የጡት ጤንነትና ካንሰር ምርመራዎች

0

normal-anatomy-of-breast-tissueበሚከተሉት ምክንያቶች ሀኪምዎ የጡት ካንሰር ሊኖርብዎ ይችላል ብለው ይጠረጥሩ ይሆናል።

የማሞግራም ምርመራ ውጤት ችግሩን አመልክቶ ከሆነ · በጡትዎ ወይንም በጡትዎ ጫፍ ላይ ለውጥ አለ ብለው ለሀኪምዎ ተናግረው ከሆነ  በጡትዎ አካል ላይ ምርመራ በማድረግና ስለጤንነትዎ እና ስለ እርስዎና ቤተሰብዎ የህክምና ታሪክ ከሰሙ በሗላ በጡትዎ ውስጥ እባጭ ካለብዎት ሀኪምዎ በመጠኑ፤ በቅርጹና በይዘቱ ላይ የአካል ምርመራ በማድረግ ሊረዱትና እብጠቱ በጡትዎ ውስጥ መንቀሳቀሱን ለማወቅ ይችላሉ።  ካንሰር የሌለባቸው እብጠቶች ሲዳበሱ የሚሰጡት ስሜት ካንሰር ካለባቸው እብጠቶች የተለየ ነው። ምርመራውን ለማረጋገጥ ሀኪምዎ የተለየ ምርመራ እንዲያደርጉ ያመቻቹልዎታል/ያነግሩዎታል። ይህ የተለየ ምርመራ ካንሰሩ ያለበትን ደረጃና (stage) ይዘቱን (grade) ለመለየት ይረዳል።  ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መካከል አንዱን ወይንም ካዛ በላይ ምርመራዎች ሊኖርዎት ይችላል።

የምስል ጥናት Imaging Studies

የምስል ጥናት በጡት ውስጥ ያለውን የሰውነት ክፍሎች/ብልቶች እና አጥንቶችን በዝርዝር ለማሳየት ያስችላሉ። ራጂ (ኤክስሬይ)፤ አልትራሳውንድ፤ ሲቲ ስካን ወይንም ቦን ስካንን በመጠቀም የህምና አገልግሎት የሚሰጥዎት ቡድን በጡትዎ ውስጥ ያለውን ዕጢ መጠንና ወደ ሌላ የሰውነት አካልዎ መሰራጨቱን አለመሰራጨቱን የሚያሳይ ምስል ያገኛሉ። እነዚህ ምርመራዎች በሚደረጉበት ጊዜ የሚሰማ ህመም የለም እና ማደንዘዣ አያስፈልጋቸውም።፡ቀደም ብሎ የተነሱት የማሞግራም ምርመራ ቢኖርም እንኳ ለይቶ ለማወቅ የሚረዳ ሌላ ማሞግራም ምርመራ ሊደረግ ይችላል። በዚህ ምርመራ ወቅት ህመሙ የታየበትን ቦታና ጡትን በተለያዩ ገጽታዎች የሚያሳዩ ብዙ ምስሎች እንዲነሱ ይደረጋል። ማሞግራም መነሳት ጥሩ ስሜት የማይሰጥ ሊሆን ይችላል እንዲያውም ሊያም ይችላል ምክንያቱም ጡትዎ በሁለት ጠፍጣፋ ትሪ መሰል መስታወት መካከል ጫና ይደረግበታል። ከዚህ በተጨማሪ ምስሉ በሚነሳበት ወቅት ከአንድ ደቂቃ ያነሰ ቢሆንም ምንም ንቅናቄ ማድረግ ሳይኖርቦት መቆየት አለብዎት።

ባዮፕሲ (የናሙና ምርመራ) Biopsy Tests

የናሙና ምረመራ የሚያስፈልገው የካንሰር ህመም መኖሩን ለማረጋገጥ ነው። ይህ የሚደረገው ከሰውነት ውስጥ በሚወሰዱ ሴሎች ላይ በማጉሊ መሳሪያ (microscope) በማየት/በመመርመር ነው። ሴሎቹ ካንሰር ያለባቸው ከሆኑ በምን ያህል ፍጥነት እንደሚያድጉ ለማወቅ ቀጣይ ጥናት ይደረግባቸዋል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ  የጡት ናሙና ምርመራዎች/መንገዶች አሉ።· በረቀቀ መርፌ የሚወሰድ (Fine Needle Aspiration)፡ – ይህ ምርመራ በጣም ቀጭን መርፌን በመጠቀም ከዕጢ ውስጥ ያለውን ፈሳሽ ወይንም ሴሎች የሚወሰድበት ነው። ይህ ምርመራ ፈጣን ሲሆን ትንሽ ሊያም ይችላል ምክንያቱም ጡት ቶሎ የሚሰማው አካል ስለሆነ።·        ኮር ኒድል ባዮፕሲ (Core Needle  Biopsy)ግን ሀኪምዎ በትንሹ በተቆረጠ ቆዳዎ ውስጥ መርፌ በመክተት አንድ ወይንም ከዚያ በላይ ናሙና ከጡትዎ ውስጥ ይወስዳሉ። አስፈላጊ ከሆነ የራጂ (ኤክስሬይ) ወይንም አልትራሳውንድ ምስል በመደገፍ መርፌውን ወደ ዕጢው  ይልካሉ። የሚቆረጠውንና የሚወጋውን የጡት አካል ብቻ የሚያደነዝዝ  መድሀኒት ሊሰጥዎት ይችላል። ከዚህ በሗላ ለአጭር ጊዜ የህመም ስሜት (tenderness) እና መበለዝ ሊሰማዎት ይችላል።

የቀዶ ጥገና ናሙና ምርመራ Burgical Biopsy

 ይህ ሙሉ ወይንም ግማሽ የዕጢ አካል ተቆርጦ የሚወጣበትና ምርመራ የሚደረግበት ነው። ሁለት አይነት የቀዶ ጥገና ናሙና ምርመራ አለ። ኢንሲሽናል ባዮፕሲ  (incisional biopsy) የሚባለው ከዕጢው ወይንም ያልተለመደ ሁኔታ ካሳየው አካል ላይ ናሙና የሚወሰድበት ነው።ኤክስሽናል ባዮፕሲ excisional biopsy) ደግሞ ዕጢውን ሙሉ በሙሉ ወይንም ያልተለመደ ሁኔታ የሳየውን የጡት አካል ሙሉ በሙሉ ለናሙና  የምርመራ የሚወሰድበት ነው። የናሙና ምርመራው እንደሁኔታው በሀኪሙ ቢሮ ወይንም በሆስፒታል ውስጥ ሊደረግ ይችላል። ምርመራውም በተመላላሽ ታካሚነት መካሄድ ስለሚችል በሀኪም ቤት ውስጥ መቆየት አያስፈልግም። የሚሰጠውም ማደንዘዣ ጥቂት የሰውነት አካልን ብቻ የሚያደነዝዝ ነው።

የላቦራቶሪ ምርመራ Laboratory Test

በናሙና ምርመራው የጡት ካንሰር ተገኝቶ ከሆነ ሀኪምዎ ተቆርጦ በወጣው የጡት አካል ላይ የሚደረግ ተጨማሪ የላቦራቶሪ ምርመራዎች እንዲደረደጉ ሊያዙ ይችላሉ። እነዚህ ምርመራዎች ሀኪምዎን ሰለካንሰሩ የበለጠ እንዲያውቁ እና ለእርስዎ የተሻለ የሆነውን የህክምና  አማራጭን ማቀድ የሚያስችሉዋቸው ናቸው።·   ሆርሞን ተቀባይ/ሪሴፕተር ቴስት (Hormone  Receptor Status Test) ሴሎቹ የሆርሞን ሪሴፕተር እንዳላቸውና እንደሌላቸው የሚያሳይ ምርመራ ነው። ሪሴፕተር ያላቸው የጡት ካንሰር ሴሎች ለእድገታቸው ኤስትሮጅንና ፕሮጀስትሮን የተባሉት ሆርሞኖች ያስፈልጉዋቸዋል እና ዕጢው ለሆርሞን ቀና/ገብ የሆነ (hormone positive) ተብሎ ይጠራል። ይህንን የሆርሞን ሁኔታ ማወቅ የዕጢው ባህሪ እንዴት እንደሚሰራ እና ለሆርሞን ቴራፒ (የሆርሞን ህክምና) የካንሰር ሴሉ መስራት አለመስራቱን ለመተንበይ (ቀድሞ ለመገመት) ይረዳል። ሆርሞን ገብ/ቀና የሆኑ ዕጢዎች (hormone-positive tumours) በአብዛኛው የማረጫ እድሜያቸውን ባለፉ ሴቶች ላይ የሚታይ ነው። ·  ኤች ኢ አር 2 ቴስት (HER2) የተባለው ደግሞ  ኤች ኢ አር 2 የተባለው ፕሮቲን የካንሰሩን ጂን (በሴሉ ውስጥ) ውስጥ መኖርና አለመኖሩ የሚታወቅበት ምርመራ ነው።  ኤች ኢ አር 2  የሚለው ቃል human epidermal growth factor receptor 2 የሚል ነው።  ኤች ኢ አር 2  በጡት ሴሎች አካል ላይ የሚኖር  ፕሮቲን ሲሆን እድገታቸውን የሚያፋጥን/የሚረዳ ነው። አንዳንድ የጡት ካንሰር ሴሎች ብዙ  ኤች ኢ አር 2 ይኖራቸዋል። ብዙ ኤች ኢ አር 2 ወይንም ብዙ የሚቆጣጠረው ጂን ካለ ዕጢው ኤች ኢ አር 2 ፖሰቲቭ (HER2 positive) ተብሎ ይጠራል። ኤች ኢ አር 2 ያለበት የጡት ካንሰር ከሌሎቹ የካንሰር አይነቶች የተለየ ባህሪ ያለው እና የተለየ ህክምና የሚያስፈልገው ነው። አንዳንድ ጊዜ የደም ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። ደም ተወስዶ የሚደረገው ምረመራ ደግሞ የተለያዩ የደም ሴሎች ደህና መስለው ይታያሉ እና ጥራቸውም/ብዛታቸውም ደህና መሆኑ ይረጋገጣል። ይህ ሀኪሙ ጡትዎ ምን ያህል በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ/እንደሚሰራ ያሳየቸዋል። ይህም ካንሰር መኖር አለመኖሩንና መሰራጨት አለመሰራጨቱን ያመለክታቸዋል።
Source: breastcancer-amharic.weebly.com
Spread the love
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.