skin_cancer_slideshowየቆዳ ካንሰር በጣም ከተለመዱት ካንሰሮች መካከል እንዱ አይነት ነው። በአብዛኛውን ጊዜ ይህ ካንሰር የሚከሰተው በፀሐይ ምክንያት ነው። ሁሉም ሰው ማንኛውም አይነት ቀለምና ቆዳ ቢኖረው በቆዳ ካንሰር የመያዝ እድል አለው።
– የፀሐይ ጨረር ሀይለኛ በሚሆንበት ከጧቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለፀሐይ መጋለጥን ይቀንሱ።

– የፀሐይ መከላከያ ቅባት ፀሀይን የሚከላከል ንጥረ ነገር ያለውን (sunprotection factor SPF) 15 ወይም ከዚያ በላይ የሆነን በየእለለቱ መጠቀም ይችላሉ። ይህንንም ቅባት ለፀሐይ ከመጋለጥዎ 15 እስከ 30 ደቂቃ በፊት በመደጋገም ይቀቡት።
– ፀሐይ ውስጥ ሲሆኑ ይሸፈኑ። ጥሩ ከለላ የሚሰጥ ባርኔጣ፤ እጅጌ ሙሉ ሸሚዝ፤ ረጅም ሱሪ እና ጨረርን መከላከል የሚችል የፀሐይ መነጽር ያድርጉ።

– ደመናማ በሆነም ቀን ቢሆን ለፀሐይ ጨረር ይጋለጣሉ። መሸፈንና የፀሐይ መከላከያ ቅባት መቀባት ይችላሉ።
– የፀሐይ ጨረር በውሀ ውስጥ እንኳን ቢሆኑ ይደርስብዎታል። በሚዋኙበትም ጊዜ መከላከል ማስፈለጉን ያስታውሱ።
– በክረምትም ቢሆን ከውሀና ከበረዶ የሚንፀባረቅ ጨረር ምክንያት ቆዳዎ በፀሐይ ሊቃጠል (ሰን በርን) ይችላል። አመቱን በሙሉ የፀሐይ መከላከያ ቅባትን መጠቀምዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
– ፀሐይ በቆዳዎ ላይ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። ልጆችንም እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ያስረዱዋቸው።
– እድሜያቸው ከ6 ወራት በታች የሆኑ ሕፃናት ላይ የፀሐይ መከላከያ ቅባትን አይጠቀሙ። ጥላ ውስጥ ማድረግና በጨርቅ መሸፈን ያስፈልጋል።
– ቆዳዎን የሚያጠይም/የሚያጠቁሩ መብራቶች ለምሳሌ ሰን ላምፕ፤ ታኒንግ ቡዝ፤ ታኒንግ ክኒን ወይንም ታኒንግ ቅባት አይጠቀሙ። የፀሐይዋን ያህል ለቆዳዎ ጠር ነው።
– በሀኪም የታዘዘ መድሃኒት የሚወስዱ ከሆነ ከመድሃኒት ቅመማ ባለሙያ (pharmasist) ጋር ይነጋገሩበት። አንዳንድ መድሃኒቶች ቆዳዎን ለፀሐይ ብርሃን/ጨረር ስሜታማ (sensitive) ያደርገዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.