(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
ጥፍረ መጥምጥ/የጥፍር ፈንገስ/ የምንለው በፈንገስ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጣን የጥፍር ሕመም ነዉ፡፡
የጥፍር ፈንገስ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• የጥፍር መወፈር
• አቅም የሌለውና የሚፈረፈር ጥፍር
• ቅርጽ የሌለው ጥፍር
• ጥቁር ቀለም ያለው ጥፍር
የጥፍር ፈንገስ የሚያስከትሉት ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
ይህ የኢንፌክሽን ዓይነት የሚከሰተው በፈንገስ አማካኝነት ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አንዳንድ ጠቃሚ ፈንገሶች እንዳሉ ሆኖ ለሕመም ወይንም ኢንፌክሽን የሚዳርጉንም ይገኛሉ፡፡
ፈንገስ በሞቃትና እርጥበታማ ቦታዎች አካበቢ የሚገኝ ሲሆን እንደ ውሃ ዋና ገንዳ እና የገላ መታጠቢያ ገንዳዎች ላይ ይዘወተራል፡፡
በሰውነታችን ላይ በሚገኙ መሰንጠቅ ወይንም መቆረጥ ምክንያት የሚመጡ ከፍተቶችን በመጠቀም ኢንፌክሽን ይፈጥራል፡፡
የእግር ጥፍር ለጥፍር ፈንገስ የበለጠ ተጋላጭ ነው፡፡ይህም የሆነበት ምክንያት በአብዛኛው በካልሲ እና ጫማ ውስጥ ስለሚቀመጥ ከሙቀት ጋር ተጨምሮ ለፈንገስ አመቺ የእድገት ቦታን ስለሚፈጥር ነው፡፡
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች?
• በዕድሜ ገፋ ያሉ ከሆነ
• ወንድ ፆታ
• በሞቃትና ወበቅ ያለበት ቦታ የሚያዘወትሩ ከሆነ
• ለእግርዎ በቂ አየር እንዳያገኝ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን እንደ ካልሲ እና ድፍን ጫማ ማዘውተር
• አብረዎት ዜሚኖሩት የጥፍር ፈንገስ ያለው ሰው ካለ
• በቆሻሻ ቦታዎች፣በመዋኛ ስፍራ እና መታጠቢያ አካባቢዎች እና በባዶ እግር መሄድ
• ቀላል የሚባል የቆዳ ላይ ጉዳት ካለብዎ
• የስኳር ሕመም ተጠቂ ከሆኑ
መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
• እጅና እግርዎን በመደበኛ ሁኔታ መታጠብ ጥፍርዎን በአጭሩ መቁረጥ እና ደረቅ በሆነ ሁኔታ መያዝ
• ላቦትን የሚያመጡ ካልሲዎችን መጠቀም እና በየጊዜው መቀያየር
• ወበቅን የሚያመጡ ጫማዎችን መጫማት
• ጥፍር አካባቢ የሚገኙ ቆዳዎችንም ሆነ ፈለግ በእጅዎ አይላጡ

ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
የጥፍር ፈንገስ ፋርማሲ በሚገኙ ፀረ ፈንገስ ክሬሞች በመጠቀም ማዳን የሚቻል ቢሆንም ጉዳዩ ከፍተኛ በሆነ ጊዜ በሓኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶችን መጠቀም ይኖርበታል፡፡ በተለይ የስኳር ሕመምተኞች የጥፍር ፈንገስ እንፌክሽን ካጋጠማችሁ ሐኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል፡፡
ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.