gg_2የኩላሊት ጠጠርን ለማሟሟት ዝንጅብልን እንዴት እንጠቀም ?

ከስራ ስር ዘሮች የሚመደበው ዝንጅብል በሻይ መልክ ለጉንፋን እና ተያያዥ ህመሞች ማከሚያ እና ማገገሚያነት ሲውል ይስተዋላል።
ይሁን እንጅ ዝንጅብል ከዚህ ያለፈ ብዙ ጠቀሜታም አለው፤ በመተንፈሻ አካል ላይ ለሚከሰቱ የጤና እክሎች እና በሽታዎች ማከሚያነት በመዋል።
በተፈጥሮው ጥገኛ ህዋሳትን፣ ቫይረስን፣ ባክቴሪያዎችን እና ለሰውነት መቆጣትና ሽፍታ መንስኤ የሆኑ ነገሮችን መዋጋት የሚችል እና በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት እንደመሆኑ መጠንም በዚህ ዘመን ገበታ ላይ አስፈላጊው ነገር ሆኗል።

በቪታሚን ሲ፣ በማግኒዥየም እና በሌሎች አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገው ዝንጅብል፥ በሽታ የመከላከል አቅምን በማዳበር፣ ከህመም ቶሎ ለማገገም፣ የምግብ መፈጨትን ለማስተካከል እና አስምን ለመከላከል እና ለመዋጋት እጅግ አስፈላጊው ነው።

ከዚህ ባለፈም ለተስተካከለ የልብ ስርአት፣ አደገኛ ኢንፍሉዌንዛን ለመዋጋት እና ለመከላከል፣ የጡንቻ ህመምን ለማስወገድ፣ ለስርአተ ምግብ መንሸራሸር እና ሰውነት ለሚያገኘው የተስተካከለ የኦክስጅን ዑደትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

እስካሁን ከተነገሩለት እና ብዙዎቹ ከሚያውቋቸው ጠቀሜታዎቹ ደግሞ ለየት ያለ የጤና ጠቀሜታም አለው።

ይህም የኩላሊት ጠጠርን ማሟሟት፣ ጉበትን ማጥራትና ማጽዳት እንዲሁም ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ ህዋሶችን መግደልም ሌላው የዚህ ተክል ልዩ ጠቀሜታ ነው።

ይህን ጠቀሜታውን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ነገሮች፥

አንድ ብርጭቆ ውሃ
ሩብ የሻይ ማንኪያ በደንብ የተፈጨ ዝንጅብል
ሩብ የሻይ ማንኪያ ተፈጭቶ የደቀቀ እርድ
የኮኮናት ወተት
ወለላ ማር

አዘገጃጀት፦ በመጀመሪያ ውሃውን በደንብ ማፍላት ከዛም ዝንጅብል እና እርዱን የፈላው ውሃ ውስጥ መጨመር።

ከ7 እስከ 10 ደቂቃ አብሮ እንዲፈላ ማድረግ እና ከተባለው ጊዜ በኋላ የኮኮናት ወተቱን ጨምሮ ለሰከንዶች ማቆየት እና ከእሳቱ ላይ ማወረድ።

አብሮ የፈላውን ውህድ በብርጭቆ በመቅዳት እላዩ ላይ ትንሽ ወለላ ማር ጠብ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱም ማጣፈጫ ጨምሮ መጠቀም።

ይህን በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትንና ልዩ የሆኑትን የዚህን ተክል ጠቀሜታ ማግኘት እና ጤናን መጠበቅ ይቻላል።

ምንጭ፥ healthywayoflife.net

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.