስ) የሚከላከል ነው። የዕጢ ከረጢቶችም ከዕጢው የሚመነጨውን ፈሳሽ ወደ ሊምፍ ኖድ ያስተላልፋሉ። ሊምፍ ኖዶችም ባክቴሪያን (ቀውስን የሚያመነጩ ህዋሶችን)፤ የካንሰር ሴሎችንና ሌሎች ጤንነት የሚያውኩ ነገሮችን ይጠምዳሉ/ያኮላሻሉ። በቡድን/ስብስበብ ያሉ ዕጢዎች  ደግሞ በጡት አካባቢ በሆነው በብብት ውስጥ፤ ካንገት ስር ካለው አጥንት አጠገብ እና በደረት ላይ ከጡት አጥንት (breastbone) ጀርባ ይገኛሉ። የካንሰር ሴሎች ከወተት ማፍሰሻ ቱቦዎች ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ ይህም ደክታል ካርሲሞንያ (ductal carcinoma) ወይንም ሎብሎች ውስጥ ያለ/ሎቡላር ካርሲሞና (lobular crcinoma) ተብለው ይታወቃሉ። ደክታል ካርሲሞና በብዛት የሚታይ ካንሰር አይነት ነው። ሌሎች የጡት ካንሰር አይነቶች ኢንፍላማቶሪ የጡት ካንሰር ((inflammatory breast cancer) እና ፓጄተስ በሽታ (Paget’s disease) ሲሆኑ እነዚህም የተለየ ባህሪ ያላቸው እና የተለየ አይነት ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ ይህ ገጽ ስለ ደክታል እና ሎቡላር  ካርሲሞና የሚመከለከት መረጃን የያዘ ነው። ስለሌሎች የጡት ካንሰር የሚመለከት መረጃ ከሌሎች ምንጮች ማግኘት ይቻላል።

የጡት ካንሰርን ማረጋገጫ ምርመራDiagnosing breast cancer

በሚከተሉት ምክንያቶች ሀኪምዎ የጡት ካንሰር ሊኖርብዎ ይችላል ብለው ይጠረጥሩ ይሆናል።– የማሞግራም ምርመራ ውጤት ችግሩን አመልክቶ ከሆነ- በጡትዎ ወይንም በጡትዎ ጫፍ ላይ ለውጥ አለ ብለው ለሀኪምዎ ተናግረው ከሆነ-  በጡትዎ አካል ላይ ምርመራ በማድረግና ስለጤንነትዎ እና ስለ እርስዎና ቤተሰብዎ የህክምና ታሪክ ከሰሙ በሗላ በጡትዎ ውስጥ እባጭ ካለብዎት ሀኪምዎ መጠኑ፤ ቅርጹና ይዘቱ የአካል ምርመራ በማድረግ ሊረዱትና እብጠቱ በጡትዎ ውስጥ መንቀሳቀሱን ለማወቅ ይችላሉ።  ካንሰር የሌለባቸው እብጠቶች ሲዳበሱ የሚሰጡት ስሜት ካንሰር ካለባቸው እብጠቶች የተለየ ነው። ምርመራውን ለማረጋገጥ  ሀኪምዎ የተለየ ምርመራ እንዲያደርጉ ያመቻቹልዎታል/ያነግሩዎታል። ይህ የተለየ ምርመራ ካንሰሩ ያለበትን  ደረጃና (stage) ይዘቱን (grade)  ለመለየት ይረዳል።  ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መካከል አንዱን ወይንም ካዛ በላይ ምርመራዎች ሊኖርዎት ይችላል።

የካንሰርን ደረጃና እርከን መለየት (Staging and grading)

አንዴ የካንሰር ምርመራ ተከርጎ ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ እና የህክምና ቡድኑ የሚያስፈልገው መረጃዎችን ካገኘ የካንሰሩ ደረጃና ይዘት ይለያል። የካንሰሩ ደረጃ የሚያመለክተው  የዕጢውን መጠን እና መጀመሪያ ከጀመረበት ቦታ አንስቶ ወደሌሎች የሰውነት አካል መሰራጨት አለመሰራጨቱን  ነው።በትንሽነት/ለጋነት ደረጃ ባለ የጡት ካንሰር ውስጥ የሚገኙት የካንሰር ሴሎች በወተት ማፍሰሻ ቱቦዎች ((milk ducts) ወይንም በሎቡልስ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ይህ ኢንሲቱ ካንሰር (in situ cancer) ተብሎ ይጠራል። ኢንሲቱ ካንሰር ከመሰራጨቱ በፊት ከታወቀ/ከተገኘ ተቆርጦ ከወጣ በሗላ ወደ ሌሎች የሰውነት አካል ክፍሎች ለመሰራጨት እድል የለውም።  የጡት ካንሰር ከበወተት ማፍሰሻ ቱቦዎች ወይንም ከሎቡል ውጭ ከተሰራጨ አጥቂ/ወራሪ ካንሰር (invasive cancer) ተብሎ ይጠራል። በጊዜ ከተደረሰበት ይህም ቢሆን በደንብ ሊታከም የሚችል ነው።  የጡት ካንሰር አምስት ደረጃዎች አሉት፦ የጡት ካንሰር የህክምና Treatment for breast cancer   ህክምና የሚሰጥዎትን ቡድን እድሜዎንና የጤናዎን ሁኔታ እንዲሁም በማረጫ እድሜዎ ውስጥ መሆን አለመሆንዎን ግምት ውስጥ ያስገባል። በተጨማሪ የካንሰሩን ደረጃና ይዘት፤ ሆርሞን ተቀባይ(ሪሴፕተር) እና የኤች አር 2 ሁኔታን በማገናዘብ ምን አይነት ህክምና/መድሃኒት እንደሚያስፈልግዎት በማጥናት ቡድኑ ሃሳብ ይሰጥዎታል። የህክምና ቡድኑ ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች የህክምናውን አይነት እንዲወስኑ ይረድዎታል። ጥያቄ ወይንም ስጋት ካለብዎት እነርሱን ያነጋግሩ።  የጡት ካንሰር አምስት ደረጃዎች አሉት፦
ስለ ጡት ካንሰር ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች ካስፈለጎት
Source: breastcancer-amharic.weebly

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.